ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጣሁበት መንገድ || Kawsar Ali

  Рет қаралды 52,703

እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

Күн бұрын

Original Video • የሶማሊ ክርስቲያን እህት ድንቅ ምስ...
መልካም ዜና
የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።
ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”
መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-
“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)
ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።
ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
- (ኢሳይያስ 53፥10)
ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።
{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)
እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።
1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።
2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።
የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
/ @dhugaanniboqachiisa
አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
t.me/BibleAndMe
Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

Пікірлер: 644
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 4 ай бұрын
ሁላችሁም like በማድረግ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ አድርጉ። ምስክርነቷን እንዴት አያችሁት?
@debebeteklu1451
@debebeteklu1451 4 ай бұрын
ተባረኩ !
@David85979
@David85979 4 ай бұрын
Leigzaber minn yisanewal?
@samiraabdohoussein6953
@samiraabdohoussein6953 4 ай бұрын
አያልቅም ድረማችሁ
@jjamila542
@jjamila542 4 ай бұрын
ድረማው እስከ ስንት ክፍልነው ወይስ ጨረሰች 😂😂
@yesufMohamed-hf8mz
@yesufMohamed-hf8mz 4 ай бұрын
😂😂😂😂😂
@markoskaltiso7153
@markoskaltiso7153 3 ай бұрын
እህቴ እግዚአብሔር አብዝቶ አብዝቶ ይባርክሽ ! የወንጌል አገልግሎታችሁን መደገፍ አንድንችል አካውንትና ስልካችሁን አሳውቁን; ኢየሱስ ለዘለዓለም ጌታ ነዉ !
@የሺየአገሬናፋቂ
@የሺየአገሬናፋቂ 4 ай бұрын
ጌታየመሰገን እንም ሙስላም ነበረሁ የአዉም ወሎወስጥ ጌታየማይታወቅበታ ገን እንደት እንደት እንደሚወጣየአውቃል እየሱሰ ጌታነው ❤❤❤❤❤❤❤💞💞🎉🛐🛐🛐🙏🙏እንኳንጌታእየሱሰ አረዲን
@HajeraRedi
@HajeraRedi 4 ай бұрын
ክክክክክ የምር የወሎ ሙስሊም???😁😁
@SinteWerku
@SinteWerku 3 ай бұрын
ጌታ ኢየሱስ ይባርክሽ እህቴ እንዳንቺ ለክርስቶስ የተሰጠ እና ታማኝ የሆነ ህይወት ይስጠን ተባረኪ ምሳሌ ነሽ!!!!
@senaittecle8342
@senaittecle8342 3 ай бұрын
Amen Amen Amén 🙏 እግዚአብሄረር አምላክ ዘበንሽ ይባርክ አንችንና ባለቤትሽን ለብዝዎች ማምለጫ ያድርጋቹ ኢየሱስን ምታሳዪ ብርሃናቹ ይድመቅ እንወዳቹ አለን❤❤❤
@wesenllemma-vt4oc
@wesenllemma-vt4oc 3 ай бұрын
Amen amen amen cover with the blood of Jesus almighty amen 🙏 🙌 ♥️
@ZuZuZules
@ZuZuZules 4 ай бұрын
እኔ ሙስሊም ኦርቶዶክስ ነበርኩ በመጨረሻም ኢየሱስን አግኝቼ አረፍኩ ኢየሱስ ያሳርፋል
@meronealmo2877
@meronealmo2877 3 ай бұрын
Wawu yese amen 🙏🙏🥰
@ወለተስላሤየሰመአቱየቅዱስ
@ወለተስላሤየሰመአቱየቅዱስ 3 ай бұрын
እእእእእ ከኦርቶዶክስ ወተሽነው እረፍት ያገኘሽው
@ZuZuZules
@ZuZuZules 3 ай бұрын
