ለልጆች ዱቤ መስጠት... ስራህ ያዉጣህ ነዉ!

  Рет қаралды 126,246

Donkey Tube

Donkey Tube

Күн бұрын

የዶንኪ ትዩብን አገልግሎት ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ
storm-visage-3...
የዛሬዉ ቪዲዮ ከወትሮ ይለያል ኮሜዲያን እሸቱ ከአዲስ አበባ 90 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘዉ አዳማ ከተማ ተገኝቱዋል።
ኮሜዲያን እሸቱ በልጅነቱ ዱቤ ከእናቱ ጋር ዱቤ ወደሚወስድበት ሱቅ ከ 20 አመት በኋላ በመሄድ ለ 5 ሰዎች ዱቤያቸውን ይከፍላል እንዲሁም ዱቤ የወሰዱትን እቃ በተጨማሪ ለእያንዳንዳቸው 1500 ብር የሚፈልጉትን ነገር እንዲወስድ ያረጋል ታዲያ እነዚህ ሰዎች ዱቤያቸው ሲከፈል ምን ይሰማቸው ይሁን?
In today’s unique video, we follow the beloved comedian Eshetu as he embarks on a heartfelt mission in Adama city, just 90 km from Addis Ababa. Reflecting on his childhood, Eshetu shares a touching story about visiting a store with his mother where they witnessed the struggles of Dube, who took out a loan.
Fast forward 20 years, and Eshetu has found a way to give back. In a remarkable act of kindness, he has paid off the loans of five individuals, each receiving 1500 birr to help them achieve their dreams. Join us as we explore Eshetu's inspiring journey, filled with laughter, compassion, and the impact of giving back to the community.
Don’t forget to like, subscribe, and hit the notification bell for more uplifting stories!

Пікірлер: 331
@user-ns4kc3wj6l
@user-ns4kc3wj6l 12 күн бұрын
በእውነት እሽዬ እንዴት እንደምመርቅህ አላውቅም ኦሮጊቷ እንዴት እንዳስለቀሱኝ አቦ እግዚአብሔር አምላክ የማያልቀውን ኃብት ከእድሜ ከጤና ጋር ይስጥህ ወንድሜ ምክንያቱም ለእንደዚህ አይነት ደካማ ሰዎች እንደ አንተ አይነት ልበ ቀና ሰው ያስፈልጋል፡፡
@danielnida8895
@danielnida8895 13 күн бұрын
ዱቤ የተከፈለላቸው እናት ምርቃት ለሁላችንም ይሁንልን
@ThomasAddisu
@ThomasAddisu 13 күн бұрын
Amen
@ዜድየአላህባህሪያ
@ዜድየአላህባህሪያ 13 күн бұрын
አሚን
@hannafantayedemisse6455
@hannafantayedemisse6455 12 күн бұрын
Amen❤
@NajatMohammad-jm1se
@NajatMohammad-jm1se 12 күн бұрын
Amiiiiiiiin
@minyiluteferi2681
@minyiluteferi2681 11 күн бұрын
አሜን
@verotube
