Рет қаралды 1,039
◦ሊታይ የሚገባው ድንቅ የሠርግ ቅኔ
በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የዲያቆን #አብርሃም_ይመርና የወ/ሪት #እመቤት_ተሾመ ጋብቻ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ #በአባ_ተስፋዬ_እማምሰው ዋና መሪነት በምሥጢረ/ሥርዐተ ተክሊል ሚያዝያ ፳፪/፳፻፲፬ ዓ.ም ተከናወነ።
ዲያቆን አብርሃም ይመር ከልጅነት ዕድሜው ጀምሮ በድሬዳዋ አብያተ ክርስቲያናት በቅንነትና በታዛዥነት በዲቁና፣ በስብከተ ወንጌልና በመሰል መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እያገለገለ የመጣና በማገልገል ላይ ያለ፥ ብዙ የወደፊት ተስፋ የምንጥልበት በሳልና አስተዋይ የቤተ ክርስቲያናችን ፍሬ ነው።
በዓለማዊም ትምህርቱ በብቁ የጋዜጠኝነት ሙያ የድሬ ቲቪ ቀዳሚ ዜና አንባቢ በመሆን ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግል ቈይቷል። በአሁኑም ጊዜ የማስተርስ ዲግሪውን በማግኘት ሕዝብ የሚገለገልበትን ታላቅ ተቋም በመምራት ላይ ይገኛል።
➲እኔም ድንቅ በሆነው የሠርጉ ቀን በመድረኩ ተገኝቼ የተቀኘሁትን፥ የአእምሮ ጭማቂ የሆነውን ቅኔዬን እንዲህ ጽፌ ጋበዝኳችሁ፦
፩.፩. ግዕዝ ጉባዔ ቃና
▪️➤መኑ ተስፋየ እግዚአብሔር አኮኑ፥
▪️➤እንዘ እብል አነ በአምሳለ ዳዊት እዜኑ። (መዝ. ፴፰፡፯)
፩.፪. ግዕዝ ጉባዔ ቃና
◦ኀያል አብርሃም አመ ተመይጠ በኀይል፥
◦ዐሥራቶ አቅረበ ለመልከጼቅ ተክሊል። (ዘፍ. ፲፬፡፳)
፪.፩. ዕዝል ጉባዔ ቃና
◦ጻድቅ አብርሃም በዐቂቦቱ ዘእግዚአብሔር ቃለ፥
◦በአፈ መላእክት ወሰብእ ክልኤቱ ዐርከ ፈጣሪሁ ተብህለ።
፪.፪. ግዕዝ ጉባዔ ቃና
◦ጻድቅ አብርሃም ኀበ ነበበ ወኀበ አጽምዐ ቃላ፥
◦ለሣራ ተክሊል መርዓቱ እግዝእትየ ይቤላ። (ዘፍ. ፲፰፡፲፪)
፫.፩. ዘአምላኪየ
▪️➤ኢሳይያስ ለከ ዘይመስለከ መኑ፥
▪️➤ስምከ በቀለመ ወርቅ ተጽሕፈ አኮኑ፥
▪️➤ወመልአከ ኀይል ዘብርት እም ላዕሉ ይጼልለከ እፎኑ።
፫.፪. ዘአምላኪየ
◦ቅዱስ መጽሐፍ ከመ ቀዲሙ ነገረ፥
◦አብርሃም በሕገ ልቡና አምላኮ አእመረ፥ (ዘፍ. ፲፪፡፩)
◦ወብሕታዌ ሥጋ በኣለ/ጣዖተ ለሊሁ በእደ ዚኣሁ ሰበረ። (ኩፋ. )
፬. ሚ በዝኁ
◦ለአበ ኵሉ አብርሃም ይቤሎ ተክሊል እግዚአብሔር አብ፥
◦ በዘርእከ ለከ ይትባረኩ አሕዛብ፥ (ዘፍ. ፳፪፡፲፰)
◦ወእሁበከ ከነዓን እንተ እምኔሃ ይውኅዝ ዘኢይነጽፍ ሐሊብ። (ዘፍ. ፲፯፡፰፤ ዘፀ. ፴፫፡፪-፫)
፭. ዋይዜማ
◦በማእከለ አፍላግ ዘሦርያ እንዘ ሀለወ አብርሃም ማእከለ አቡሁ ወእሙ፥
◦ተክሊል እግዚአብሔር ጸውዖ አቅዲሙ፥ (ሐዋ. ፯፡፪-፫)
◦አብርሃም አብራም ኀበ ኀበ ይብል በስሙ፥ (ዘፍ.፲፪:፩)
◦ወመጋቤ ሥርዐት መቅድመ ድኅረ ፈጠሮሙ፥
◦መላእክት በሥርዐት ተሠይሙ/ቆሙ።
፮. ኀፂር ዋይዜማ
◦በከነዓን ወለተ ኪዳን አብርሃም ነበረ፥
