Рет қаралды 692
ዘይላ ጥንታዊ ከተማ ናት እና በጥንታዊ ጊዜ አቫላይትስ ተብላ ትጠራ የነበረች ሲሆን በሰሜን ምስራቅ አፍሪካ በርበራ ውስጥ የምትገኝ የንግድ ወደብ ነበረች። በጥንት ጊዜ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በህንድ መካከል ባለው ትርፋማ ንግድ ከተሰማሩ በርካታ የከተማ ግዛቶች አንዷ ነበረች። ነጋዴዎች ዕቃቸውን ለማጓጓዝ ቤደን በመባል የሚታወቀውን ጥንታዊውን የሶማሊያ የባህር ላይ መርከብ ይጠቀሙ ነበር።
በምዕራብ ከአል-ሐባሽ ሀበሾች ጋር በአካባቢው ይኖሩ የነበሩት ባርባሮኢዎች ፔሪፕለስ ኦቭ ኤሪትሬያን ሲ በተባለው የ1ኛው ክፍለ ዘመን የግሪክ ሰነድ መሰረት ከግብፅ እና ከእስልምና በፊት ከነበረችው አረቢያ ጋር ሰፊ የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር። የጉዞ ማስታወሻው እንደ አቫላይት ባሉ የወደብ ከተማዎቻቸው ከሌሎች የተለያዩ ሸቀጦች መካከል የባርባሮይ የንግድ እጣን ይሸጥ እንደነበረ ይጠቅሳል። የፔሪፕሉስ ጸሐፊ ብቁ መርከበኞች በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ለንግድ መጓዛቸውንም ይጠቁማል። ሰነዱ የባርባሮይ የአስተዳደር ሥርዓት ያልተማከለ እና በመሠረቱ የራስ ገዝ የከተማ-ግዛቶች ስብስብ መሆኑን ይገልፃል። በተጨማሪም "በቦታው የሚኖሩት የበርበር ሰዎች በጣም የማይታዘዙ ናቸው" በማለት ይጠቁማል፤ ይህም የእነርሱን ገለልተኛ ተፈጥሮ የሚያመለክት ነው።
እስልምና ወደ አካባቢው የተዋወቀው ከሂጅራ ብዙም ሳይቆይ ከአረብ ባሕረ ገብ መሬት ነው። የዘይላ ሁለት ሚህራብ መስጂድ አል-ቂብላታይን በ7 ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ ሲሆን በከተማው ውስጥ እጅግ ጥንታዊው መስጂድ ነው። በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ሙስሊሞች በሰሜናዊ ሶማሌ የባህር ዳርቻ ላይ እንደሚኖሩ አል-ያዕቁቢ ጽፏል። በተጨማሪም የአዳል ግዛት ዋና ከተማው እንደነበረው ጠቅሷል፤ የአዳል ሱልጣኔት የዘይላ ዋና ከተማ ቢያንስ በ9ኛው ወይም በ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን እንደተጀመረ ይጠቁማል። እንደ አይ ኤም ሉዊስ ገለጻ፣ ፖለቲካው የሚተዳደረው ሶማሌነትን በያዙ አረቦች ወይም አረብነትን የያዙ ሱማሌዎችን ባቀፉ የአካባቢ ሥርወ-መንግስቶች ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የተመሰረተውን የሞቃዲሾን ሱልጣኔት በደቡብ በኩል በቤናዲር ክልል ያስተዳድሩ ነበር። ከዚህ የምስረታ ዘመን ጀምሮ ያለው የአዳል ታሪክ ከጎረቤት አቢሲኒያ ጋር በተደረጉ ተከታታይ ጦርነቶች ይገለጻል።