@@ወለተስላሤየሰመአቱየቅዱስ እንደዚያ ማለቴ አይደለም ውዴ የሐይማኖት ድርጅት አያሳርፍም አያድንም ሰው የሚድነው የሚያርፈው ኢየሱስን ሲያገኝ ነው ማለቴ ነው 💒
@tbeltsa9525
@tbeltsa9525 3 ай бұрын
Egiziyabeher yimesigen ekani wede tikikilegha hayimanoti metashi ena gin me.musilim demo oritodokusi ale enideye or to maleti ketigha maleti new okisi maleti ketitegha maleti new ena enidexa alawekim neber
@NatiJabir
@NatiJabir 3 ай бұрын
@@ወለተስላሤየሰመአቱየቅዱስ እና
@jesuspower2638
@jesuspower2638 3 ай бұрын
በጣም በጣም አመሰግናለሁ በርቱ!! ወንጌል የማይካድ እውነት ነው።
@mesk_erem
@mesk_erem 3 ай бұрын
ኦኦኦኦኦ ኢየሱስ ጌታ ዘመንሽን ይባርክ እህቴ ይህ ማንቂያ የሆነ ምስክርነት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም❤❤❤❤❤
@bertukanosman6760
@bertukanosman6760 4 ай бұрын
አቤት እየሱስ እውነተኛ ዳኛ! በፍቅር ሀሉንም የሚያምበረክክ!❤❤❤
@ZuZuZules
@ZuZuZules 4 ай бұрын
ኢየሱስ እኮ መልካም አባት ነው😢😢😢😢
@israelalge
@israelalge 4 ай бұрын
“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” - ዮሐንስ 14፥6
@salemgashe8721
@salemgashe8721 4 ай бұрын
እውነት ነው በዚመልክት እኛ ሙስሊሞች እናምናለን ምክንያቱም በዛ ዘመን ሰወች አምላካቸውን የሚያውቁት በእየሱስ በኩል ነው ለዚእም ነው እየሱስ የተላከው ስለ አምላኩ አንድነት እንዴት መፀለይ እንዳለባቸው ምን ተፈቅዶል ምን አልተፈቀደም አምላክ ማነው የሚለውን በእየሱስ በኩል እንጂ በምንም በኪል ፈጣሪን ማወቅ ወደፈጣሪ ሃሳብ መምጣት አይቻልም ነበር ዝለዚህም ነው እየሱስ የተላከው በሱ ትምእርትበኩል እንጂ በሌላ በኩል የፈጣሪን ሃሳብ ማወቅ አይቻልም ነበር ለዛ ነው እየሱስ እኔ መንገድ ሂወት ነኝ በኔ በኩል እንጂ የፈጣሪን ፈላጎት የምታውቅት በሌላ መንገድ ከሄዳቹህ ወደገነት አትሄዱም በኔ መንገድ ከሄዳቹ የ ፈጣሪን ምህረት አግኝታቹ ወደገነት መዳረሻው የን ስትምሮ ነው ማለቱ ነው የአረዳአድ ችግር ብቻ ነው
@salemgashe8721
@salemgashe8721 4 ай бұрын
ግን አንድ ጥያቄ አለኝ እየሱስ የተላከው ለአለም አይደለም ለ እስራኤላውያን ብቻ ና ብቻ ነው ለወገኖቹ እስራኤላውያን የተላከ መሆኑን እራሱ ተናግሮል 😮 ወደ ሐዛብ እንዳትሄዱ ብሎቹ ነበር ግን ለምንድነው እየሱስስን የማትሰሙት ከኛጋር እልክ ተያይዛቹ ነው
@bertukanosman6760
@bertukanosman6760 4 ай бұрын
እኔም እንዳንችው ከ ድቅድቅ ጨለማ በክርስቶስ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ተጠራሁ❤
@zebibajemal2023
@zebibajemal2023 4 ай бұрын
ታድለሽ የሚገርም ምስክርነት እኛንም እግዚያብሄር ይርዳን ተባረኪ እህቴ ብርክ በይ ጥማቴን ነዉ የነገርሽኝ እግዚያብሄር ከናንተ ጋር ይሁን
@hassttrrff7936
@hassttrrff7936 3 ай бұрын
ጌታ መልካም ነው በእውነት እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም
@taezazwoldu5302
@taezazwoldu5302 3 ай бұрын
Very great testimony! This shows how the heart of people becomes stony to trust jesus.
@dinkutasew
@dinkutasew 3 ай бұрын
ዋዉ እግዚአብሔር ይባርክሽ ማርያምን በጣም ደስ የሚል ሚዲያ❤❤❤❤
@tewachewahadu
@tewachewahadu 3 ай бұрын
ተባረኪ፣ እውነተኛውን የኢየሱስ መንገድ እንሰብካለን። ብዙ የሱማሌ ዜጎች ወደጌታ እየመጡ ነውና ጸልዩ።
@ngussebayou9288
@ngussebayou9288 3 ай бұрын
አቤት የእግዚአብሔር ምህረቱ ጌታ ምስኪኖችንም ይወዳል ደካሞችንም ይወዳል ሰው የጣለውን ያነሳል ❤❤❤❤❤❤❤🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@kidilove1715
@kidilove1715 4 ай бұрын
❤❤ ሃሌሉያ ጌታ ኢየሱስ የተባረከ ይሁን እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ይሁን❤❤
@sarahaile9628
@sarahaile9628 3 ай бұрын
