ህጻናት 6 ወር ሲሞላቸው ምን እና እንዴት እናስጀምራቸው ?

  Рет қаралды 34,013

Habesha Health Clinic

Habesha Health Clinic

9 ай бұрын

ህጻናትን 6 ወር ሲሞላቸው ምን አይነት ተጨማሪ ምግብ እናስጀምራቸው ? እና እንዴትስ እናስጀምራቸው ? የትኞቹ ምግቦች የተሻሉ ናቸው ? ከማስጀመራችን በፊት ማወቅ ያሉብን ነገሮች ምንድን ናቸው? የምግብ አለርጂ ሲከሰት እንዴት መለየት እንችላለን እናም በምን መንገድስ እናውቃለን።
ልጅዎ ጠጣር ለመጀመር ዝግጁ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች ምን ምን ናቸው።
1. ልጅዎ በድጋፍ መቀመጥ ይችላል.
2. ምግብ በምንሰጣቸው ጊዜ ጭንቅላታቸውን ቀጥ አድርገው መያዝ ይችላሉ
3. እናም እጃቸውን እና ጣቶቻቸውን ያውቃሉና በምመገባቸው ግዜ እነሱም ይሳተፋሉ።
4. ለዝግጁነት ሌላ ቁልፍ ምልክት ልጅዎ የምግብ ፍላጎት እንዳለው ማሳየቱ ነው። ስለዚህ ምግብ በሚመገቡበት ጊዜ ልጅዎ በትኩረት ይከታተላል። ስለዚህ እርሶ ምግቡን ከሳህኑ ወደ አፍዎ ሲወስዱ ይመለከቶታል። ያ ማለት ስጡን እያሉ ነው እና ምግብ ወደ እነርሱ ስናቀርብ አፋቸውን ይከፍታሉ።
እና የመጨረሻው የዝግጁነት ምልክት፣ አጋዥ፣ ነገር ግን የግድ መሆን የለበትም፣ ልጅዎ የምላስ መገፋት ስሜት መቀነሱ ነው reduced tongue thrust reflex የምንለው። ያ ማለት ምግብ አፋቸው ውስጥ እንዳደረግን ምላሳቸው ምግቡን ወደ ውጭ አይገፋም። ይህ ደግሞ ምግቡ በአፍ ውስጥ እንዲቆይ እና ተመልሶ እንዲውጡ ይረዳቸዋል።
ታድያ ለተጨማሪ ምግብ ዝግጁነታቸውን ካረጋገጥን ከማስጀመራችን በፊት ማወቅ ያለብን አስፈላጊ ነገሮች
1 ልጅዎን ተጨማሪ ምግቦችን ስታስጀምሩ አንድ አይነት አዲስ ምግብ ብቻ ይስጡት።ይህንንም ሌላ ሳንጨምር ለተወሰኑ ቀናት መስጠት አለብን።
2 የምግብ አሌርጂ ምልክቶችን ማወቅ አለብን። ምልክቶቹ የቆዳ ሽፍታ፣ የፊት እብጠት፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ማሳል፣ የመተንፈስ ችግር እና ሲሪታ ማሰማት፣ ድክመት ወይም የገረጣ ቆዳ ያካትታሉ።
3 ስናስጀምር ቤት ያፈራውን እና የምናውቀውን በቤት ውስጥ በቀላሉ ያዘጋጀነውን የምግብ አይነት መጀመር ። በተቻለ መጠን የህፃናት ምግብ በቤት ውስጥ ተመጥኖ የተዘጋጀ ቢሆን ይመረጣል።
4. የተፍጩ ምግቦችን ስናዘጋጅ ለምሳሌ ከ አጃ ወይም ከሩዝ ዱቄት ስናዘጋጅ የጡት ወተት፣ የ ፎርሙላ ወተት ወይም ፈልቶ የቀዘቀዘን ውሃ መጠቀም ።
5. ተጨማሪ ምግብ ስናስጀምራቸው ምግቡ ላይ ጨው ወይም ስኳር አለመጨመር። ያስጀመርን ሰዎች ቀስ በቀስ መቀነስ።
6. መጀመሪያ ላይ በአንድ የሻይ ማንኪያ ምግብ ወይም በትንሽ በጣት መጠን ልክ የተዘጋጁ ምግብ ማስጀመር። እና ቀስ በቀስ ለልጅዎ የሚሰጡትን የምግብ ፍላጎት እንደ ፍላጎታቸው መጠኑን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መስጠት።
7. 9 ወር እስኪሞላቸው ድረስ የጡት ወይም የፎርሙላ ወተት ከወሰዱ ቡኋላ ነው ተጨማሪ ምግብ መውሰድ ያለባቸው። ወይም በተለየ ሰዓት። ነገር ግን ከ 9 ወር ቡኋላ ግን በተቃራኒ ነው።
8 ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን መቀነስ። ስለዚህ ልጅዎ በምግብ ሰዓቱ ላይ እንዲያተኩር ምግብ ስንመግብ ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክ መገናኛ መዝጋት አለብን(ቲቪ፣ ታብሌት፣ስልክ...