ከ1214-17 በነበረው ጊዜ ኢብን ሰይድ ዘይላን እና በርበራን ጠቅሷል። ዘይላ እንደነገረን ከሆነ ትልቅ መጠን ያላት ሀብታም ከተማ ነበረች እና ነዋሪዎቿ ሙሉ በሙሉ ሙስሊም ነበሩ። የኢብኑ ሰኢድ ገለጻ በርበራ በይበልጥ አካባቢያዊ ጠቀሜታ እንደነበራት፣ በተለይም የቅርብ የሶማሌ አካባቢን እያገለገለች እንደነበረ፣ ዘይላ ደግሞ የበለጠ ሰፊ ቦታዎችን እያገለገለች እንደነበረ እንድምታ ይሰጣል። ነገር ግን ዘይላ በብዛት ሶማሊያዊ እንደነበረች ምንም ጥርጥር የለውም እና አል-ዲማሽቂ የተባለው ሌላው የአስራ ሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አረብ ጸሃፊ ለከተማዪቱ የሶማሊኛ ስም አዉሎድ (አዳል) የሰየመ ሲሆን አሁንም በአካባቢው ሶማሌዎች ዘንድ ይታወቃል። በአስራ አራተኛው ክፍለ-ዘመን ይህ የሶማሊያ ወደብ ለኢትዮጵያ ያለው ጠቀሜታ በጣም እየጨመረ በመምጣቱ ወደ መካከለኛው እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በሚደረገው የንግድ መስመር የተመሰረቱት የሙስሊም ማህበረሰቦች በሙሉ በግብፅ እና በሶሪያ በተለምዶ ይታወቁ የነበረው "የዘይላ ሀገር" ተብሎ ነበር።
የታሪክ አጥኚው አል-ኡማሪ በ1340ዎቹ በመካከለኛዎቹ ዘመኖች ምዕራባዊውን እና ሰሜናዊውን የሶማልያ አካባቢ እንዲሁም መሰል አካባቢዎችን ተቆጣጥራ ስለነበረው ስለ አውዳል ባደረገው ጥናት እንዲህ ብሏል “በዘይላ (አውዳል) ምድር በዓመት ሁለት ጊዜ የዝናብ ወቅትን ጠብቀው ያርሳሉ… በዘይላ ሰዎች (በአውዳሊ ሶማሌዎች) ቋንቋ የክረምት ዝናብ ‘ቢል’፣ የበጋ ዝናብ ደግሞ ‘ካራም’ ተብሎ ይጠራል።”
ስለ ወቅቶች የጸሐፊው ገለጻ በአጠቃላይ በታሪካዊው አውዳል ውስጥ ካራን ወይም ካራም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ጠቃሚ የዝናብ ወቅት ከሆነው የአካባቢ ወቅቶች ጋር ይዛመዳል። የዓመቱ ሁለተኛ አጋማሽ 'ቢሎ ዲሪር' ይባላል። (ቢል ማለት ወር፤ ቢሎ ደግሞ ወራት ማለት ነው) የታሪክ ምሁሩ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህን አሁንም ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትን ማለትም ካራንን እና ቢልን እየጠቀሰ ይመስላል። ይህ የሚያመለክተው የጥንት የሶማሌያውያን የፀሃይ የቀን አቆጣጠር የዘይላ ዜጎች ዛሬ ከሚጠቀሙት ጋር በጣም ተመሳሳይ መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የመካከለኛው ዘመን የዘይላ ነዋሪዎች በብዛት ሶማሌዎች እንደነበሩ፣ ሶማሊኛ ይናገሩ እና የሶማሌ የግብርና ልማዶችን ይተገብሩ እንደነበር ተጨማሪ ማረጋገጫ ይሰጣል።
በተከታዩም ክፍለ ዘመን፣ የሞሮኮው የታሪክ ምሁር እና ተጓዥ ኢብን ባቱታ፣ ከተማይቱ ብዙ ግመሎች፣ በጎችና ፍየሎች ያሏቸው የሻፊኢ አስተምህሮን የሚከተሉ ሶማሌዎች ይኖሩባት እንደነበር ገልጿል። የሱ ገለጻም የከተማዋን አሪፍ ተፈጥሮ በነዋሪዎቿ ስብጥር የሚመላክት እና የከብት እርባታ መገኘት በአካባቢው የሚኖሩ ዘላኖች መኖራቸውን ያሳያል። በተጨማሪም ዘይላን እንደ ትልቅ ዋና ከተማ እና በብዙ ሀብታም ነጋዴዎች የተሞሉ ብዙ ታላላቅ ገበያዎችን ገልጿል። ዘይላ የበርካታ ሃናፊዎች መኖሪያ እንደነበረች ይታወቃል ነገር ግን በቅድመ ዘመናዊት ዘይላ የሐናፊ ህዝብ ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ምንም አይነት ጥናት አልተደረገም።