@verotube 13 күн бұрын
እሼን የማደንቀው የነበረበትን የማይረሳ እሁን እገኘሁ ብሎ የማይኮራ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ነው በጣም አከብረዋለሁ ተባረክ ልጅህን ያሳድግልህ
@ErmiyasDebasu
@ErmiyasDebasu 13 күн бұрын
እኒህ ሙስሊም ወንድሞች በጣም ይለያሉኮ አሁን በዚህ ዓመት ላይ ነው ሸምሱ የተባለ የሰፈራችንን ሱቅ እንጀራ እንዲሰጠኝ እና ብር ስለሌለኝ መንጃ ፈቃዴን ያዝ አልኩት ኧረ ምን ነካህ ይኮሄ የምንጠቀምበት ነገር ነው ሲኖርህ ታመጣለህ ይዘህ ሂድ አለኝ እኔም አመስግኜ ወስጄ በነጋተው ብሩን ከፍልኩ እድሜ ይሰጣቸው በእውነት።
@SEADAMOHAMED-h5j
@SEADAMOHAMED-h5j 12 күн бұрын
መልካምነት ደግ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው በኔ የደረሰው ከባድ ነው ተቸገርን ብለው በጣም ብዙ ገንዘብ ክህደት ተፈፅሞብኛል እሄው ልቤ ተሰብሮ ሰዎችን ሁሉ እንዳላምን እንድፈራ አደረጉኝ የዋህነቴን እንደ ሞኝ መልካምነቴን እንደ መልካም አጋጣሚ አድርገው ተጠቀሙብኝ በቃ ሰው ክፉ ነው ብየ ማሰብ ጀምሪያለሁ 😢😢😢
@SEADAMOHAMED-h5j
@SEADAMOHAMED-h5j 12 күн бұрын
ለከዱኝ ክህደት እንኳ የጥፋተኝነት ስሜት አይሰማቸውም😢😢😢 ብቻ ከፈጣሪየጋ እፋረዳቸዋለሁ
@BelievedGod
@BelievedGod 13 күн бұрын
ባለ ውለታውን የማይረሳ ሰው ምንኛ የታደለ ነው ❤❤❤❤
@-oj4gq5xi8g
@-oj4gq5xi8g 13 күн бұрын
ትልቁ ባለውለታ ግን ተረስቷል
@ዜድየአላህባህሪያ
@ዜድየአላህባህሪያ 13 күн бұрын
በችግራችን ግዜ ያረጉልንን ሰዎች ባገኘን ግዜ ማስታወስ ትልቅ ነት ነው ተገቢም ነው የተከፈለላቸው እናት እንዴት እንዳስለቀሱኝ ማጣት ከባድ ነው እሼ አላሀ ጨምሮ ይስጥክ መልካምነት ለራስ ነው
@user-bf7wq8qt4h
@user-bf7wq8qt4h 13 күн бұрын
አሼ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነህ ተባረክ ለኔ እደሰጠኸኝ የመሰለኝ
@abher-
@abher- 12 күн бұрын
የተከፈለላቸው እናት ያስለቀሰው ማነው ምርቃታቸው ለሁላችን ይሁን 😢
@selam7006
@selam7006 11 күн бұрын
Amen enenem aselekesewegnal
@mahletmamuye9578
@mahletmamuye9578 11 күн бұрын
በተለይ ድርቆሽ በውሐ እያራስኩ ሲሉ😢😢
@ethiopiaworku3205
@ethiopiaworku3205 13 күн бұрын
እኔም ከልጅነት ጀምሮ ያሳደገን የሰፈራችን ሱቅ በድሩ እጅግ ደግ ሩህሩህ እንደአባት የምናየው ደግ ሰው ነው ከስደት ወደ አገር ስገባ ያደኩበት ሰፈር ሄጄ አገኘሁት በመጀመሪያ ቀን አልተዘጋጀሁም በቀጣይ ቀን ስጦታ ልሰጠው ብሔድ አጣሁት እኔም ወደምኖርበት ተመለስኩ ፈጣሪ ብሎ ዳግም ስሔድ ባገኘው ደስ ይለኛል ተባረክ እሼ 🙏 በችግራችን ጊዜ ለደረሱልን ሁሉ እግዚአብሔር ብድራቸውን ይክፈላቸው።
@shid1221
@shid1221 13 күн бұрын
እሼ የዕውነት ተባረክልኝ
@wubreview
@wubreview 12 күн бұрын
