Рет қаралды 65,102
የ አስራ ሁለት አመት ታዳጊን በልመና በስርቆት እና በመዋሸት ቤተሰቡን እንዲያሳዝን ያደረገው ክፉ መንፈስ እና የእግዚአብሔር ማዳን
ሰኔ 11 / 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የመልአከ ኃይል መምህር ኃይለመለኮት ግርማ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከናውንዋል!
#like_Comment_Share_Subscribe በማድረግ_አገልግሎቱን_ይደግፉ።
የራእይ ፍላጎት ባለው ልብ ውስጥ መመለስ እና በአምልኮት የሚገለጥ ተስፋ፤ ከእግዚአብሔር የመጠበቁ ጊዜ ሁኔታ በፊት ቀረ፡፡ አሁን ዔሊ ኡኡ.. አለ፡፡ መጮሕ ጀመረ፡፡ ‹‹ሰው ሰውን ቢበድል እግዚአብሔር ይፈርድበታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ ማን ይለምናል? እነርሱ ግን እግዚአብሔር ሊገድላቸው ወድዷልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም፡፡
እናትና አባት ወደ እግዚአብሔር ያልጸለዩለት፣ ያልሰገዱለት፣ ያላመለኩለት ትውልድ አይሰማውም፡፡
ሂድና ተማር እየተባለ እስክርቢቶና ደብተር ተሰጠው እንጂ፤ መንፈሳዊ በረከት አልተሰጠውም፡፡ በጸሎትና በመንፈሳዊ በረከት አልተባረከም፡፡ የተባረክንበትንም መንፈሳዊ የልጅነት ክብርና ጸጋችንን ወደ ተንኮልና ክፋት መንገድ ለውጠን፤ መንፈስ ቅዱስ በገባበት እግር ዲያብሎስ ውስጣችን ገብቶ አርክሶታል፡፡ አባት ያልተጸለየለት፤ ያልተመሰገነለትና ራእይ ያልታየለት ትውልድ፤ መጨረሻው እንደዚህ ነው፡፡
ሽማግሌው ዔሊ፤ ‹‹ሽማግሌ አይገኝ›› የሚለውን የእርግማን ቃል ሰማ፡፡ የተከበሩ አባቶች የሌሉት፣ አባቶቹን የሚሰድብና የሚያወግዝ፣ የሚቃወምና የሚተች፣ ትውልድ ተፈጠረ፡፡
በዔሊ ዘመን የነበረው ድፍረት፤ በእኛም ዘመን አለ፡፡ አሁን ሽማግሌ ጠፍቷል፡፡ የሚያስታርቅና የሚመክር የለም፡፡ ሽማግሌው፤ ኃይል፤ ጉልበት፤ ሞገስ፣ ክብር የለውም፡፡ እንደውም አንዳንድ ሽማግሌዎች የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ስንመለከት፤ ከትናንሾቹ ልጆች የሚበልጥ፣ የሚያስገርምና የሚያሳፍር ሆኗል፡፡
መዝሙረ ዳዊት. 4÷6
‹‹ ብዙሃን እለ ይቤሉ መኑ ያርእያነ ሠናይቶ፤ ተዐውቀ በላዕሌነ ብርሃነ ገጽከ እግዚኦ፡፡ »
‹‹በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው፡፡ አቤቱ የፊትህ ብርሃን በላያችን ታወቀ፡፡››