አርቲስት ሂሩት በቀለ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን | Hirut Bekele | Tamagne Beyene

  Рет қаралды 42,461

Tamagne Show

Tamagne Show

Күн бұрын

#TamagneShow #TamagneBeyene #TamagneMedia
የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፈርጥ አንጋፋ አርቲስት ሂሩት በቀለ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፡፡
( ‪@TamagneShow‬ ‪@tamagnebeyene‬ )
ሂሩት ከ1950ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድረስ የበርካቶችን የልጅነት፣ የጉርምስና እንዲሁም የአዋቂነት ዘመን በሙዚቃዎቿ ያደመቀች እንቁ ነበረች፡፡ በጊዜው ሴቶች በአደባባይ ስፍራዎች የመገኘት እድላቸው የተገደበ በነበረበትና በተለየም በኪነ ጥበቡ ዘርፍ የፈለጉትን ያህል ለመሳተፍ እድል በማያገኙበት በዛ ጊዜ፣ ሂሩት በዘመኗ ለነበሩ እንዲሁም ከዛ በኋላ ለመጡ ሴቶች እጅግ መነቃቃትን የፈጠረች አርቲስት ነበረች፡፡ ወደ 35 ዓመታትን በፈጀው የሙዚቃ ጉዞዋ፣ ሂሩት ከሁለት መቶ በላይ ሙዚቃዎችን የተጫወተች ሲሆን በ1986/87 ከሙዚቃው ዘርፍ በጡረታ ከተገለለች በኋላ፣ እራሷን ለእምነቷ አሳልፋ በመስጠት 3 የመንፈሳዊ መዝሙር አልበሞችን ሰርታለች፡፡
አንጋፋዋ ድምፃዊት ሂሩት በቀለ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም በተወለደች በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
ነፍስ ይማር !
[ ተጨማሪ ምስል 📽 Seifu On EBS ]
Our social Media Links
Facebook
✓ bit.ly/3M6mvzg
Instagram
✓ / tamagnemedia1
Telegram
✓ t.me/TamagneMe...
===============================
Tamagne Beyene Official Accounts
Facebook
✓ / artisttamagne
KZbin
✓ / @tamagnebeyene