ሚገርም እይታ ወርቅ ልብህን ፈጣሪ አይንሳህ❤❤❤
@seedforafarmer4126
@seedforafarmer4126 12 күн бұрын
የተከፈለላቸው እናት በጣም አሰለቀሱኝ አይኔ እሰኪያብጥ ድረስ እሼ ትናቱን የማይረስ መውደቅ መነሳትን ማጣት ማግኘት ሁሉ በእኩል እንደ አመጣጡ የሚቀበል ድንቅ ሰው ነህ።
@manycell9813
@manycell9813 12 күн бұрын
አቤት እሚገርም ትውስታ ነው በየአካባቢችን ያሉ ብዙ ያዋሉ አሁንም ያሉ ባለሱቆች ባለውለታችን ናቸው ክብር ዛሬም ነገም ያለ ልዮነት እስካሁን ላሉ ሙስሊም ወንድሞቻችን ባለሱቆች❤
@fikeryashenfal4921
@fikeryashenfal4921 13 күн бұрын
በ1963 አመ/ም ተግባረዕድ እማር ነበር፣ የሄድኩት ከአርሲ ነበር፣ ተግባረዕድ በየወሩ ከክፍለ ሀገር ለሄዱ 15ብር የከፍለናል፣ ታዲያ፣ ወይዘሮ ጤናዬ የሚበሉ፣ሰንጋ ተራ ምግብ አዘጋጅ ነበሩ፣ ወር ሙሉ እየመዘገብን እንበላ ነበር፣ አንድ ትልቅ እነጀራ በሹሮ ወጥ 15ሳንቲም፣ ሥጋ ወጥ 25ሳንቲም፣ የዶሮ ወጥ 50ሳንቲም ነበር።ወሩ ሲመጣ እንዘጋና ዱቤችንን እንቀጥላለን። ዛሬ የዚህን ባለሱቅ ታሪክ ስሰማ ወይዘሮ ጤናዬን አስታወሰኝ፣ የሄ መተማመን ዛሬም መቀጠሉ በጣም ደስ የላል፣ እሸቱም ማስታወስህና ይሄንን በማድረግህ እናመሰግንሃለን!
@ShegerBusiness
@ShegerBusiness 12 күн бұрын
እሸቱ በናንተ ዘመን በጎ የሰሩ ሰዎች የልጅ ልጅ ነው! በጎነት ተወራራሽ ነው ብዙ ግዜ.... ❤
@user-we8je5jb4d
@user-we8je5jb4d 13 күн бұрын
እመቤቴን እሼ የተባረክ ፣ እናትህና ባለቤትህ የታደሉ ናቸው🎉
@onelove9191
@onelove9191 13 күн бұрын
የብዙዎቻችን ህልም ይህን ማድረግ ይህን ውለታ መመለስ በጣም ይገርማል እሼ አሪፍ ሀሳብ ነው።🙏🙏🙏🙏🙏👌👌👌👌👌ገራሚ ሀሳብ
@Withsabawyan
@Withsabawyan 11 күн бұрын
የሄ ዘመን የማያውቀው ንፁ ሰው ነህ ለንደናንተ የመሰሉ ሰዎች ብሎ ፈጣሪ ይታረቀን 🙏
@takelederesa
@takelederesa 12 күн бұрын
አሼ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነህ ተባረክ ለኔ እደሰጠኸኝ ባለ ውለታውን የማይረሳ ሰው የብዙዎቻችን ትዝታ ነው የሱቅ ዱቤ በችግራችን ጊዜ ለደረሱልን ሁሉ እግዚአብሔር ብድራቸውን ይክፈላቸው።
@ትበይንፀጋየ
@ትበይንፀጋየ 12 күн бұрын
እኔ የድቤ አምጭ ተብየ ስላክ ቆሜ ነበር የምውል የድቤ ወሰደች እዳይሉኝ ችግር በጣም ከባድ ነው ግን ለሁሉም ግዜ አለው 😢😢😢 እሽ ተባረከ ❤❤❤
@keyayene3325
@keyayene3325 13 күн бұрын
❤❤❤ትላንት የተደረገለትን የማይረሳ ሰዉ ትልቅ ሰዉ ነዉ❤❤እሼ
@dailyspor26
@dailyspor26 4 күн бұрын
እሸዋ የኔ ውድ አላህ ይሄን ምርጥ ልብህን ተንከባከበው ትልቅ ደረጃ ትደርሳለህ ጠቅላይ ሚነስትር እናደርጋሃለን
@besty6194
@besty6194 12 күн бұрын
እሸቱ እጅግ የሚያስደስት ስራ ነው የሰራኸው ይኛ እናት ምርቃት ይድረስህ ትውልድህ ይባረክ በጣም አመሰግንሃለሁ
@user-sv7cl3wf2h
@user-sv7cl3wf2h 13 күн бұрын
