ያለ የውጪ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) እቃ ከውጪ እንዴት ማስገባት ይቻላል? የሚጠየቀው መስፈርት .....

  Рет қаралды 4,448

The Ethiopian Economist View

The Ethiopian Economist View

Күн бұрын

ዳያስፖራዎች ባላቸው የውጪ ምንዛሬ ከሀገር ውሰጥ የንግድ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ ሳይጠይቁ ካሉበት ቦታ ሆነው እንዴት በፍራንኮ ቫሉታ ዘዴ ወደ ኢትዮጲያ እቃ በማስገባት ለራሳቸው መጠቀም ወይም መነገድ ይችላሉ?
በተለያየ አጋጣሚ የውጪ ምንዛሬ ያከማቹ ሰዎች ከንግድ ባንኮች የውጪ ምንዛሬ ሳይጠይቁ እንዴት በፍራንኮ ቫሉታ ዘዴ ወደ ኢትዮጲያ እቃ በማስገባት ለራሳቸው መጠቀም ወይም መነገድ ይችላሉ?
በፍራንኮ ቫሉታ እቃ ከውጪ ለማስገባት የሚጠየቀው መስፈርት ምንድን ነው ?የውጪ ንግድ (Import) ላይ ለመሳተፍ ምን አይነት መስፈርት ማሟላት ይገባል?
በዚህ ቪዲዮ መልስ ለመስጠት እንሞክራለን…
Email: Wase.belay12@gmail.com
Facebook፦ / economistwasyhun
Telegram: t.me/WaseAlpha