Пікірлер: 50
@TamagneShow
@TamagneShow Жыл бұрын
kzbin.info/www/bejne/nWTPnnmqZ7OUbac
@sewyewyew4005
@sewyewyew4005 Жыл бұрын
የአባቴ ልጅ አንቺ በደህና እግዚአብሔር ወደጉያዉ ሰዉሮሻል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙየተመሰገነ ይሁን
@andualemmengistu9668
@andualemmengistu9668 Жыл бұрын
ታማኝ በየነ ሂሩትን ስላሰብካት እጅግ አመሰግናለሁ ነብስ ይማር ለዘመድ ለወዳጅ አድናቂዬቿ መጽናናትን እመኛለሁ ።
@yohannskebede6278
@yohannskebede6278 Жыл бұрын
ታማኝ አንተን ያቆይልን ፈጣሪ 🙏
@Eyerus879
@Eyerus879 Жыл бұрын
ነፍስዋ በሰላም ትረፍ 😢😢😢
@jelo3241
@jelo3241 Жыл бұрын
ልክ የሂሩትን ማለፍ ስስማ በመጀመሪያ ትዝ ያለኝ ታማኝ ነው ምክንያቱም በሁሉም interview ሁሉ ለሂሩት ያለውን ፍቅር ስለሚገልጽ አስታወስኩህ እግዚአብሔር ያጽናህ። ሂሩት እድለኛ ናት ወደ ተሻለው ቦታ ሄዳለች ታማኝዬ እጅግ በጣም እወድሃለው ለእግዚአብሔር ያለህ ነገር ደግሞ ይደንቀኛል ዘመንህ ሁሉ ያለምልመው ጌታ ኢየሱስ በነገር ሁሉ ይባርክህ ይርዳህ !!!!
@melakudegene9581
@melakudegene9581 Жыл бұрын
😢1979 በሀገራችን አቆጣጠር አአ 100 አመት ሲከበር የቀበሌአችንን ባህል ያደመቅነው በሷ ዘፈን ነበር ዘመን በሀያ አምስት ሳንቲም ለስላሳ እየጠጣን የልጅነት ትዝታ መቼም አይረሳም We really miss and remember her forever 😢 RIP
@getahunbelay8651
@getahunbelay8651 Жыл бұрын
መቸም ፍጡር የሆነ ሁሉ ከሞት የሚቀር የለም ገና በለጋው እድሜአችን ትዝ ይለኛል በእድገት በህብረት የሥራና ይእውቀት ዘመቻ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ በነበረው የዘፈን ምርጫ ፕሮግራም ክፍለ ጊዜ የሒሩት በቀለና የጥላሁን ገሠሠ እንዲሁም የመሐመድ አሕሙድ ዘፈን የማያቀሩ ነበሩ የሂሩት ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ ነበር ነፍስሽን በአፅደገነት ያኑርልን🙏🏾🙏🏾🙏🏾
@جيزان.محمدالطاهش
@جيزان.محمدالطاهش Жыл бұрын
የሒሩት ድምፅ የኔ አሳዛኝ የኔ ልዩ በምን ልግለፅሽ ዘፈኖችሽ አብረውኝ ይኖራሉ ውስጤን ነው የተሰማኝ በጣም
@tessemaabera2547
@tessemaabera2547 11 ай бұрын
ሂሩት በቀለ ለሀገራችን ለኢትዮያ ላበረከትሺው በድምፃዊነት በጦር ግንባር ለሰራዊቱ ሞራል በመስጠት ለሀገር ከፍ ያለ ውለታ አበርክተሻል ኢትዮጰያ ሁሌም ታስብሻለች ነብስ ይማር
@abebeche722negash
@abebeche722negash Жыл бұрын
ኡፍፍፍ አይ ታማኙ ስውድህ 🙏💚💛❤️
@teshagerzenebe241
@teshagerzenebe241 Жыл бұрын
ገና የሂሩትነ ማረፍ ስሰማ ያንተ ኢንተርቪ ነዉ ትዝ ያለኝ 😂 ግን አግኝተሀት ይሆን ?
@kokiaweke1767
@kokiaweke1767 Жыл бұрын
በጣም የምወዳት አንጋፋ ሙዚቀኛ ነበረች ሀዘኔ ከልብ ነው ነፍስ ይማር ሂሩትዬ 😥💔🙏
@ezanateferi346
@ezanateferi346 Жыл бұрын
Herutya belgnta ysmahut zone kaymroya altefam 1973 yserashew nbshe bgnte tehune
@dawitandesso8157
@dawitandesso8157 Жыл бұрын
One of the legendary Ethiopian history music always l respect proud of you from the beginning at the end
@ሀሊማመሀመድ-ተ6ዘ
@ሀሊማመሀመድ-ተ6ዘ Жыл бұрын
አይይይ ታማኝ ሂሩት ሞተች ሲባል ቅድሚያ አተ ትዝ አልከኝ ፈጣሪ ፅናቱን የሚሉ ስጥህ
@seyoumalemseged8182
@seyoumalemseged8182 Жыл бұрын
I have been so lucky person to work with hirut bekele she was great human being inside and out i Love hirut for ever
@hibreworkbogale4370
@hibreworkbogale4370 Жыл бұрын
"No justice No peace "LESS talk more actions. Amhar is not disarming. Mr Abey should be able to court for genocide criminal justice. More than one million tigray and Amhar die.
@salemamen7170
@salemamen7170 Жыл бұрын
ጎበዝ አንተን አየሁ አጀንዳችን መሆን ያለበት የ አማራ ህዝብ ጭፍጨፋ ነው ሁላችንም አይናችንን ከሱ ላይ ማንሳት የለብንም
@nunubelete8142
@nunubelete8142 Жыл бұрын
የእውነት ሁሉን ያሞላች ደርባባ አለባባስዋን ጨምሮ የምታኮራ ድንቅ ኢትዮጵያዊት ነበረች እህቴ ነፍስሽ በሰላም ትረፍ 🙏💚💛❤ 🙏💔
@addisalemzeleke
@addisalemzeleke Жыл бұрын
Yess
@habeshawit2008
@habeshawit2008 5 ай бұрын
