የያማ ግዛት ታሪክ/Kingdom of Yamma የጃንጀሮ ግዛት ታሪክ

  Рет қаралды 376

Tarik History

Tarik History

Күн бұрын

የያማ ግዛት ታሪክ።
የያማ ወይም የየማ ግዛት በአሁኗ ኢትዮጵያ ይገኝ የነበረ ትንሽ ግዛት ነበረ። ይኽም በኦሞ ወንዝ እና በጅማ ጊቤ ወንዞች በተመሰረተ ልከማዕዘን ይገኝ ነበረ። በምዕራቡም በኩል የጅማ ግዛት በደቡቡ ደግሞ የጋሮ ግዛት ያዋስኑት ነበር። ቦር አማ፣ አዙሉ እና ቶባ የተባሉት ሦስቱም ተራራዎች ያለፈውን ግዛት መገኛ የሚለዩ ነበሩ። ግዛቱም የአሁኗን ሶኮሩ ወረዳ እና የም ዞንን ይይዝ ነበረ።
የግዛቱ ሌላኛው ስም ጃንጀሮ ይባላል። ነገር ግን ይህንን የአማርኛ ስያሜ በአሁኑ ጊዜ የግዛቱ ክፍል በሆነው በሆነው አካባቢ የሚኖሩት የየም ሰዎች አይቀበሉትም።
ከሲዳሞ ግዛቶች መካከል አንዱ ቢሆንም በ1886 እስከተካሄደበት ዘመቻ ድረስ ያማ ለመሻገር በሚከብዱት ወንዞቹ ምክንያት ከጎረቤቶቹ ተነጥሎ ያለ እና እጅግ ጥቂት ብቻ ግንኙነት የነበረው ግዛት ነበረ። ለመጀመርያ ጊዜ በአውሮፓውያን የተጎበኘው እ.ኤ.አ በ1614 ቢሆንም እስከ 1950ዎቹ መጨረሻ ግን ስለ አካባቢው በውጪ ሰዎች ዘንድ የነበረው መረጃ እጅግ አናሳ ሆኖ ዘለቀ።
ያማ በታሪክ መዝገብ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀሰው በይሥሐቅ ቀዳማዊ የድል ዘፈን ውስጥ ነበረ፤ ይኸውም ከአባይ ወንዝ በደቡብ ከሚገኙ እና ለንጉሰ ነገስቱ በፈረስ ግብር ከሚከፍሉ ግዛቶች መካከል ነበረ። የመጀመርያዎቹ የያማ ነገስታት ከሀልማም ጋማ ሥርወ መንግስት የወጡ ነበሩ። የምዋ ጎሳም ከሰሜን የመጣን ነን ብለው ሥርወ መንግስቱን ገለበጡ።
እ.ኤ.አ በ1614 አባ አንቶንዮ ፈርናንዴስ የተባሉ ቄስ በደቡብ በኩል በህንድ ውቅያኖስ በኩል ወደ ማሊንዲ የሚወስዳቸውን መንገድ እየፈለጉ በነበረበት ወቅት ግዛቱን ጎብኝተው ነበር። አባ ፈርናንዴስም የያማን ንጉስ አገኙት እና እንደገለጹትም፦
"እንደ ባህላቸው የስድስት ያርድ አካባቢ ከፍታ ያለው የምሽግ ማማ ላይ ነበረ፤ ወደ ከፍታው መውጫ ደረጃም ከጀርባ ነበረ። ሁሉም ባለ ሟሎቹ ከታች ቆመው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ በከፍታው ነበረ፤ በምንጣፍም ላይ ተቀምጦ ነበር፤ በዛም ሆኖ አከራካሪ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጥ እና ተግባራቱን ሁሉ ይከውን ነበር። ከሀር የተሰራ ነጭ የህንድ ልብስ ለብሶ ነበር፤ መልኩም ጥቁር ነበር።"
እ.ኤ.አ በ1844 የጅማ ግዛት ጦረኞች የያማን ሠራዊት በማሸነፍ የያማን ንጉስ በእስር ወሰዱ። ከሦስት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ በ1847ም ነፃነቱን በማግኘት ይበልጥ ጠንካራ ከነበረው ጎረቤቱ ጋር የነበረውን ትግል ቀጠለ።
እ.ኤ.አ በ1880ዎቹም ጅማ የያማ ክፍሎችን በጦርነት ወርሮ ያዘ። የተቀረው የግዛቱ ክፍልም እ.ኤ.አ በ1894 በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ተጠቀለለ። የመጨረሻው ንጉስ አባ ባጊቦም ወደ ጉራጌ አገር ሸሸ፤ ነገር ግን በመጨረሻ ለዳግማዊ ምኒልክ ተገዛ። ልጁ አባ ጫብሳም ክርስትያን ሆነ እና ገብረ መድኅን የሚል ስም ተሰጠው። ርስት የያዘውን ኢትዮጵያዊም አገልጋይ ሆነ።
ማጣቀሻ(Reference)
en.wikipedia.o...

Пікірлер: 5
@MrAbdallah-oq8hh
@MrAbdallah-oq8hh 4 ай бұрын
Good job ❤❤❤❤❤❤
@tarikhistory
@tarikhistory 4 ай бұрын
Thanks
@meseretgetawedey
@meseretgetawedey 4 ай бұрын
የየም ብሄር እንዳለ አላቅም ነበር የየም ህዝቦች ባህላችሁን ቋንቋችሁን አሰተዋውቁ❤❤❤🎉🎉🎉
@KukuKuku-q8s
@KukuKuku-q8s 4 ай бұрын
እኖ የማ 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
@korkut37
@korkut37 3 ай бұрын
እና የየም ህብዝ አመጣጥ ከየት ነው ከሀዲያ ጋር ዝምድነው ምንድነው?
ስለልጅ ኢያሱ ያልተሰሙ አስገራሚ ታሪኮች
16:05
Quilt Challenge, No Skills, Just Luck#Funnyfamily #Partygames #Funny
00:32
Family Games Media
Рет қаралды 33 МЛН
I thought one thing and the truth is something else 😂
00:34
عائلة ابو رعد Abo Raad family
Рет қаралды 12 МЛН
Farmer narrowly escapes tiger attack
00:20
CTV News
Рет қаралды 13 МЛН
እስክንድርን ያስደነገጠችው ታላቋ ሕንደኬና ጥበቧ
27:27
Dr Rodas Tadese አንድሮሜዳ Andromeda
Рет қаралды 39 М.