Пікірлер: 42
@ephremhailu4744
@ephremhailu4744 3 күн бұрын
Great 👍 thank you for share wonderful bro
@getamesaykassaye161
@getamesaykassaye161 3 күн бұрын
እስቲ በደንብ እንድታብራራልኝ የምፈልገው ኢንቨስትመንት ፈቃድ እንደ ኢንፓርት እና ኤክስፖርት ፈቃድ ሆኖ አያገለግልም ወይ አምራቾች ንግድ ፈቃድ ከማውጣታቸው በፊት ማሽነሪ እንዴት ያስገባሉ????
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የንግድ ፍቅድ ሲወጣ የንግድ ዘርፍ መለየት አለበት! የንግድ ዘርፉ አስመጪነት ከሆን ምን ማስመጣት! ላኪነት ከሆነ ምን መላክ የሚለውን መግለጽ አለበት! የኢንቨስትመንት ፍቃዱ ወይም የንግድ ፍቃዱ የሚሰማራበት ዘርፍ መግለፅ አለበት! ከውጪ ለሚገቡ ቁሳቁሶች የውጪ ምንዛሬ የክፍያ አማራጮቻቸውን ገልፀው በራሳቸው አልያም በአስመጪዎች በኩል ማስገባት ይችላሉ!
@shemsedin9495
@shemsedin9495 2 күн бұрын
Thank you for the information
@MEU916
@MEU916 3 күн бұрын
Best update wasu
@getamesaykassaye161
@getamesaykassaye161 3 күн бұрын
ማሽነሪ ወይም የአኢንቨስትመንት የካፒታል ፣ የግንባታ፣ የሙከራ ጥሬ ዕቃ እንዴት ከንግድ ፈቃድ በፊት በፍራንኮ ቫሉታ ማስገባት ይቻላል ???
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የኢንቨስትመንት ፍቃድ ካወጣ በኋላ የኢንቨስትመንት ስራ ስለመጀመሩ ሲረጋገጥ።
@zerihungetachew8475
@zerihungetachew8475 2 күн бұрын
1.የ ፍራንኮ ቫሉታው የዶላሩ ምንጭ አይጠየቅም ? 2. እዛ ከከፍለ ነው በኋላ የአስመጪነት ፍቃድን ብቻ ነው የምንልክለት ? ለኤክስፖርተሩ ምንልካቸው ሠነዶች ምን ምን ናቸው
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
ፍራንኮ ቫሉታ (በተለያየ መልኩ የተገኘ የውጪ ምንዛሬን መጠቀም ማለት ነው! ከየት አመጣህ የፍራንኮ ቫሉታ አመክንዮ አይደለም! ሻጭ (ሌላ ሀገር ያለ ኤክስፖርተር) ክፍያ እንደምትፈፅሙለት ማረጋገጫ እና የጭነት ሁኔታ እና ክፍያ ነው የሚጠይቀው!
@zerihungetachew8475
@zerihungetachew8475 2 күн бұрын
በጣም አመሰግናለሁ ከይቅርታ ጋር የዶላር መጠኑስ ?
@zerihungetachew8475
@zerihungetachew8475 2 күн бұрын
የጭነት ሁኔታ ግልዕ አይደለም ወንድሜ
@zerihungetachew8475
@zerihungetachew8475 2 күн бұрын
ይቅርታ ለሻጭ ስላጭነት ሁኔታ ምን እንልክለታለን
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
ጭነት የሚከናወነው ጅቡቲ ድረስ በሻጭ ከሆነ (የጭነት ሁኔታ ስምምነት ለማለት ነው)።
@getamesaykassaye161
@getamesaykassaye161 3 күн бұрын
በኢንቨስትመንት አዋጅ እና ደንብ አንጻር አንድ ሰው እንዴት ከንግድ ስራ ከማውጣቱ በፊት ከላይ የጠቀስኳቸውን ዕቃዎች አእንዴት በፍራንኮ ቫሉታ መስገባት ይችላል ???
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣት ለኢንቨስትመንት ከመረጠው ቦታ ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት የተረከበ መሆኑን ከታች ባሉ ተቋማት ተረጋግጦ በመጨረሻ የገንዘብ ሚኒስትር ደብዳቤ በመያዝ በራሱ የውጪ ምንዛሬ ሊያስገባ ይችላል።
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የኢንቨስትመንት ፍቃድ በማውጣት ለኢንቨስትመንት ከመረጠው ቦታ ለኢንቨስትመንት የሚሆን መሬት የተረከበ መሆኑን ከታች ባሉ ተቋማት ተረጋግጦ በመጨረሻ የገንዘብ ሚኒስትር ደብዳቤ በመያዝ በራሱ የውጪ ምንዛሬ ሊያስገባ ይችላል።
@danielesayas3524
@danielesayas3524 3 күн бұрын
ወንድሜ በጣም እናመሰግናለን። በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው። ኣንድ ጥያቄ ኣለኝ ኣምራች የሆነ ሰው ለምያመርተው ነገር የሚጠቅመው ጥሬ እቃ ለማስገባት የማምረቻው ፍቃድ በቂ ነው? ወይስ ድጋሜ የኣስመጪ ፍቃድ ያስፈልገዋል?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
ለምሳሌ፦ ማሽነሪ ከሆነ በኢንቨስትመንት ፍቃዱ (ፋብሪካውን መገንባቱን አረጋግጦ) ገንዘብ ሚኒስትር ለጉምሩክ በሚፅፍለት ደብዳቤ ለፋብሪካው ማሽነሪ አስገብቶ ለራሱ መጠቀም ይችላል! የጉምሩክ ግዴታዎቹን እየተወጣ ሊያመጣ ይችላለሰ አስመጪ የመሆን ግዴታ የለበትም።
@shemsedin9495
@shemsedin9495 2 күн бұрын
Franco valuta ለማስመጣት commercial license ለማውጣት የሚፈልግ importer startaup capital block account ላይ ማሳየት ያለበት የገንዘብ መጠን ከ import value equivalent መሆን አለበት ወይስ በምን አግባብ ነው ማሥረጃውን የሚያቀርበው I mean as far as source of investment is franco valuta how or from where the importer should provide sart up capital which is blocked account for the process of registering commercial license?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
