Рет қаралды 1,749
የሚያስጨንቀን ዋናው ነገር፡-
ሰው የመሆን ጸጋ እና ፈተናው አእምሯችን ላይ ነው::
ከተረዳነው ሰው የመሆን ጸጋው እጅግ ጥልቅ ነው:: ምክንያቱም በአእምሯችን ተጠቅመን የምናስበውን እና የምናምነውን ሁሉ መሆን፣ ማግኘት እና መስራት እድል የተሰጠን ፍጡር ነንና::
ካልተረዳነው ደግሞ ሰው የመሆን ፈተናው እንዲሁ ጥልቅ ነው:: አእምሯችንን እኛ በመጠቀማችን ፋንታ አእምሯችን እኛን የሚጠቀመን ከሆነ በሁለት መንገድ ምድር ላይ አለ ለተባለ ሁሉ ፈተና እንጋለጣለን፡-
1. የገጠመህን ፈተና በማግዘፍ ያሳይሃል::
2. አሁን ፈተና ከሌለ ወደ ትናንት ወይም ነገ ሄዶ ችግር በመፈለግ፡፡