Рет қаралды 746
ምንም የሌለው የለም "Compassion"
የሰው ህይወት በእስትንፋሰ እግዚአብሔር መጀመሩ እሙን ነው። ይህም ከእግዚአብሔር ህይወትን በተካፈለ ቅፅበት የባህሪው ተካፋይ እንዲሆን አድርጎታል (communicable attributes)። ከተካፈልናቸው ባህርያት መካከል አንዱ ደግሞ ርህራሄ ነው ።
"ማቴዎስ ፱፣ ፴፮
ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።"
ለሰዎች የምናሳየው ርህራሄ የእግዚአብሔር ባህርይ ተካፋይ እንደ መሆናችን መጠን ወቅትና ጊዜ እየጠበቅን የምንገልጠው ሳይሆን ሁልጊዜ የምንኖረው እና የምናደርገው ተግባር ነው። አሁን ባለንበት ወቅት ሰው ከሚያልፍበት የራስ ትግል አንፃር ለሌሎች የማደርገው የለኝም በማለት ሰውን መርዳት ከገንዘብ ያለፈ እሳቤ እንዳለው የዘነጋ ይመስላል። በዛሬው ክፍል ስለ ርህራሄ አንስተን ተወያይተናል ተባረኩበት።
ለማንኛውም አስተያየት በዚህ የቴሌግራም አካውንት ይፃፉልን። t.me/MelhikPod...
#melhik #melhikpodcast #compassion