◦ወለተ ኪዳን ከነዓን እስመ ኮነቶ ማኅደረ። (ዘፍ. ፲፯፡፰)
፯. ሥላሴ
◦አብርሃም ለአብርሃም ውስተ ርእሰ ደብር ከመ ይሡዖ ለምሥጢረ ተክሊል ይስሃቅ እመኒ እግዚአብሔር ጸውዖ፥
◦ለይስሃቅ ምሥጢረ ተክሊል ርእሰ ደብር ሦዖ፥
◦ወበዕፀ ሳቤቅ ቃል እሱሮ ለእመ ርእየ በግዖ፥
◦መሥዋዕተ አኰቴት አስተማሊዖ፥
◦ውስተ ርእሰ ደብር ሦዐ በአስተብቍዖ፥
◦ለባሕቲቱ ምሥዋዐ ሠሪዖ። (ዘፍ. ፳፪፡፩-፲፰)
፰. ዘይእዜ
◦ይቤሎ አብርሃም ለፈጣሪሁ አመ ኮሎዶጎሞር ቦአ ወአመ ጸብዐ ነገሥተ፥ (ዘፀ. ፲፬፡፲፯-፳)
◦በመዋዕልየ ትፌኑኑ ወሚመ ታርእየኒሃ ኪያሃ ዕለተ፥
◦ወኀበ አምላኩ ተክሊል አምኀ አምኃተ፥
◦ዓዲ ቍርባነ ወመሥዋዕታተ፥
◦ለዕበየ ክብሩ አቅረበ ወኢያትረፈ አሐተ፥
◦(ዓዲ ቍርባነ ወመሥዋዕታተ፥)
፱. ሣህልከ
◦ዘመሐልከ ቃለ ለአብርሃም፥ (ዘፀ. ፴፪፡፲፫)
◦ምሥጢረ ተክሊል አምላክ እንተ አልብከ ሕሰም፥
◦ኪዳነ አብርሃም ተዘከር ወዕቀብ መርዔተ ሕዝብከ እም ብእሲ ዘደም።
፲. መወድስ
◦ምሥጢረ ተክሊል እግዚእ እግዚአብሔር ይቤሎ ለአብራም አብርሃም ሰመይኩከ፥
◦ወዐቢየ ሕዝበ እሬስየከ፥
◦ወስመከ አሌዕል ወበምድር ከመ ኆፃ ባሕር አበዝኅ ዘርአከ፥
◦ወበበረከትየ እባርክ ኵሎ አሚረ እለ እም ልቡና ይባርኩከ፥
◦ ወበመርገምየ እረግም ዘይረግሙከ፥
◦አብርሃም አብርሃም ፃእ እም ሀገርከ፥
◦ዓዲ ተፈለጥ እም አዝማዲከ፥
◦ወነዐ ኀበ ምድር ዘአነ እሁበከ። (ዘፍ. ፲፪፡፩-፫)
፲፩. ኵልክሙ መወድስ
◦ምሥጢረ ተክሊል ጳውሎስ በውስተ መልእክቱ በሃይማኖቱ አብርሃም ከመ ጸድቀ ነገረነ፥ (ሮሜ. ፬፡፫)
◦ወምሥጢረ ቍርባን ያዕቆብ እንተ ስምዐ ጽድቅ ኮነነ፥
◦ይቤለነ በመልእክቱ (ያዕ. ፪፡፳፩) ጸድቀ በምግባረ ጽድቁ አብርሃም አቡነ፥
◦አኀዊነሂ ወአኀቲነ ኀበ እመ አምላክ ንትማኅፀን እንዘ ናቴሕት ርእሰነ፥
◦ውስተ ሕጽነ አብርሃም በገነት ከመ ታንብረነ/ታርፍቀነ፥
◦እግዝእትነ እግዝእትነ ነጽሪ መንገሌነ፥
◦እንዘ ንብል ወንበል አመ ለጸሎት ቆምነ፥
◦ሰላመ አብርሃም ፍቁርኪ/መርዓዊኪ የሀሉ ማእከሌነ።
◦ድንግል ስምዒ አስተብቍዖተነ።
◦ሰላመ አብርሃም ፍቁርኪ/መርዓዊኪ የሀሉ ማእከሌነ።
፲፪. ኀፂር ኵልክሙ መወድስ
◦ለአብርሃም አብ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ፥
◦ዕቀበነ ወተኖለወነ በሥጋ ወነፍስ።
ቴሌግራም
t.me/yaredzer
ፌስቡክ ድኅረ ገጽ
/ ያሬድ-ዘርአ-ቡሩክ-1035990911...
/ yared.zeraburuk
ቲክቶክ
vm.tiktok.com/...
ዩቲዩብ
/ @yared-zeraburuk
◦ ◦ ◦
"ክቡር አውስቦ በኵለሄ ፤ ወለምስካቡኒ አልቦቱ ስዕበት" ዕብ. ፲፫፡፬
"ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር ነው፤ ለመኝታውም ርኵሰት የለበትም።" ዕብ. 13:4
"Marriage [is] honourable in all, and the bed undefiled." (Hebrews 13:4)