9 ህፃናትን ለብቻ አለመመገብ ። ከቤተሰብ ጋር አብሮ መስጠት እናም ይዘናቸው ሳይሆን ከፊት አስቀምጠን መመገብ።
10. ከአንድ ዓመት ጀምረው ከኩባያ በደንብ መጠጣት ስለሚችሉ ጡጦ እንዲተው ያድርጉ ምክንያቱም ለጥርስ መበስበስ ስለሚያጋልጥ እናም ከአንድ ዓመት እስከ ዓመት ከሦሥት ወር ባለው ጊዜ የማታ ጡጦ ስለማይጠቅማቸው ያቁሙ። ይህም አላስፈላጊ ውፍረትን እና የጥርስ ጤንነትን ይጠብቃል
6 #ወር #የሞላቸውን #ምን እና #እንዴት #ተጨማሪ #ምግብ #እናስጀምራቸው? #ዝጉጁነት #ለምግብ #ጠጣር #ምግቦች #የአለምጤናድርጅት #ጤና #ማንኪያ #ጡጦ #አቡካዶ #ማንኪያ #አጃ #ሩዝ #አለርጂ #ምልክቶች #ቤት #የጡትወተት #የፎርሙላ ወተት #when #to start #feeding #milk #6 month#complementary #important
#ህፃናት#fypシ゚viral#ህፃናት##fypシ゚viral#baby#የህፃናትጤና#fypシ゚viral#ህፃናትን_ያሳድግልን##fypシ゚viral#babyboy##fypシ゚viral#babygirl#fypシ゚viral#pediatrics#fypシ゚viral#ጤናማህፃናት#fypシ゚viral#pediatria#fypシ゚viral#childhealth#fypシ゚viral#healthychild#fypシ゚viral#ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Пікірлер: 21
@user-bz5oz3ye7z
@user-bz5oz3ye7z 7 ай бұрын
እናመሰግናለን ወድማችን❤❤❤❤
@ephremhailu4744
@ephremhailu4744 6 ай бұрын
Thank you for share
@abebech3154
@abebech3154 6 ай бұрын
እናመሰግናለን❤❤❤
@ShewitMichael-bs8yy
@ShewitMichael-bs8yy 4 ай бұрын
Namsgenaln wendemi❤❤❤❤
@user-hz8xy3se7d
@user-hz8xy3se7d 8 ай бұрын
❤🙏❤
@user-iy7jv8en5e
@user-iy7jv8en5e 5 ай бұрын
ልጀ 5 ወር ከ ሁለት ቀኑ ነው ከ 28 ቀን በኃላ ነው መጀመር ያለብኝ ? በምንስ ላስጀምረው ሸሪፋስ ይመከራል ?
@munaahmed5876
@munaahmed5876 8 ай бұрын
እናማስገናለን ብርታ
@asnakeamsalu4423
@asnakeamsalu4423 19 күн бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@AsterAdelo
@AsterAdelo 3 ай бұрын
የኔ እየቀዘነ አሰቸገረኝ ውሀ ነው የምመሰለው
@abLEMLEM
@abLEMLEM 6 ай бұрын
ሰላም ዶክተር ልጄ formula milk በቅርብ ነው የጀመረችው ግን ከጠጣች በኋላ ማስመለስ እና በጡጦ አልጠጣም እያለች ነው ምን ላርግ
@Habeshahealthclinic
@Habeshahealthclinic 6 ай бұрын
በጣም ይቅርታ ስለዘገየው አሁን እንዴት ናት እናም ስንት ነው እድሜው
@Joel_1621
@Joel_1621 5 ай бұрын
አሁን ስንት ወሯ ነው እኔም ልክ እንዳንቺ ጡጦ እምቢ ብሎኝ የእናት ጡት ጫፍ የሚመስል ጡጦ አለ በሱ ጀመረልኝ በሱ ሞክሪ
@user-ol3jy8pn8y
@user-ol3jy8pn8y 7 ай бұрын
