ዘማሪት ፋንቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ | Kidus Giorgis Ethiopian Orthodox Mezmur 2018

  Рет қаралды 13,287

Kidanemihret

Kidanemihret

Күн бұрын

Пікірлер: 10
@Kidanemihret
@Kidanemihret 6 жыл бұрын
†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ልመናው ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ በዕውነት ለዘለዓለሙ ይደረግልንና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረገው ተአምር ይህ ነው። በዚያን ወራት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ አራት ዓመት በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በነገሡ በሃያ ስድስት ዓመት የምኒልክ የጦር አለቃ ገበየሁ ድል ከአደረጋቸው በኋላ እንደገና ምኒልክን ወግተው ኢትዮጵያን በቅኝ አገዛዝ ሊገዙ የሮም ሰዎች መጡ። ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ሀገሬ ኢትዮጵያን እወዳለሁ የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ ባስቸኳይ ይነሣ መስቀለ ሞቱንም ተሸክሞ ይከተለኝ እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር ወሰን አልፎ ሀገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት መጥቷልና ሲሉ ዓዋጅ አስነገሩ። ዳግመኛም በፈረሶቻቸው መጣብር ላይ በጦራቸው አንደበት ላይ በጋሻቸው እምብርት ላይ የመስቀል ምልክት እንዲያደርጉ ጭፍሮቹን አዘዟቸው መስቀል ጠላትን ድል አድራጊ እንደሆነ አስቀድሞ ያውቁ ነበርና። ከዚያም ተነሥተው ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር ዘመቱና ከትግራይ አውራጃዎች አንዷ የምትሆን አድዋ ከምትባል አገር ደረሱ። የሣህለ ማርያም ዳግማዊ ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦተ ጊዮርጊስን አስይዘው ከሊቀ ጳጳሱ ከአባ ማቴዎስ እንዲሁም ከቀሳውስቱና ከመነኮሳቱ ጭምር ከንጉሡ ጋር ወደ ጦርነቱ ተጓዙ። በዚህም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኮሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ። ቅዳሜ ሌሊት ለእሑድ አጥቢያ የካቲት ፳፪ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ የጦር ልብሳቸውን ለብሰው ከሠራዊታቸው ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄዱ። ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝተው ከሌሊቱ አሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመሩ። የንጉሡ የሣህለ ማርያም ምኒልክ ሚስት ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም ሌሊት በታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስና በእመቤታችን ሥዕል ፊት በጸሎትና በስግደት አድረው ሲነጋ ወደ ጦርነቱ ቦታ በመሔድ እጅግ በሚያስደንቅ አነጋገራቸው ኃይለ ቃል በጦርነቱ መካከል እየተገኙ ለንጉሡ ወታደሮች የሞራልና የብርታት ድጋፍ ይሰጡ ነበር። በዕውነትም ለተመለከታቸው ሁሉ እንደ ኃይለኛ ተጋዳይ አርበኛ ይመስሉ ነበር እንጂ የሴቶች የተፈጥሮ ባሕርይ በእርሳቸው ላይ አይታይባቸውም ነበር። የንጉሡም ወታደሮች የንግሥቲቱን የጀግንነት አነጋገር በሰሙ ጊዜ በእሳት ላይ እንደተጣደ የብረት ምጣድ ልባቸው ጋለ፤ ይልቁንም ላም እንዳየ አንበሳና የፍየል መንጋ እንዳየ ነብር እየተወረወሩ በጦርነት መካከል በመግባት የጠላትን ጦር በሰይፍ ይጨፈጭፉት ነበር። መጽሐፍ ሹመቱን ሽልማቱን ያየ አርበኛ ከጦርነት ከሰልፍ ወደ ኋላ አያፈገፍግም ብሎ ተናግሯልና። በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም ምኒልክ በጦርነቱ መካከል ሳሉ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኮሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምህላ ያደርሱ ነበር። ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል እቴጌ ጣይቱም በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አልተለዩም ነበር። የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር። በዚህም ዕለት ይኸውም የካቲት ፳፫ ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ በዚህም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ ማለትም የቀስተ ደመና ምልክት ታየ ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የሚመስል ጢስ ይወጣ ነበር። ከዚህም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ። ከዚህም የነጎድጓድ ድምፅ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ ለመዋጋትም አልቻሉም፤ ይልቁንም ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረስ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በዓየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲህ ማን ያድነናል አሉ፤ ምድር ጠበበቻቸው በዚህም ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው። የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታች ሄደች። ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም ምኒልክ በእግዚአብሔር ኃይልና በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት በጦርነት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጁ። ስለዚህም በዳዊት የምስጋና ቃል የድል ዘውድ ያቀዳጀኝን እግዚአብሔርን ባለ ዘመኔ አመሰግነዋለሁ፤ ለፈጣሪዬም እዘምራለሁ አለ ሕዝቡም ሁሉ በክብር ከፍ ከፍ ያለ እግዚአብሔርን በፍጹም ምስጋና እናመሰግነዋለን፤ የሮማውያንን ኃይል ቀጥቅጦ አጥፍቷልና ሠረገሎቻቸውንም ሠባብሯልና፤ ሠራዊቱንም ሁሉ በምድር ላይ በትኗልና እያሉ አመሰገኑ። በፈጣሪያቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል በጦርነቱ መካከል የረዳቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስንም በፍጹም ማድነቅ አደነቁት። የሮማም የጦር ሠራዊት በኢትዮጵያዊያን ፊት ተዋረዱ ዳግመኛም በኢትዮጵያ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ አላደረጉም። በምኒልክም ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያ ከጦርነት ለዓርባ ዓመት ያህል ዓረፈች። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክም ከዓድዋ ጦርነት ከተመለሱ በኋላ አዲስ አበባ ከተማ መካከል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠሩ። ስሟንም ገነተ ጽጌ ብለው ሰየሟት። ቅዱስ ጊዮርጊስ በጦርነት ቦታ ሁሉ ይረዳቸው ነበርና። ልመናው ክብሩ በእኛ ለዘለዓለሙ በዕውነት ይደርብን! ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን። (ምንጭ፦ ተአምረ ጊዮርጊስ) (የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት/St. George Church Sunday School)
@እመቤቴሆይፍቅርሺይብዛልኝ
@እመቤቴሆይፍቅርሺይብዛልኝ 6 жыл бұрын
Kidanemihret አሜን በእውነት ይሁልን ይደረግልን የልዳው እኮኮም የልዳው ፀሐይ የልዳው ስማእት አሁንም ለሃገራችን ስላምን ይስጥልን የእናት ሃገራችን ጥላቷን ፍጥኖ ያጥፋላትኝ ቃለ ህይወት ያስማልን ከልብ እናመስግናልን መልካም የተዋህዶ እንቁ ወጋኖቻችን ያብዛልን የቅዱሳን አምላክ በቤቱ ያፅናልን አሜን፫ በፆሎታችሁ አስቡኝ ወለተ ማርያም
@ቅድስትተዋህዶ-ቀ2የ
@ቅድስትተዋህዶ-ቀ2የ 6 жыл бұрын
Kidanemihret amen amen amen kalehiwet/ zimare melaekt yasemaln be ewnet betam ygermal hagerachin ahunm EGZIABHER ytebkln ye like semaetu bereketna eredet kegna ayleyen.
@elshaadayelshaaday2235
@elshaadayelshaaday2235 6 жыл бұрын
አሜን ፫ ቃለ ህይወትን ያስማልን !!!
@masaisamu1972
@masaisamu1972 4 жыл бұрын
ዝማሬ መእላእክን ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያዉርስልን ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ እንደ አባቶቻችን ጊዜ ለኛም ፈጥነሕ በፈረስሕ ድረስልን ሐገራችን ኢትዮጵያ ሳትጠፋ የኢትዮጵያ ቅዱስ ሰማእቱ ዘወትር ከሐይምሮየና ከመንፈሴ የማትወጣ በእለት በእለት ስምሕን ጠርቸ የምማጸንሕን ጸሎቴን አደራ ባለዉለታየ ጠባቂየ ተራዳየ አትለየኝ አሜን አሜን አሜን ።
@እመቤቴየነገርኩሽንአ-ጨ7ፈ
@እመቤቴየነገርኩሽንአ-ጨ7ፈ 4 жыл бұрын
አሜን የሰማአቱ ቅዱስ ጌወርጊስ በርክት ይድርሰን
@hanaabata9021
@hanaabata9021 4 жыл бұрын
አሜን ዝማሬ መላክ ያሰማልን
@tigisttruneh2082
@tigisttruneh2082 3 жыл бұрын
Amen !
@freweinigebremicheal9515
@freweinigebremicheal9515 4 жыл бұрын
Amen
🔴የቅዱስ ሩፋኤል መዝሙሮች  l kidus rufael  Mezmur l Ethiopia Orthodox
25:35
መልከ ጻዲቅ l MelkeSadik
Рет қаралды 5 М.
የእመቤቴ ማርያም መዝሙር | Ethiopian orthodox spiritual songs Mezmur
58:13
JISOO - ‘꽃(FLOWER)’ M/V
3:05
BLACKPINK
Рет қаралды 137 МЛН
ብፈረስካ ገስግስ 🛑 New Eritrean Orthodox Tewahdo Mezmur 2021  Bfereska Gesgs ዘማሪ ኣቤኔዘር ዳንኤል
8:11
ትምክሕተ ኩልነ ድንግል ማርያም TUBE TMKHTE KULNE
Рет қаралды 61 М.
Dej Tenahu Koyiche Kidane Mihiretini
6:49
MEZMUR50
Рет қаралды 17 МЛН
🔴  አዲስ ዝማሬ  "ፀሐይ ዘልዳ- ጊዮርጊስ"
7:59
ማኅቶት ቲዩብ - Mahtot Tube
Рет қаралды 75 М.
Ethiopia: Zemarit Fantu Welde Kalen Lemewelde
4:37
Zemarit Fantu Welde
Рет қаралды 607 М.