እሼ እኔም እደሱ ባለ ቁቅ ነበርኩኝ ብዙ ወዳጅና ደንበኛ ነበረኝ ሰው መርዳት በጣም ነው የሚያስደስተኝው ተባረክ ባለሱቁ
@MohamedAnwar-zz9uh
@MohamedAnwar-zz9uh 7 күн бұрын
ሴትየዋ ለብቻቸው ሌላ ፕሮግራም ያስፈልጋቸዋል እጅግ አክብረህ ነው ምወድህ ሰላምህ ብዝት ይበል ከመላው ቤተሰብህ 🙏🙏🙏
@ShegerBusiness
@ShegerBusiness 12 күн бұрын
እሼ ኮንቴንትህ 1ኛ! በቃ ትፈጥረዋለህ!... ሁሉም ዩቲዩበር አካባቢውን ብቻ በልቡ ቢያስተውል ተሰጥኦ ሲጨመርበት ... ምንም የፈረንጅ ስራ ላያስፈልገው ይችላል!❤
@fvv1680
@fvv1680 12 күн бұрын
🙏🙏🙏🙏እሼ አንተን ወለደች እናት በጤና በሠላም ሺ ዓመት አላህ ያኖርል አንተም አላህ ይጠብቅህ❤🤲
@Tsedalekabede
@Tsedalekabede 8 күн бұрын
እኔመ ሁሌም የማረሳተ በእድሜ ትንሽዬ ልጅ ነች ቀስራ ስሰራ ንፋሮታመጣልኘ ነበረ መቼም አድቀን አመሰግናታለሁ እዲሁም በዚ በኘደት አድ እህቴ ሲርበኘ በአጥር ምግብ ደብቃ ታቀብለኘ ነበረ 😭😭😭😭😭ዉለታዋን የት አግቼ ልክፈላተ ጌታ እኔን እደረዳቹ እሱ ይርዳቹ❤❤❤❤❤❤
@FatumaTube-dp1sl
@FatumaTube-dp1sl 13 күн бұрын
የኔ እናት ሁሌም ዱቤ ነው የምትሰጥ አንዳንድ ሰው ምንገድ ቀይሶ ሌላ ቦታ ይገዛሉ እሷ በዱቤ ወስዳ እሷም በዱቤ ትሸጣለች አይይይ እናቴ በስንቱ መልካምነትሽ ላንሳሽ የኔ መልካም አላህ እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥሽ ❤❤❤😢😢
@ShegerBusiness
@ShegerBusiness 12 күн бұрын
ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን ለደጋግ እናቶቻችን!❤
@FatumaTube-dp1sl
@FatumaTube-dp1sl 12 күн бұрын
@@ShegerBusiness አሚን ያረብ ወላህህ
@MdAlle-kz7vj
@MdAlle-kz7vj 13 күн бұрын
እሸ እዉነት ዘመንህ ሁሉ ይባረክ❤❤❤❤❤❤❤
@FantuKelecha
@FantuKelecha 13 күн бұрын
እንዴት መባረክ ነው ! እሼ እግዚአብሔር አብዝቶ ....አብዝቶ......አብዝቶ ይባርክህ 🙏
@zamzamamin5175
@zamzamamin5175 13 күн бұрын
እሼው በጣም የምወድህ ልጅ ህ ሂሊም ዱአ አረግልሃለሁ ተባረክ የወለድከው ይባረክ የናትህንም እድሜ አላህ ያርዝምልን ያሰብ❤❤❤❤
@wubreview
@wubreview 12 күн бұрын
ሰው ማለት ትላንትን የማይረሳ ነው❤ተባረክ እሼ
@tezeradesalegne1217
@tezeradesalegne1217 12 күн бұрын
እሺ አግዛብሔር ይስጥል ፣ እድሜ ጤና ይስጥህ ይሄ ለሁላችንም ትምህርት ነው
@user-we8je5jb4d
@user-we8je5jb4d 13 күн бұрын
ውይ እሼ የብዙዎቻችን ትዝታ ነው የሱቅ ዱቤ😅❤
@sofiabadri8350
@sofiabadri8350 12 күн бұрын
سبحان الله ይገርማል መልካም እነት ለራስነው
@azebkebede7422
@azebkebede7422 12 күн бұрын
እናኒዬ ነብስሽን በአፀደ ገነት ያኑርሽ ዱቤ እየሰጠሽ ቸግራችንን በአንቺ አልፈናል። ከኛ ሰፈር!!
