○ ዓለም ማረፊያ ናት የመጋቤ ስብሀት አለሙ አጋ መዝሙር ○ Alem marefya nat m/s alemu aga mezmur

  Рет қаралды 2,265

Ermias begena ኤርምያስ በገና

Ermias begena ኤርምያስ በገና

Күн бұрын

🔰የአቶ ሥዩም መንግስቱ አጭር የሕይወት ታሪክ
(፲፱፻፳፭-፳፻፱ ዓ.ም)
አቶ ሥዩም መንግስቱ ከአባታቸው ከሊቀጠበብት መንግስቱ አገኘሁና ከእናታቸው ከወ/ሮ ካሳዬ አለሙ በ፲፱፻፳፭ ዓ.ም በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ልዩ ስሙ የጎራ ደብር በሚባለው ቦታ ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ እዚያው የተወለዱበት አካባቢ በጉባኤ ቤቶች መንፈሳዊ ትምህርትን ማለትም በመጀመሪያ በየውስ ሚካኤል ደብር ከመምህር ባሳዝነው ምትኩ ጾመ ድጓንና ድጓን፤ በመቀጠልም ከመምህር ገብረሥላሴ ቅኔን ተምረው አጠናቀዋል፡፡
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ጉጉትና ፍላጎት በመንፈሳዊ ትምህርት ብቻ ሳይወሰኑ በዘመናዊ ትምህርትም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመግባት በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡
°°°
በሥራ ዓለምም ከ፲፱፻፵፯ ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ እስከተገለሉበት ፲፱፻፹፪ ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው በቁስቋም፤ በወሰንሰገድና በመድኃኔዓለም አጠቃላይ ፪ኛ ደረጃ ት/ቤት በአማርኛ ቋንቋና በግብረገብ መምህርነት እንዲሁም በመድኃኔዓለም አጠቃላይ ፪ኛ ደረጃ ት/ቤትና በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ጽ/ቤትና በትምህርት ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት በመጽሐፍት ዕቃ ግምጃ ቤትነት አገልግለዋል፡፡
°°°
ከላይ ከተጠቀሱት ት/ቤቶች በሥነ ምግባራቸውና በችሎታቸው ተመርጠው በቤተ መንግስት የአማርኛ ቋንቋና ግብረገብ ትምህርት በማስተማር እስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በቆዩባቸው የሥራ ዘመናትም በሥራቸው ታታሪ፤ ውጤታማ፤ በሥራ ባልደረቦቻቸውም ዘንድ ቅንና ተወዳጅ እንዲሁም ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡ በዚህም ሥራቸው የተለያዩ የምስጋና የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል፡፡
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ ከፍተኛ የዕደ ጥበብ ሙያ ችሎታ ያላቸው ሲሆኑ ከሚታወቁበትም አንዱ ተረስቶ የነበረውን ጥንታዊና ሐይማኖታዊ የሆነውን በገናን በመስራት ነበር፡፡ በመስራት ብቻም ሳይገደቡ በገናን በመደርደርና በማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ከመጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ ጋር በመሆን እንደ አሁኑ ጊዜ የበገና ትምህርት ቤት ከመከፈቱ በፊት ለብዙ ተማሪዎች የውጭ ሀገር ሰዎችም ጭምር ሳይቀር፤ በገናን በማስተዋወቅና በመስራት እንዳይረሳና እንዳይጠፋ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካደረጉት ሙያተኞች አንዱ ነበሩ፡፡
°°°
ከጥንት ጀምሮ በገናን ሲያደምጡ በድምጹ እጅግ ይማረኩ ስለነበረ እንደውም ሥራ ከምፈታ ለምን በገና አልሰራም በሚል ከመርካቶ አሮጌ በገናን በ፫፻ ብር ገዝተው አሠራሩን በማየት መሥራት እንደጀመሩ ይናገራሉ፡፡ ከዚያም መጋቤ ስብሐት አለሙ አጋን አፈላልገው በማግኘት የሠሩትን በገና ለመጋቤ ስብሐት በማሳየትና ከርሳቸው የማሻሻያ ምክሮችን በመቀበል እንዲሁም የራሳቸውን ጥረት በማከል በበገና ዙሪያ ያላቸውን የአደራደርም ሆነ የበገናን የአሰራር እውቀታቸውን እንዳዳበሩ ይናገራሉ፡፡
°°°
በተጨማሪም የሰሯቸውን በገናዎች ወደ መጋቤ ስብሐት እየወሰዱ እርሳቸው ለ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ለተለያዩ ስዎች ይሸጡላቸው እንደነበረም ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ ጊዜያትም ከፈረንሳይ፣ ከጣሊያንና ከሌሎች ሃገሮች ለመጡ ሰዎች በገናን በመሸጥ እና የሃገርን ቅርስና ባህል በማስተዋወቅ ዙሪያ በተዘጋጁ አውደ ርዕይዮች ላይም በገናን ይዘው በመገኝት፤ በገናን በዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ አስተዋጽ አበርክተዋል፡፡
°°°
ከዚህ በተጨማሪም በጀርመን ሀገር የታተመ የጥንታዊ አባቶች በገና በሚል ከሌሎች ሶስት ታዋቂ የበገና ደርዳሪዎች (ከእነ መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ፤ አቶ ታፈሰ ተስፋዬና አቶ አድማሱ ፍቅሬ) ጋር በመሆን የበገና መዝሙር ሲዲ አሳትመዋል፡፡
°°°
ከደረደሯቸውና ለምእመን ጆሮ ከደረሱት የበገና መዝሙራት መካከልም ‘’ግዱን ግዱን’’ ፣"ሰጊድ ሰላም" የሚለውና ‘’ሄደ መንኖ’’ የሚሉት መዝሙሮች ይጠቀሳሉ።
°°°
በዚህም ሥራቸው ከሲሳይ በገና ዜማ መሣሪያዎች ማሰልጠኛ ተቋም የምስጋና የምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡
°°°
የምስክር ወረቀቱም “የኢትዮጵያን የቅርስ የባህልና የታሪክ ውርስ ለሚጠብቁና ለምናከብራቸው ለአቶ ሥዩም መንግስቱ አገኘሁ፤ ሲሳይ በገና የዜማ መሣሪያዎች ተቋም የቃልኪዳን ታቦት ከሚታጀቡበት የዜማ መሣሪያዎች አንዱ የሆነውን በገና በመስራት፤ በመደርደር፤ በመጠበቅ፤ በማስተዋወቅና ለትውልድ በማስተላለፍ ላደረጉት ከፍተኛ የአስተዋፅኦ ይህን ሽልማት ተቋሙ በ፳፻፰ ዓ.ም በታላቅ አክብሮት አበርክተንልዎታል” የሚል ነው፡፡
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ የመንፈሳዊ ሕይወታቸውን በተመለከተ ገና ከህፃንነታቸው ጀምሮ የቤተክርስቲያን ልጅ በመሆናቸው ለሐይማኖታቸው ቀናኢና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ነበሩ፡፡ በማህበራዊ ኑራቸውም በሚኖሩበት አካባቢ በሰው ዘንድ የማይደርሱ፤ ጨዋ፣ተግባቢ፤ ትሑት፣ ለሰው አዛኝ፤ ደግ፤ የተጣሉትን የሚያስታርቁ ታላቅና የተከበሩ ሰው ነበሩ፡፡
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ በተክሊል ካገቡዋቸው ባለቤታቸው ከወ/ሮ ሐረገወይን ጌታሁን ሰባት ሴቶች ልጆችን ያፈሩ እንዲሁም የሰባት የልጅ ልጆችም አያት ነበሩ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ልጆችን ተንከባክበው በማስተማርና በማሳደግ ለቁም ነገር አብቅተዋል፡፡
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ በ፳፻፭ ዓ.ም ባጋጠማቸው የጤና ችግር ምክንያት የግራ ጣታቸው እንደ ልብ ባለ መንቀሳቀሱ የሚወዱትን በገና መደርደር ካቆሙ በ ፳፻፱ ዓ.ም ፬ኛ ዓመታቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
°°°
አቶ ሥዩም መንግስቱ በሆስፒታልና በቤት ሕክምናና እንክብካቤ ሲደረግላቸው ቆይተው በተወለዱ በ፹፬ ዓመታቸው ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ቀብራቸውም ሐምሌ ፳፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በብርሃናተ አለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን መካነ መቃብር ወዳጅ ዘመድ በተገኘበት ተፈፅሟል።
#begena #begena mezmur
#begena #በገና #በገና_መዝሙር
#ኤርምያስበገና #ዝክረበገና
#ኦርቶዶክስ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ለዘለዓለም_ፀንታ_ትኑር
#Begena #Ermiasbegena #Orthodoxtewahedo #Oriental
#church #photo
#photography #creative
#artistic #artwork
#bass #instrumental
#Begena #hilling
#meditation #strings
#harp #handmade
#kerar #kerarlesson