ከአቢሲኒያ እና ከአረቢያ ጋር ሰፊ የንግድ ልውውጥ በማድረግ አዳል በ14ኛው ክፍለ ዘመን የብልጽግና ከፍታ ላይ ደረሰች። ዕጣን፣ ከርቤ፣ ባሮች፣ ወርቅ፣ ብርና ግመሎች ከሌሎች በርካታ ሸቀጦች ጋግ ትሸጥ ነበር። ዘይላ በዚያን ጊዜ ሶማሌዎች (በዋነኛነት)፣ አፋር፣ ሀረሪ፣ እና አረቦች እንዲሁም ፋርሳውያን ነዋሪዎች ወዳሉባት ወደ ግዙፍ የመድብለባህል ከተማነት ማደግ ጀመረች። ከተማዋ እስልምናን ወደ ኦሮሞ እና ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በማድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራት።
በ1332 የአቢሲኒያ ንጉሠ ነገሥት አምደ ፅዮን ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ዘመቻ ለማስቆም ዘይላን ማዕከሉ ያደረገው የአዳል ንጉሥ ባደረገው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ተገደለ። በ1410 የኢፋት የመጨረሻው ሱልጣን ዳግማዊ ሰአድ አድ-ዲን በዳዊት ቀዳማዊ በዘይላ ሲገደል ልጆቹ ወደ የመን አምልጠው ከዚያ በኋላ በ1415 ተመልሰዋል። በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የአዳል ዋና ከተማ ከባህር ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ዳካር ተዛወረ፤ የዳግማዊ ሰአድ አድ-ዲን የበኩር ልጅ ዳግማዊ ሳብር አድ-ዲን ከየመን ከተመለሰ በኋላ አዲስ ማዕከል መስርቶ ነበር። በተከታዩ ክፍለ ዘመንም የአዳል ዋና ከተማ እንደገና ወደ ሐረር ተዛወረ። ከዚች አዲስ ዋና ከተማም አዳል በኢማም አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ጋዚ (አህመድ ግራኝ) በመመራት የአቢሲኒያን ግዛት የወረረ ውጤታማ ጦር አደራጀች። ይህ ዘመቻ በታሪክ የአቢሲኒያ ወረራ (ፉቱህ አል ሀበሻ) በመባል ይታወቃል። በጦርነቱ ወቅት ግራኝ አህመድ በዘይላ ወደብ በኩል ከኦቶማን ግዛት የመጡለትን መድፎች በመጠቅም በአቢሲኒያ ጦር እና በፖርቹጋል አጋሮቻቸው በክሪስቶቮ ዳ ጋማ ጦር ላይ አሰማርቷል። አንዳንድ ምሑራን ይህ ጦርነት እንደ ነፍጥ፣ መድፍ እና ጠመንጃ ያሉ የጦር መሳርያዎችን መጠቀም ባህላዊ የጦር መሳሪያዎችን ከመጠቀም እንደሚሻል ያረጋገጠ ነው እያሉ ይሞግታሉ።
የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዘይላ በምስራቅ አፍሪካ የባህር ዳርቻ ከሚገኙ ሌሎች በርካታ ወደቦች ጋር በፖርቹጋላዊው አሳሽ እና ፀሃፊ ዱአርቴ ባርቦሳ ተጎበኘች፣ ከተማዋንም እንዲህ ሲል ገልጿታል፡- “ይህችን የበርበራ ከተማ አልፌ ወደ ቀይ ባህር መግባቴን ቀጠልሁ። ብዙ መርከቦች ተዘዋውረው ልብሶቻቸውንና ሸቀጣቸውን የሚሸጡባት ዘይላ የምትባል ሌላ የሙሮች ከተማ አለች። ብዙ ሰውም ይኖርባታል፤ በድንጋይ የተሰሩ ጥሩ ቤቶች፣ እና ጥሩ ሰፈሮች አላት፤ ቤቶቹም በእርከን የተከለሉ ናቸው፤ ነዋሪዎቹም ጥቁር ናቸው። ብዙ ፈረሶችም አላቸው፤ ብዙ ከብቶችን በሁሉም አይነት መንገድ ያዳቅላሉ፤ እነርሱንም ለወተት፣ ለቅቤ እና ለሥጋ ይጠቀሟቸዋል። በሀገሪቱም ስንዴ፣ ማሽላ፣ ገብስ እና ፍራፍሬ የተትረፈረፈ ነው፤ ይህንንም ተሸክመው ወደ አደን ይወስዳሉ።"
ማጣቀሻ(Reference)
en.wikipedia.o...