@Mነኝየመዳምታክሲ
@Mነኝየመዳምታክሲ 13 күн бұрын
እሸ ተባረክ ጎበዝ ነህ በርታ❤
@user-ib2fu2wp1c
@user-ib2fu2wp1c 13 күн бұрын
ጠዋተ ሲወጡ ሰላምታ ካበዙ ማታ ዱቤ ለመጠየቅ ነዉ ይል ነበር አብዱልአዚዝ አህህ አላህ ይራህመዉ እሱም ደግ ነበር😢
@ShegerBusiness
@ShegerBusiness 12 күн бұрын
ደግነት ይከፍላል!
@mekelesalemayehu6279
@mekelesalemayehu6279 12 күн бұрын
😂 የራሴን አስታወሽኝ ለዛነው የሳኩት
@nuale-c9p
@nuale-c9p 11 күн бұрын
ልሳቅ 😂ወይስ ልዘን😢ነፍስ ይማር
@user-ib2fu2wp1c
@user-ib2fu2wp1c 11 күн бұрын
@@nuale-c9p ኩፉ አይንካሽ
@adaahchpatal5527
@adaahchpatal5527 13 күн бұрын
በእውነት እግዚአብሔር ይሰጠህ❤❤❤❤ ጀግና😊
@hlemaNgest
@hlemaNgest 10 күн бұрын
እሸቱ መድሀኒ አለም ጨምሮ ጨማምሮ ይስጥህ አተንፁህ ኢትዮጵያውይ ጀግና ነህ
@tizitatadesse8606
@tizitatadesse8606 10 күн бұрын
መልካምነትህን ተማሪዎች ሆነህን ስታግዘን ነው የማውቀው... ገና ነፍ ነገር እጠብቃለሁ እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏
@SamrawitGirma1
@SamrawitGirma1 13 күн бұрын
እሼ የኔ ደግ ተባረክ ወንድሜ❤
@rabyaa7059
@rabyaa7059 12 күн бұрын
መልካም ስው አይ ድህነት ድህነት ችግርን ርሃብን የሚውቀው የድርሰበት አስለቀሱኝ እግሪን ተሰብሪ ብለው ባለመክፍላቸው ሲለምኑት
@HayimiyouTube
@HayimiyouTube 13 күн бұрын
ዛሬ youtube ላይ ሲገባ ሲገባ የመጀመሪያ ነኝ 😂👍
@YenalemHabta
@YenalemHabta 13 күн бұрын
2017 የኛ አመት ይሁንልን ❤❤
@qweqwe444
@qweqwe444 12 күн бұрын
እግዚአብሔር ይስጠዉ መልካምነት መልሶይከፍላል !!!!!❤❤❤❤
@KonjitBerhanu-pm4ll
@KonjitBerhanu-pm4ll 13 күн бұрын
THank you Eshe,
@Science_Geez
@Science_Geez 13 күн бұрын
Surprising show🎉🎉🎉
@belayneshbelta7583
@belayneshbelta7583 12 күн бұрын
Thank u both of u❤❤❤❤
@EtholoveSeewt-cj9rj
@EtholoveSeewt-cj9rj 13 күн бұрын
❤❤❤የእማማ ምረቃት እንባዬ ተራሴን ረሰረሰ እፍፍፍፍ ማጣት ክፉ ነዉ ልጄ ድምጿ ጠፍቶ ነዉ እግሬን ተሰብሬ ሶስት ቀን ድርቆስ በውሃ ነዉ የምበላው ቶፊቅዬ አንተን አላስችግረም ብዬ ሲሉ እፍፍፍፍ ልቤን ነካኝ እኔም ምስኪን አባት አለኝ ያውም ለ15 አመት በስደት በናፈቆት እየተንከራተትኩ
@mekelesalemayehu6279
@mekelesalemayehu6279 12 күн бұрын
ዱቤ የተከፈለላቸውን እናት ስልካቸውን ባገኘሁ
@bezamengesha22
@bezamengesha22 13 күн бұрын
