Рет қаралды 10,181
አመሰግናለሁ እግዚአብሔር አምላክ ንጉስ ነውና
ሁሉን ይሁን ያለ ውብ አርጎ የሰራው እርሱ ነውና
ብቻውን የሚኖር በታላቅ ብርሀን ሰው በማይቀርበው
የፍጥረት መሰረት ተቆጣጣሪ ሁሉ በእጁ ነው
ላመስግነው ቆሜ እንደገና ጥበብ ሀይልም የእርሱ ነውና
ከንፈሮቼ ለእርሱ ይዘምሩ እስትንፋሴም ይሁን ለክብሩ
የእግዚአብሔር ቸርነት ምህረቱ ከቦኝ ነው ዛሬ ላይ መቆሜ
ትንፋሼን መንገዴን በእጆቹ የያዘው ሆኖልኝ አቅሜ
ወራት ተቆጠሩ አመታት አለፉ ዛሬም ዘምራለሁ
በህይወት እንድኖር ስለፈቀደልኝ አመሰግናለሁ
አቤት አቤት የእግዚአብሔር ቸርነት የእግዚአብሔር ምህረት
አቆመኝ እኔም ልስገድለት
እጄን ይዞኝ አምላኬ ወዶኛል ጌታ ራርቶልኛል
ሳመልከው እጅግ ደስ ይለኛል
ኧረ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ስንቱ ታለፈ
ኢየሱስ እየቀደመ
ወዳጄ እየቀደመ
ውድዬ እየቀደመ
ስንቱን ተራራ ባንተ አለፍኩኝ
ስንቱን ሸለቆ ውሀ ሞላኸው
ጌታዬ ባንተ ሁሉ ሆነልኝ
ክብር ምስጋና ላንተ ይድረስልኝ
በህይወቴ በኑሮዬ ጣልቃ እየገባ
ጣልቃ እየገባ ጣልቃ እየገባ
መንገዴን አቀና
ማእረጌ ነህ
ሁሉን ያለፍኩብህ
አምላኬ አምላኬ
አምላኬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ
ጌትዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ
ውድዬ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ
ኢየሱስ መታመኛዬ አንተ ነህ ለኔ ክብሬ
Ameseginalehu / Sintu Talefe
Daniel Amdemichael / Mesfin Gutu
Amharic Cover Gospel Song 2021