Рет қаралды 1,572
#lyrics
ሰው ጥያቄውን ሊመልስ
ቁልቁል ሲደምር ሲቀንስ
የህይወትን ዋጋ ያሰላል
ዜሮን ፅፎ አንድ አለኝ ይላል
ከቁጥርም በላይ የላቀ
የማይታይ ግን የታወቀ
ዜሮነቴ ላይ ፊቴ ተፅፎ
ያከበረኝ ዋጋዬን አግዝፎ
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ አባት
የወደደኝ ያለምክንያት
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አለኝ ወንድም
የሚያበረታኝ ስደክም
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ ወዳጅ
ፍቅሩ ብርቱ የማያረጅ
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ እረኛ
የህይወቴ መተማመኛ
በልቤ የማኖረው
ከምንም ጋር የማልደምረው (+)
በዘመኔ ላይ የነገሰው
ከህይወቴ የማልቀንሰው (-)
የሚጨምር እጅግ የበዛ (×)
ማንነቴን ሁሉ የገዛ
ሞልቶ ተርፎኝ የማካፍለው(÷)
ኢየሱስ ነው አለኝ የምለው
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ አባት
የወደደኝ ያለምክንያት
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አለኝ ወንድም
የሚያበረታኝ ስደክም
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ ወዳጅ
ፍቅሩ ብርቱ የማያረጅ
አንድ አለኝ አንድ አለኝ አንድ እረኛ
የህይወቴ መተማመኛ
የዘመኔ ጥረት ጥሪቴ አንድ ያለኝ ቱባ ንብረቴ
የሰወርኩት በልቤ ሙዳይ የህይወቴ አብይ ጉዳይ
Contact - +251 949 764949