Рет қаралды 16,032
እንቁላል ቁጭ ቁጩን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እና መጠን
ዛሬ የምናዘጋጀው ወጥ ለ5 ሰዎች የሚበቃ ነው
የግብዓት አይነት
1 ኪሎ ላም ተደርጎ የተፈጨ ቀይ ሽንኩርት
4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
የምታዘጋጁትን ቁሌት በብስል ቂቤ ማብሰል የማትፈልጉ ከሆነ የዘይቱን መጠን ከፍ ማድረግ ይኖርባቹሃል
2 የሾርባ ማንኪያ የተነጠረ ብስል ቂቤ
3 ሾርባ ማንኪያ በርበሬ
ሁላችንም ቤት የሚገኘው የበርበሬ አይነት እና ይዘት ሊለያይ ስለሚችል ሽንኩርቱ ላይ ትንሽ ትንሽ በርበሬ እየጨመራችሁ አማስሉ
1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
5 እንቁላል
1 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቂቤ
የፈላ ውሃ ወጡን ለመከለስ እና ቁሌቱን ላላ ለማድረግ
የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እና መጠን
1 የሾርባ ማንኪያ የማቁላያ ቅመም
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ኮረሪማ
የምትፈልጉትን ያህል ጨው
1 የሾርባ ማንኪያ ነጭ/ምጥን የሽሮ ዱቄት
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የመከለሻ ቅመም
ቀይ ቁሌት ላይ ቲማቲም የማናስገባበት ምክንያቶች
ወጥ ላይ ቲማቲም ሲገባ ወጡ ሲያድር አረፋ ያወጣል
ቲማቲም የገባበት ወጥ ትክክለኛ የሆነውን የሃበሻ የቁሌት ጠዓሙን ያሳጣዋል
ቲማቲም የገባበት ቁሌት ለቀናት ሳይበላሽ መቆየት አይችልም
ወጡ ላይ ቲማቲም ሲገባ የበርበሬው የማቃጠል ጠዓም ይጠፋና ስኳር ስኳር የማለት በኃሪን ያመጣል