Рет қаралды 3,520
አርቲስት ዘለቀ ገሠሠ በሙዚቃው ዓለም ከአራት አሥርት ዓመታት በላይ ያሳለፈና አለማቀፍ እውቅናን ያተረፈ አንጋፋ ሙዚቀኛ ነው። በሙዚቃ ሥራዎቹ መነሻውን ከኢትዮጵያ አድርጎ እስከ አለም አቀፍ መድረኮች ድረስ በመጫወት ለሬጌ ሙዚቃ የራሱን አስተዋጽኦ አበርክቷል። አርቲስት ዘለቀ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎቹም ይታወቃል።
በ Open Up ዝግጅታችን ለማርሊ ሌብል መፈረም፣ ከዚጊ ማርሊ ጋር የዘፈን ግጥምና ዜማዎችን መጻፍ፣ የአፍሪካውያን-አሜሪካውያን ማሕበር ባዘጋጀው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ብዙ ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት ማቀንቀን ምን እንደሚመስሉ ለመቲ አውግቷታል። ጨዋታ አዋቂው ዘለቀ እና መቲ በ MTV ስለተላለፈውና አርቲስቱ ስላዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት፣ በቅርቡ በፈረንጆቾ 2025 በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው One Love ኮንሰርት እና አርቲስት ዘለቀ በተደጋጋሚ ስላጋጠሙት የመኪና አደጋዎች፤ እንዲሁም ስለሌሎች የሕይወቱ ገጽታዎች ተጫውተዋል። ሁለቱ ተነግሮ ስለማያልቀው የአርቲስት ዘለቀ ሕይወት ያደረጉትን ጭውውት ሁለተኛውን ክፍል ጋበዝናችሁ።
ቀጣይ ክፍሎችና ሌሎች የፈንዲሻ ቲቪ ዝግጅቶችን እንደተለቀቁ ለማግኘት ሰብስክራይብ፣ ላይክ፣ ሼር በማድረግና ሀሳብ፣ አስተያየቶቻችሁን ኮሜንት በማድረግ የፈንዲሻ ቤተሰብ ይሁኑ።
#OpenUpWithMeti #ethiopianpodcast #zelekegessese #ethiopianmusic