Рет қаралды 4,795
የፍላፍል በርገር
የፍላፍል በርገሩን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እና መጠን
250ግራም ሽንብራ ዱቤ
ሽንብራ ዱቤውን በደንብ ትለቅሙት እና ሰፋ ያለ ሰሃን ላይ ገልብጣችሁ ውሃ ዘለግ አድርጋችሁ ጨምራችሁ ቢያንስ ለ6 ሰዓት ማቆየት
5 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
1 ራስ ተለቅ ያለ ቀይ ሽንኩርት
ትንሽ የሾርባ ቅጠል
ዳቦ
ዳቦውን ስልሱ ላዩ ላይ እንዲቀርላችሁ አስቀድማችሁ መጥበሻ ላይ ጥበሱት
የሰላጣ ቅጠል
በደንብ በአቸቶ እና ውሃ የታጠበ
1 ቲማቲም
1 ሽንኩርት
የማጣፈጫ ቅመሞች
1 የቡና ማንኪያ እርድ
1 የቡና ማንኪያ ከሙን
1 የቡና ማንኪያ የድንብላል ዱቄት
የድንብላል ዱቄት ከሌላችሁ የድንብላል ቅጠሉን መጠቀም ትችላላችሁ
1 የቡና ማንኪያ ሚጥሚጣ
አበሳሰል
ዲፕ ፍራየር የምትጠቀሙ ከሆነ
በ180 ዲግሪ በደንብ ታግሉ እና ቢያንስ ለ 6 ደቂቃ መጥበስ
መጥበሻ የምትጠቀሙ ከሆነ
በከፍተኛ ሙቀት ዘይት ለ5 ደቂቃ ታግሉና ፍላፍሉን ጨምራችሁ ቀለሙን እስኪቀይር ድረስ መትበስ
ማባያ ስልስ
ኬች አፕ
ተሂኒ ስልስ
ማባያ
የድንች ጥብስ
የስኳር ድንች ጥብስ