Рет қаралды 65,121
እንዲህ አይነት ግሩም ዝማሬ ሰምተን እንድንባረክበት በብዙ መስዋዕትነት ያቀረቡልንን የህብረት መዘምራንን ኢየሱስ እየባረከ ይባርክ።አሜን።
እናንተም ከተባረካችሁበት በኮመንት ላይ ተባረኩ በማለት ከዚህ የበለጠ ፀጋ እንዲበዛላቸው ደግፏቸው።
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን
APOSTOLIC CHURCH OF ETHIOPIA
watch full video #apostolicsongs #apostolicchurchsongs #ኢየሱስ #nahom terefe #viralvideo
እኔ የየሱስ ነኝ
ተገዝቻለሁኝ በዋጋ እንዳልሆን ለራሴ
ነፍስን እስከመስጠት በሚደርስ ፍቅር ተወድጄ
ደዌዬን ሁሉ ተቀብሎ ህመሜን ወስዶልኝ
ብቻውን ዋጋ ከፍሎልኛል ብቻውን ይግዛኝ
እኔ የኢየሱስ ነኝ /3
ይህንን በልቤ ጽፌ አትሜዋለው
አዎ ከእንግዲሀ ስለኔ ለሞተው እና ለተነሳው በህይወት ኖራለው
በሩን ከፍቼለት አንድ የክብር ንጉስ ወደ ልቤ ገብቷል
አይሆንም ለሌላ በቃ ተዘግቷል /2
ብርሃን እንድሆን ለጨለማው አለም በነፍሴ እንዲኖር ጨው
በፍቅር እየኖርኩ ክርስቶስን ላሳይ ተጠርቻለሁ አምላኬን እንድመስለው
ለሃጥያት ሞቼ ህይወቴ ከርሱ ጋር በሰማዩ ስፍራ
ኢየሱስ በክብር እስኪገለጥ ድረስ ተሰውሮ ይኖራል
እኔ የኢየሱስ ነኝ...
የሚናጠቀው ጊዜ ጉልበቴን በብርቱ የሚፈልገኝ
ለነፍሴ ማይጠቅመው ብዙ ነው ፈጽሜ እንዳልወደው ያረገኝ
ማደሪያው ለአምላኬ ይቀደስ ብቻውን በልቤ ይንገስ
ክብሩ አይልቀቅ ከስፍራው ትልቅ ሆኖ ይኑር ኢየሱስ
እኔ የኢየሱስ ነኝ...
ነፍሴን በፈቃዴ አስገዛለታለው ለጠራኝ በፍቅር /2
ብሞትም ኢየሱስ እንዲከብር
ብኖርም ኢየሱስ እንዲከብር
Apostolic Songs