Рет қаралды 118,744
#ሁላችንም_ልንማርበት_የሚገባ_ታላቅ_ትምህርት_ሼር_ሼር_ሼር
Subscribe, Share, Like, Comment እያደረጋችሁ ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!
#ሼር_ሼር_ሼር_ይደረግ!
እስቲ የተዋህዶ ልጆች ሁሉ ስለ ማርያም እያላችሁ ሼር አድርጉት።እመቤታችን በወርቅ ጫማዋ ለተጠማ ውሻ ውሃ አካፍላ በመስጠት መልካምነትን እንዳሳየችን እኛም ቃሉን የተጠሙ ብዙዎች አሉና ሼር በማድረግ እኛ የምንጠጣውን የህይወት ቃል እናካፍል።
አንዳንዶቻችን ቁጭ እንዳልን ማንም ሳይነካንና ሳያናግረን እንበረግጋለን፡፡ አንዳንዶቻችን ሥራ እየሠራንና ትምህርት እየተማርን ያለምክንያት እንጨነቃለን፡፡ አንዳንዶቻችን ወደ ውስጣችን አስበን ስለነገው የነፍሳችን መድረሻና ሁኔታ በጥልቀት ስንመረምር ፍርሃትና ጭንቀት ይውጠናል፡፡ በየዕለቱም የምንሰማቸው የተለያዩ አደጋዎችም ቤታችን ቁጭ ብለን እንድንፈራ ያደርጉናል፡፡ ምድር በከፍተኛ ሁኔታ የጭንቀትና የፍርሃት እስር ኃይል መግለጫ ከሆነችባቸው ጊዜያትና ዘመናት ውስጥ ይኸው የኛው የምንገኝበት ትውልድ ውስጥ ያለው ዘመን ነው፡፡ ስለዚህ ብዙ ነገር ነው የሚያስጨንቀን፡፡ ብዙ ነገር ነው የሚያስፈራን፡፡ የምንሰማቸውና የምንመለከታቸው ሰበር የዜና መግለጫዎች በአብዛኛው ፍርሃትንና ጭንቀትን የሚነዙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ አሁን አሁንማ እንደ አገር ዜጎችም በጋራ መፍራት የጀመርንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ጦርነት ያሰጋናል፡፡ በሽታ ያሰጋናል፡፡ ኑሮ ያሰጋናል፡፡ አለመተማመን ያሰጋናል፡፡ መበታተን ያሰጋናል፡፡ እንደዜጋ መተያየት አለመቻላችን ያሰጋናል፡፡ አንዱ ኢትዮጵያዊ ለሌላው ኢትዮጵያዊ አሰፈሪ፤ አንዱ ወገን ለሌላኛው ወገን አስጨናቂ የሆነበት ዘመን ወደ ኑሮአችን መጣ፡፡