Рет қаралды 125,793
#EthiopianOrthodoxTewahido_AmharicMezmur #Based_on_EOTC | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር
|| Best Ethiopian Orthodox Tewahido Mezmur (Spiritual Song)
#Subscribe #Mezmure_Dawit_Tube
@MezmureDawitTube #Holy #bible
#the #fathe #the #son #the #holyspirit #one #God #Amen
እልል በሉ
እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
አመስግኑ ለክብሩም ዘምሩለት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ
በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን
ውለታው ግሩም ነው ክብር ለእርሱ ይሁን/፪/
እልል በሉ ................
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም/፪/
እልል በሉ .................
ሕይወቱን የሠዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩም አይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋር /፪/
እልል በሉ ....................
ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአማላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ
እልል በሉ..................