ውለታን አለመርሳት ህ ምርጥ ሰው ነህ እሸ❤❤ትንሺ ሲያገኙ ለሰላምታኳ ይኮራሉ እኮ ተባረክ❤❤
@abebechwedajo328
@abebechwedajo328 13 күн бұрын
የኔ ጀግና ተባረክ። ትላንትን የማይረሳ ነገን ያሳምራል
@EnateArsema
@EnateArsema 13 күн бұрын
እሼ አንደኛ ሙሉ ሁኔልን አንተ ልዩ ልጅ ተባረክ
@FelekRahel
@FelekRahel 12 күн бұрын
ተባረክ እሸቱ እድሜ ከጤና ይስጥህ🎉🎉🎉🎉🎉🎉❤
@diasporabilu7563
@diasporabilu7563 13 күн бұрын
Thanks so much brother
@AbbaHenokMamo
@AbbaHenokMamo 12 күн бұрын
የዛሬ ማንነት በመልካም ለመኖር ትላትን ማስታወስ ትልቅነት ነው።ሁለታችሁም በጣም ታኮራላችሁ።
@adee4662
@adee4662 12 күн бұрын
አሜን እማማ ለኛህም ይድረሰን❤❤❤❤❤❤❤እሼ ተባረክ
@mikiyasnigatu3263
@mikiyasnigatu3263 13 күн бұрын
እድሜና ጤና ይስክ እሽዬ
@user-kf7ot9ow6h
@user-kf7ot9ow6h 11 күн бұрын
ካለህበት ደረጃ የተሻለ ነገር ላይ አሏህ ያድርስህ በዚህ በትንሽ ሱቁ እያበደረ ሱብሃነሏህ አሏህ ይስጥህ❤❤❤
@BrightVision-t5p
@BrightVision-t5p 13 күн бұрын
እግዚአብሔር አምላክ ይመስገን
@yohannisgetu9062
@yohannisgetu9062 12 күн бұрын
እግዚአብሔር የበለጠ ክብርና ሞገስ ይስጥህ
@zamzamamin5175
@zamzamamin5175 13 күн бұрын
አገሬ ሰመጣ ላገኝህ እፈልጋለሁ ሁሌም እከታተልሃሁ አላህ ይጨምርልህ
@MuhammedEmirates-j5t
@MuhammedEmirates-j5t 12 күн бұрын
ይጨምርልህ
@haymanotmoges2386
@haymanotmoges2386 12 күн бұрын
.በኦዉነት ካወኩት ጀሞሮ እሸቱ መለሠ በጣም የሚገርመኝ ና የማደንቀዉ ሠዉ ነዉ እግዚያብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ
@etalemkasaa5586
@etalemkasaa5586 13 күн бұрын
እሼ መልካም ሰው እግዝአብሔር የልብህን መሻት ይሙላልህ
@bayushtefera3958
@bayushtefera3958 13 күн бұрын
እሺዬ እግዚአብሔር ይባርክህ ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@emebetbelay3772
@emebetbelay3772 12 күн бұрын
ሬድዋንዬ ስላየሁህ ደስ ብሎኛል የዱቤ ታሪክ ባይኖረኝም ጥሩ ሰው ነበርክ እሸቱ አሪፍ ስራ ነው የድሮን ማስታስህ
@user-dg1uh6kf1k
@user-dg1uh6kf1k 13 күн бұрын
እሼ ጀግና ፀጋውን ያብዛልህ በርታ
@tsegayemergia7874
@tsegayemergia7874 12 күн бұрын
በጣም ደስ የሚል ባለ ሱቅ
@shanyfahiye919
@shanyfahiye919 13 күн бұрын
YOU ARE VERY KIND PERSON MAY ALLAH REWARD YOU.
