Рет қаралды 6,220
የዳጣ ሽሮውን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አይነት እና መጠን
ዳጣውን ለማዘጋጀት
ግማሽ ኪሎ የሚጥሚጣ ቃሪያ
100 ግራም 1ጭ ሽንኩርት
50ግረም ዝንጅብል
1 የሾርባ ማንኪያ የድንብላል ዱቄት
የድንብላል ዱቄት ካላዘጋጃችሁ እርጥቡን የድንብላል ቅጠል መጠቀም ትችላላችሁ
2 የሾርባ ማንኪያ ጨው
ጨው ዳጣው በደንብ እንዲፈጭ ከሚያግዙት ግብዓቶች መካከል ዋናው ስለሆነ ባታሳንሱ ይመረጣል
ግማሽ ኩባያ ዘይት
እርጥብ የሮዝሜሪ ቅጠል 1
እርጥብ የጤናአዳም ቅጠል 1
እርጥብ የበሶ ብላ ቅጠል 1
አፈጫጭ
ዳጣውን ስትፈጩ ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች
የሚጥሚጣ ቃሪያውን ጭራ እና ቃሪያው ላይ የበሰበሰ እንዲሁም የተበላሸ ካለው ነጥሎ ማውጣት ወይም ሙሉ ለሙሉ አለመጠቀም
በደንብ ሽርክት አልል ካለ ጨው አንሶታል ማለት ነው
ድርቅ ካለባችሁ ውሃ ትንሽ ጠብ ጠብ እያደረጋችሁ መፍጨት
ግብዓቶቹ ለመፍጫችሁ እንዳይከብደው በቢላ በከፊል መክተፍ
ዳጣውን በከፍል እየፈጫችሁ መልሳችሁ እየከፈታችሁ ሳይፈጭ እላይ የቀረውን ወደታች ማውረድ እና ይህንን ሂደት መደጋገም
ዳጣው የበለጠ ድቅቅ እንዲልላችሁ ከፈለጋችሁ በሽንኩርት መፍጫ ከፈጫችሁ በዓላ ደግማችሁ በጭማቂ መፍጫ መፍጨት
ሽሮ ወጡን ለማዘጋጀት
3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
2 የሾርባ ማንኪያ ዳጣ
ይህ የዳጣ መጠን የሚወሰነው እንደምትፈልጉት የሽሮ ወጤ የማቃጠል ይዘት ነው የበለጠ ሞቅ እንዲል ከፈለጋችሁ የምትጨምሩትን የዳጣ መጠን ከፍ ማድረግ ይኖርባቹሃል
ግማሽ የቡና ማንኪያ ኮረሪማ
2 የሾርባ ማንኪያ ሽሮ
የምትጨምሩት ሽሮ እንደምትከልሱት የውሃ መጠን እና እንደምትፈልጉት የሽሮ ውፍረት አይነት ይወሰናል
500ሚ.ሊ የፈላ ውሃ
ሽሮ በደንብ እስኪወፍር ድረስ ማንተክተክ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የተነጠረ ለጋ ቂቤ
የበሶብላ ቅጠል
ማስታወሻ
ሽሮውን ስታዘጋጁ ዳጣው የራሱ ጨው ስላለው ያዘጋጃችሁት ሽሮ ላይ ጨው ቀምሳችሁ መጨመር ይኖርባቹሃል
ዳጣው በእሳት ሲበስል ጉሮሮን የመከርከር በኃሪ ስላለው ህፃናት በኩሽና ውስጥ ባይኖሩ ይመረጣል