Рет қаралды 102
ቅድስት ድንግል ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው ይኽ በእውነትም ተአምር ነው። ንጽህተ ንጹሃን ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ከሴቶች ሁሉ የተለየች ከሴቶች መካከል የተባረከች እንደሆነች መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ በልዬ ልዬ ቦታ ተናግሮላታል። ከሴቶች መካከል ልዬ ከሚያደርጋት መካከልም አምላክን በማኅፀኗ መወሰኗ አንዱ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከመጸነስ ጀምሮ እስከምትወልድ ድረስ ብዙ ድንቅ ነገሮች በድንግል ማርያም ላይ ተከናውነዋል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልማደ አንስት ወይም የሴቶች ልማድ ፍጽሞ ያልነበረባት ከልማደ አንስት ውጭ የነበረች ብዙ ከአዕምሮ በላይ እንዲሁም ከህግ በላይ የሆኑ ድርጊቶች በእርሷ ተፈጽመዋል። በተለይም ጌታችን መድኃኒታችንን ከጸነሰችበት ጊዜ ጀምሮ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ ነው ብሎ አባ ኤፍሬም ሶርያዊው በውዳሴ ማርያም ድርስቱ እንደተናገረው። በዛሬው ቪዲኦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያለዘርዓ ብእሲ ከመጸነሷ በላይ በከብቶች በረት በግርግም ስትወልደው በልማደ አንስት ወይም በሴቶች ልማድ ምጥ በሌለበት መንገድ ሳታምጥ ወለደችው መባሉ እንዴት ይታያል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የምታገኙበትን ቪዲኦ አዘጋጅተናል።
It is called how Mary gave birth to her without conception. This is truly a miracle. The Bible has repeatedly said that the Virgin Mary, the pure mother of God, is different from all other women and blessed among women. One of the things that makes her special among women is that she conceived God in her womb, and in connection with this, many wonderful things were done to the Virgin Mary from conception to delivery. Our Lady, the Holy Virgin Mary, was a woman of custom or the custom of women, who was outside of the custom, many actions that were beyond the mind and beyond the law were done by her. In particular, what has been done by you since the time our Lord conceived our Savior is wonderful, as Father Ephraim the Syrian said in his essay in Praise of Mary. In today's video, we have prepared a video in which you will get an answer to the question of how it is said that Our Lady, the Holy Virgin Mary, rather than conceiving our Lord and Savior Jesus Christ without seed, gave birth to him in a stable in a manger with a traditional midwife or a woman's custom without giving birth to labor.