@hilinawondimu4373
@hilinawondimu4373 12 күн бұрын
እሼ ዳንኤል እባላለሁ ሐረር አራተኛ የሚባል አካባባቢ መደብር አበረኝ ለኔ ዱቤ ውስጤ ነበር የሚገርምህ ፍፁም ፍሰሐ በደንብ ያቀኛል።
@dudrudggj5190
@dudrudggj5190 13 күн бұрын
እንዴት ደስ እንደሚል❤❤
@kidankidankidankidan7031
@kidankidankidankidan7031 13 күн бұрын
የኔ እናት እንደው ምን ልሁንልዎ ድርቆሽ በውሃ ነክሬ አሉ አሉ ወይይ😢አረ በክርስትና ስም እና ቤቢ ሻወር እያላቹ ብር የምታባክኑ ምናለ እንደዚህ የተቸገሩትን ብትረዱልን😢እሼ እግዚአብሔር ጨምሮ ይስጥህ የነበረበትን የማይረሳ ሰው የተባረከ ነው።
@user-bc9bx3rr4s
@user-bc9bx3rr4s 12 күн бұрын
እባዬ ነው የመጣው የምር እፍፍፍፍ ማጣት አይኑ ይጥፉ
@manalo1965
@manalo1965 12 күн бұрын
እኔስ እሽየን ሳየው ዝብየ ማለቅሰው ነገርስ ❤❤❤❤❤❤ ዘመንህን ይባርከው እሸየ እግዚአብሔር እንዳንተ ያለ ጀግና ነው ለኢትዮጵያ ሚያስፈልጋት
@MichaelRistom
@MichaelRistom 13 күн бұрын
WA WA WA BRAVO ESHETU GOD BLESS YOU AND PLEASE CONTINUE
@nebiyathaile2718
@nebiyathaile2718 13 күн бұрын
መልካም ሠው ነው ተባረክ
@sindushenkut6693
@sindushenkut6693 12 күн бұрын
እጅግ በጣም ደስ የሚል ዌብሳይት ነው ኮመዲያን እሸቱ እግዚአብሔር ይቢርክህ
@userenter2635
@userenter2635 12 күн бұрын
ኧረ የሼ ወዳጆች የትናችሁ ላይክ ኮመንት አርጉ🙏እሼ ምርጥ ሰው ❤❤❤እዳተአይነት ባለሱቅ ያብዛልን🙏❤❤❤
@birtukandesalegn2591
@birtukandesalegn2591 12 күн бұрын
wooooow that is really great what you have done and God gives you more back it is wonderful Action woooow
@workneshdese2644
@workneshdese2644 10 күн бұрын
ወይይይይ እሼሼሼ❤ አደራህን ይሄን ቀና ልብህን እግዚአብሔር አይቀይርብህ መድሐኒአለም ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ❤
@Rediet-u7y
@Rediet-u7y 13 күн бұрын
First from ናዙ
@AB-TUBE1113
@AB-TUBE1113 8 күн бұрын
Wow it's amazing 🎉
@abebechtariku6554
@abebechtariku6554 12 күн бұрын
እግዚአብሔር ይህ ጨምርልህ💚💛❤😍
@endegenafiseha1750
@endegenafiseha1750 11 күн бұрын
እሼ ሬድዋን በጣም መልካም ሰው ነው ምስጋና ይገባዋል❤❤❤❤❤
@Abush-ng7iq