የንግድ ፍቃድ ካፒታል ከሚያስመጣው እቃ ወጪ ግዴታ እኩል መሆን የለበትም! ከካፒታሉ በላይ ተበድሮ ሊያስመጣ ይችላል ነገር ግን የገንዘቡን ምንጭ በማስረጃ (ለምሳሌ፦ ተበድሮ ከሆነ የውል እና ማስረጃ የብድር ውል ማስረጃ) ማረጋገጥ አለበት። ካፒታሌ 100ሺ የገዛሁት የአንድ ሚሊየን ብር ቢል የ900ሺ ምንጭ መረጋገጥ አለበት። በፍራንኮቫሉታ ለመሸመት የውጪ ምንዛሬ ከ deposits (በቤት ከሆነ ካከማቸበት) አውጥቶ ሊጠቀም ይችላል (ከንግድ ፍቃድ ካፒታል ጋር አይገናኝም!) የራሱን የውጪ ምንዛሬ ተጠቅሞ በፍራንኮ ቫሉታለ ገዝቶ ሲያስገባ ለቀረጥ የምን ያህል ሸምቶ እንዳመጣ invoice ነው ማቅረብ ያለበት።
@shemsedin9495
@shemsedin9495 2 күн бұрын
@theethiopianeconomistview Thank you so much very clear and informative
@MisrakBekele-g8i
@MisrakBekele-g8i 3 күн бұрын
Thanks so much
@getamesaykassaye161
@getamesaykassaye161 3 күн бұрын
የፍራንኮ ቫሉታ አዋጅ 88/1995 ከአዲሱ የውጭ ምንዛሬ የገንዘብ ፓሊሲ አንጻር እንዴት ታየዋለህ
@ዳድቱንጋ
@ዳድቱንጋ 3 күн бұрын
ሱፐር ማርኬት ያለዉ ሰዉ፣ለሱፐር ማርኬት የሚሆኑ ግብአቶችን ማስገባት አይችልሞይ? የግድ አስመጭ መሆን አለበቶይ?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የሚያመጣው ምርት ለሌሎች በሽያጭ የሚተላለፍ ከሆነ የአስመጪነት ፍቃድ ያስፈልገዋል!
@Tsegaye-f9z
@Tsegaye-f9z 3 күн бұрын
ወንድሜ ጥሩ እና ጠቃሚ ኢሹዎች ታነሳለ ግልፅ ያልሆነው ዕቃው ከተጫነ በዋላ ነው ምን ምን ድክመት ተሞልቶ ነው ተቀባይ የሚሆነው ? እና ደሞ ስልጣኑ የተሰጠው ጉምሩክ ባለስልጣን ነው?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
መስፈርቱ ከTIN ነበር ይጀምራል፤ ከዛ የንግድ ፍቃድ (የአስመጪነት)፤ የባንክ የክፍያ ሁኔታ መምረጥ (ፍራንኮ ቫሉታ)፤ የሻጭ ሁኔታን ማቅረብ (ዋጋ፤ የጥራት ማረጋገጫ፤ ወዘተ)፤ የጭነት ሁኔታ መወሰን (unimodal or multimodal)፤ የቀረጥ እና የጉምሩክ ክፍያዎች ማድረግ፤ ወዘተ ነው ሂደቱ። (እቃው ከተጫነ በኋላ የተለመዱ መደበኛ የጉምሩክ ሂደቶችን የፍቃድ፤ የግዥ፤ የጥራት፤ የቀረጥ ክፍያ፤ ወደ ሃገር ውስጥ የማጓጓዝ፤ ወዘተ መረጃዎችን ማቅረብ ያስፈልጋል)።
@Tsegaye-f9z
@Tsegaye-f9z 3 күн бұрын
የሻጭ ሁኔታ ስትል በፍራንኮፋልታ ቢመጣ ደረሰኝ
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
የሚገባው እቃ ቀረጥ የተጣለበት ከሆነ invoice ማስፈለጉ አይቀርም!
@FreeEthiopia14
@FreeEthiopia14 3 күн бұрын
How much money to show to get import and export license?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 3 күн бұрын
ቢዝነሱን ለማከናወን የሚረዳ ካፒታል (ገደብ የለውም) እቃው ሲገባ ጉምሩክ (ገቢዎች) ካፒታል እና የተሰራው ቢዝነስ ገንዘብ መጠንን ማስተያየቱ እና ማስረጃ መጠየቁ አይቀርም (1 ሚሊየን ብር ካፒታል አስመዝግቦ የ10 ሚሊየን እቃ ቢገዛ ስለ 9 ሚሊየኑ መረጃ ይጠየቃል (ብድር እንኳን ቢሆን በውል እና ማስረጃ የተረጋገጠ)።
@FreeEthiopia14
@FreeEthiopia14 2 күн бұрын
@@theethiopianeconomistview Thank you for your answer. I’ve heard a lot of gossip about needing to show a large sum of money to get an import and export license. What is the minimum amount required to obtain the license?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
No limit! It depends on ur capacity!
@getumersha5738
@getumersha5738 2 күн бұрын
If I have foreign currency why I wait a line
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
የራስህ የውጪ ምንዛሬ ካለህ ለ Lc ተራ አትጠብቅም!
@bilewbirhanu830
@bilewbirhanu830 2 күн бұрын
ለራሴ የምገለገልበት መኪና በፍራንኮ ቫሉታ ማምጣት እችላለሁ ወይ
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
የኤሌክትሪክ ከሆነ አዎ!
@binyamletarge2481
@binyamletarge2481 2 күн бұрын
@@theethiopianeconomistview ያለንግድ ፈቃድ ይቻላል?
@theethiopianeconomistview
@theethiopianeconomistview 2 күн бұрын
Sure! (አውቶሞቢል ከሆነ)!
Je peux le faire
00:13
Daniil le Russe
Рет қаралды 22 МЛН
Minecraft Creeper Family is back! #minecraft #funny #memes
00:26
Je peux le faire
00:13
Daniil le Russe
Рет қаралды 22 МЛН