ሂሩትዬ😢😢😢😢😢 ምን ይደረግ እግዚአብሔር አዋቂ ነው
@mahidawed8016
@mahidawed8016 Жыл бұрын
ያ ማለፊያው ዓይንህ እና አለኝ የማዋይህ የምንጊዜም የኔ ምርጥ የሒሩት ዘፈኖች
@mogesgetachew855
@mogesgetachew855 Жыл бұрын
Hirut Bekele! Used to be one of the best gifted human being who entertained Ethiopian people in good and bad time. Nothing forever in this world makes very sad Especially at this time except trashes. God bless you forever
@leteyletey3923
@leteyletey3923 Жыл бұрын
💔😭😭😭😭😭😭💔💔💔
@yeshumethiolove275
@yeshumethiolove275 Жыл бұрын
ውይ ታማኝ ልክ እኔ አለባቸው ተካን እንደምወደው ማለት ነው 😢ነፍሳቸውን ይማር
@alganeshbahre8598
@alganeshbahre8598 Жыл бұрын
I met Hirut in person
@mequanentyohanes4713
@mequanentyohanes4713 Жыл бұрын
እኔም በጣምምምምም ነው ምወዳት
@Ethiohabtina
@Ethiohabtina Жыл бұрын
hirut, enem sisemat betesebochen new yemastawusew inam ina yelijinet tizitayen new yemitametabigne. my parents had all her kasets and she was my parents favorite.
@mahtebubekele9342
@mahtebubekele9342 Жыл бұрын
We have many cassettes of Hirut .our families love her music n listen on Saturday afternoons resting. I carry her cassettes to field trips in Harareghe
@jestsforall7040
@jestsforall7040 Жыл бұрын
Hirut Bekele one of great Ethiopian icons Legend RIP !!
@tr7094
@tr7094 Жыл бұрын
ታማኝየ አንተም መተኪያ የሌለህ አርቲስታችን ነህ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር እመኝልኅለው!!! ሂሩቴንም እግዚአብሔር ከደጋጉች ጋር ያሳርፍልን!
@Bnnbvj
@Bnnbvj Жыл бұрын
Rip😂🙏
@tigistb4317
@tigistb4317 Жыл бұрын
Rip
@mehrets.tadesse1170
@mehrets.tadesse1170 Жыл бұрын
Rest in peace 🙏🏽
@tekleababera1965
@tekleababera1965 Жыл бұрын
RIP👍👍Big Respect ሂ ሩ ት በ ቀ ለ ❤️❤️
@stighehanaghebreyesus1696
@stighehanaghebreyesus1696 Жыл бұрын
Reast in peace
@abebenegash9988
@abebenegash9988 Жыл бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤😂😂😂😂😂
@መሰረትየታደስልጅአባቴንና
@መሰረትየታደስልጅአባቴንና Жыл бұрын
ውይ በስማም ሞተች ነፍስን ይማርልን
@mahderassefa2986
@mahderassefa2986 Жыл бұрын
Hirut, Nefs Yimar
@Muledoyo
@Muledoyo Жыл бұрын
የምር በጣም ነዉ የምወዳት ነፍስ ይማር
@mariarossi6555
@mariarossi6555 Жыл бұрын
😭🙏
@ביטי-ש5ח
@ביטי-ש5ח Жыл бұрын
😭😭
@ኢትዮጵያለዘላለምትኑ-ቀ1ሠ
@ኢትዮጵያለዘላለምትኑ-ቀ1ሠ Жыл бұрын
RIP my mother
@Future979
@Future979 Жыл бұрын
የተለጠፈው ፎቶ የ አበባ ደሳለኝ ፎቶ ነው ነፍስ ይማር
@meharetugedele
@meharetugedele Жыл бұрын
ይመስላ ግን የሒሩት ነው
@abduseid5291
@abduseid5291 Жыл бұрын
እኔም አደንቃታለሁ
@mickimaraki7886
@mickimaraki7886 Жыл бұрын
ነብስ ይማር😢
@adanechtekle7636
@adanechtekle7636 Жыл бұрын
ነፍስ ይማር
Остановили аттракцион из-за дочки!
00:42
Victoria Portfolio
Рет қаралды 3,8 МЛН
ОТОМСТИЛ МАМЕ ЗА ЧИПСЫ🤯#shorts
00:44
INNA SERG
Рет қаралды 4,7 МЛН
iPhone or Chocolate??
00:16
Hungry FAM
Рет қаралды 42 МЛН
OYUNCAK MİKROFON İLE TRAFİK LAMBASINI DEĞİŞTİRDİ 😱
00:17
Melih Taşçı
Рет қаралды 12 МЛН
Episode 12: Bizunesh Bekele: Her Life, Her Music
22:29
Insight Ethiopia
Рет қаралды 64 М.
December 2012 - Hirut Bekele and Tefera Negash Testimony and Interview
1:13:35
Ethiopian Evangelical Church in Toronto
Рет қаралды 47 М.
Остановили аттракцион из-за дочки!
00:42
Victoria Portfolio
Рет қаралды 3,8 МЛН