Рет қаралды 15,968
የኑሮ ውድነቱ ሁሉንም የሚፈትን ቢሆንም የመንግስት ሰራተኛውን ግን በተለየ ያጠቃዋል። ምክንያቱም የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ በጥቂቱ ለመጨመርም ዓመታትን መቆየት አለበት ነገር ግን ለኑሮ የሚያስፈልገው ወጪ በየቀኑ ይጨምራል።
መንግስት ለሰራተኞች ደሞዝ መጨመር በገበያው ሊፈጥር የሚችለውን የዋጋ ንረት በመስጋት (ግምታዊ!) ለውጥ ላለማከናወን ብዙ ምክንያት ቢደረድርም ሰራተኛው አማራጭ ባለማግኘቱ የመኖር አቅሙን አዳክሞታል።
የደሞዝ ጭማሪ እንደሚባለው የዋጋ ንረቱን እንደሚጨምረው እና እንደማይጨምረው እንዲሁም ደሞዝ ጭማሪን ሊተካ የሚችል የደሞዝ ማካካሻ (Wages) እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚያሳይ ይህንን ቪዲዮ አዘጋጅቻለሁ እስከመጨረሻው ተከታተሉት፡፡