@Abush-ng7iq 12 күн бұрын
እሼዬ በእዉነት እግዛብሄር አብዝቶ ይስጥህ የእዚያችን እናት ስሰማአ እምባአ የዉ የተናነቀኝ ኢትዮጵያን እግዛአብሄር ይመልከታት ስንቱዉ ይሆን እንደሷአ በችግር የሚሰቃየዉ 😢
@woinewoine5413
@woinewoine5413 10 күн бұрын
እግዚአብሔር ይባርክ ❤👏
@mesfinbirhane2445
@mesfinbirhane2445 12 күн бұрын
እግዚሀቤር ይመሰገን የድንግል ልጅ እሺ እግዚሀቤር አብዝቶ ይሰጥህ ወንድሜ🙏🙏🙏🙏
@lidiyaworku9290
@lidiyaworku9290 12 күн бұрын
Redwan yeseferachin tihut sew new♥️ Eshe Egziabher chemiro yistih 🙏
@HayatGuragewa
@HayatGuragewa 12 күн бұрын
እኔም ተለውጭ ለማመስገን ያብቃኝ ያገሬ ልጆች ድዋ አርጉልኝ
@BelaynewBelaynewA
@BelaynewBelaynewA 12 күн бұрын
እሽ እግዚአብሔር ይባርክህ!!!
@tigistassefa6596
@tigistassefa6596 11 күн бұрын
ጌታ ኢየሱስ ይባርክህ ይብዛልህ
@AsQw-fu4uq
@AsQw-fu4uq 13 күн бұрын
እፍፍፍአይእሸ ከዝህ መጥፎዘመን ይጠብቅህ
@Sara-ne3cl
@Sara-ne3cl 11 күн бұрын
እሽ ድቤ የተከፈለላቸዉን እናት ኤደህ ብታያቸዉ ደስ ይል ነበር ድርቆሽ በዉሀ እየበላሁ ሴሉ ዉስጤን ነዉ የነካዉ
@yeshibeyene3530
@yeshibeyene3530 13 күн бұрын
ላንተም ለባለሱቁም እግዚያብሄር እድሜና ጤና ይስጣችሁ
@beedan865-zs3yw
@beedan865-zs3yw 13 күн бұрын
እግዚአብሔር ይባርክህ እሼ❤❤❤😍😍😍
@GT-xi8bv
@GT-xi8bv 12 күн бұрын
እንዴት ደስ ይላል
@AbBisre
@AbBisre 13 күн бұрын
You are unique eshe🎉🎉🎉
@user-je3ns8op2i
@user-je3ns8op2i 13 күн бұрын
ጀግና ሠው በርታ
@emebetsefara5639
@emebetsefara5639 10 күн бұрын
አግዛቡሂር እቡዚቶ ይባርከህ😊
@umukeramyoutube8543
@umukeramyoutube8543 12 күн бұрын
ማሻ አሏህ በጣም ደስ ይላል ውነት እሺ. ተባርክ. ሀገራችንን ስላን ያደርግልን
@freweynitesfay472
@freweynitesfay472 11 күн бұрын
May God bless Ehetu most people forget where they came from be blessed always
大家都拉出了什么#小丑 #shorts
00:35
好人小丑
Рет қаралды 91 МЛН
Фейковый воришка 😂
00:51
КАРЕНА МАКАРЕНА
Рет қаралды 7 МЛН
ማን ነው በረዶ ውስጥ የሚገባው? @ComedianEshetuOFFICIAL
14:50
Comedian Eshetu- OFFICIAL
Рет қаралды 352 М.