ሰላም ዶክተር 6ወራቸው እልቅ ሲል ነውዴ የሚጀመርላቸው ምግብ የኔ 5ወር ከ3ቀኗ ነው የመጀመሪያየ ናት አላቅም
@Habeshahealthclinic
@Habeshahealthclinic 7 ай бұрын
አዎ የሚሻለው ልክ 6 ወራቸውን ሲጨርሱና ቪዲዮ ላይ የተጠቀሱትን ዝግጅነት ሲያሳዩ ነው።
@user-ol3jy8pn8y
@user-ol3jy8pn8y 7 ай бұрын
@@Habeshahealthclinic እሽ አመሰግናለሁ
@lidiasisay3742
@lidiasisay3742 6 ай бұрын
Xute mayxabsaa ba 4 war bejmre chgr allwe
@Habeshahealthclinic
@Habeshahealthclinic 6 ай бұрын
ስለዘገየው ይቅርታ ...ጡት ሆን ፎርሙላ ቢወስድም እስከ 6 ወር መጠበቅ የተሻለ ነው። ነገር ግን አማራጭ ከጠፋ ያው አሁን 5 ወር ሆኖታል ብታስጀሚሪው ችግር የለውም።
@eyerusalemeshetu9672
@eyerusalemeshetu9672 Ай бұрын
ሰላም አቡካዶ ማስጀመር እፈልጋለሁ ግን ያለሎሚ መሆኑን ሳስበው ይጎዳው ይሆናል እያልሁ ገና አላስጀመርኩትም ማለት ለኛ እንኳን ስንጠቀም ሎሚ ተጠቅመን ነው ስለዚ በባዶ ሊጎዳው አይችልም 8 ወር ነው
@Habeshahealthclinic
@Habeshahealthclinic Ай бұрын
ሎሚን ብቻውን ከሆነ ከ 1 ዐመት ቡኋላ መጀመር ያለበት በተለያዩ ምክንያቶች። ነገር ግን በጣም በትንሹ በምግብ እንደሚጨመረው ችግር የለውም። አቮካዶ ትኩስ እና ደህና እስከሆነ ድረስ እኮ ሎሚ ግዴታ አይደለም። ስለዚህ እንደተመቸሽ መስጠት ትችያለሽ። ደሞ ይህ ቪዲዮ ከጠቀመሽ ለሌላው....
@user-tu9fv7ox2z
@user-tu9fv7ox2z 8 ай бұрын
Le 6were lige ye lame wetate biteta cheger alwe
@Habeshahealthclinic
@Habeshahealthclinic 7 ай бұрын
የላም ወተት 1 ዓመት እስኪሞላው ባንሰጥ ጡሩ ነው። የማንሰጥበት ምክንያቶች ፡ 1. #ጨቅላ #ህጻናት #የእናት #ወተት ወይም የ ፎርሙላ ወተት እንደሚፈጩት የላም ወተትን ሙሉ በሙሉ ወይም በቀላሉ መፈጨት አይችሉም። 2. የ#ላም ወተት ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን እና ማዕድናት ይዟል፣ይህም አዲስ የተወለደወን እና ያልጠነከሩ #ኩላሊቶችን ያስጨንቃል። 3. በተጨማሪም የላም ወተት በቂ መጠን ያለው #ብረት፣#ቫይታሚን ሲ እና #ጨቅላ ህጻናት የሚያስፈልጋቸው ንጥረ ነገሮች የላቸውም። 4. አልፎ ተርፎም በአንዳንድ ሕፃናት ላይ የደም ማነስ ችግር ያስከትላል።ምክንያቱም የከብት ወተት ፕሮቲን የሆድንና የ#አንጀትን ሽፋን ስለሚያስቆጣ በሰገራ ላይ ደም እንዲፈስ ያደርጋል ሳይታይ ። የ#ላም ወተት እንዲሁ ለታዳጊ ሕፃናት በጣም ጤናማ የሆኑ የስብ ዓይነቶችን አልያዘም። አንዳንዴም #ትኩሳት እና #ተቅማጥ ወይም ከባድ ህመም ያስከትላል። በነዚህ ምክንያቶች ልጅዎ 12 ወር አካባቢ እስኪሞላቸው ድረስ ምንም አይነት አማራጭ ከሌለ በስተቀር ምንም አይነት የላም ወተት መውሰድ የለበትም።
IS THIS REAL FOOD OR NOT?🤔 PIKACHU AND SONIC CONFUSE THE CAT! 😺🍫
00:41
🍕Пиццерия FNAF в реальной жизни #shorts
00:41
Они убрались очень быстро!
00:40
Аришнев
Рет қаралды 3,1 МЛН