Пікірлер: 13
how to play begena in 10 minutes
10:18
Ermias begena ኤርምያስ በገና
Рет қаралды 3,9 М.
ዲ/ን ዘላለም ዘሪሁን ሙሉ የበገና አልበም
1:13:33
АЗАРТНИК 4 |СЕЗОН 3 Серия
30:50
Inter Production
Рет қаралды 949 М.
Секрет фокусника! #shorts
00:15
Роман Magic
Рет қаралды 116 МЛН
አዲሱ የመጋቢ ስብሃት አለሙ አጋ የበገና መዝሙር  መግቢያ በቆጠራና በድርብ
12:53
Akif Begena's tutorial / የበገና ስልጠና /@waknab
Рет қаралды 10 М.
ALEMU AGA ‎- Éthiopiques 11: The Harp Of King David
1:06:05
Melocactus
Рет қаралды 408 М.
መዝሙረ ዳዊት Mezmure Dawit - ቅዳሜ (መዝ 131-150)
29:57
ዜማ ተዋህዶ Zema Tewahdo
Рет қаралды 61 М.
ዓለም ማረፊያ ናት (መጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ)
4:30
የበገና መዝሙር ግጥሞች (begena mezmure lyrics)
Рет қаралды 359
АЗАРТНИК 4 |СЕЗОН 3 Серия
30:50
Inter Production
Рет қаралды 949 М.