እውይ ጌታየሱ ይባርክሽ ታድለሽ አብሬሽ ለወጌል ብዞር ፀልይልኝ ተሳክቶልሻልአብሮሽ የወጣውን ባለቤትሽን ጌታ አብዝቶ ይባርከው
@hhhjjjjjjkkjjmlkjjk
@hhhjjjjjjkkjjmlkjjk 4 ай бұрын
እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን እቺ በክርስቶስ ፍቅር የተነካች እንደሆነች ያስታውቃል
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 4 ай бұрын
ግን የሚለው የሚያስፈልግ አልመሰለኝም። በተረፈ እግዚአብሔር ይባርክሽ🥰
@user-pd1tm5wn3s68
@user-pd1tm5wn3s68 4 ай бұрын
እኮ ድሮውንም ሙስሊም አይደለችም
@user-pd1tm5wn3s68
@user-pd1tm5wn3s68 4 ай бұрын
@@ewnetyasarfal ፊቱኑም ክርስቲያን ናት
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 4 ай бұрын
@user-pd1tm5wn3s ኧረ ሙስሊሞች ግን እመኑ ተዉ😁 ሰው ሲወለድም ሙስሊም ሆኖ ነው ሚወለደው ትሉ የለንዴ እንኳን የሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ ያደገችና የኖረችው ይቅርና!! ኧረ ቢያንስ ከራሳችሁ ቁርአን ጋር ተግባቡንጂ! እንዴ!?
@tesfagabirteame9607
@tesfagabirteame9607 4 ай бұрын
Please come to Jesus Christ. I was an orthodox too.
@GetachewShegie-u5o
@GetachewShegie-u5o 4 ай бұрын
አቤት ጌታ ቸርነትህ!!!!!!
@ademsalh9529
@ademsalh9529 3 ай бұрын
Thanks Lord Jesus Hallelujah Amen
@danydan6662
@danydan6662 3 ай бұрын
Woww...Ewnet ye Egziabher Menfes anchi'Gar endale yastawqal. Ehte tebareki ❤❤
@tsigebungul2150
@tsigebungul2150 3 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን እናንተ ሸክማችሁ የከባደባችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ ብሎ ስጠራን በሚክናያት ነው እግዚአብሔር ይመስገን እየሱስ ከሞትም ያነሳል አሜን!!!!❤❤❤❤❤❤
@betiadis
@betiadis 4 ай бұрын
ጌታ ኢየሱስ ይባርካችሁ❤
@ሸገርዩቱብ-ጘ7ፈ
@ሸገርዩቱብ-ጘ7ፈ 4 ай бұрын
قال تعالى : { الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُمْ بِذِكْرِ اللَّهِ ألا بذكر اللَّه تطمئن القلوب } (الرعد : 28 ) ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@YusraAbdulwahab-oy6ks
@YusraAbdulwahab-oy6ks 3 ай бұрын
Allah❤❤
@SirajBirreabo
@SirajBirreabo 3 ай бұрын
አንቺ እህት ጌታ እንኳን ረዳሽ።የጸሎት ርዕሶቼን አሰፋሽ ተባረኪ
@Natiye23
@Natiye23 4 ай бұрын
😢😢😢 እያለቀሱኩ ነው የስማውት ክብር ምስጋና ለአምላካችን ለኢየሱስ ይሁን አሜን❤❤❤
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 4 ай бұрын
አሜን!🙏
@jjamila542
@jjamila542 4 ай бұрын
😂😂😂 ሶፍት ማነው ያሰጠህ በክህ😂አልቅሰህ ሞትክ አይደል አይዞህ በቃ 😂
@አፍያዩቱብ
@አፍያዩቱብ 4 ай бұрын
@@ewnetyasarfal ጥያቄ አለኝ መልስካለህ??ከመፃሃፍቅዱሳቹሁ???
@ሀከጀበጀከለጀገፈ
@ሀከጀበጀከለጀገፈ 4 ай бұрын
ተረተረቶ ነው ያሰለቀሰህ ። ገረም እሚለኝ ህዝቡ መጃጃሉ
@awalediris1155
@awalediris1155 3 ай бұрын
@@Natiye23 wushtam.qoshasha
@Ggghjjjjj
@Ggghjjjjj 3 ай бұрын
አቤት የኢያሱስ ስራ ግሩም እና ድንቅ ነው የኢያሱስ ስራ አሜንንንንን❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@leaddanial
@leaddanial 3 ай бұрын
i am orthodox and Jesus is the lord so i have seen on u Jesus Christ bless all the world
@nansin4739
@nansin4739 4 ай бұрын
❤❤❤❤ ተባረክልኝ ጌታ ሆይ ተመስገን
@BekiBereket-lc6xp
@BekiBereket-lc6xp 3 ай бұрын
ሴት ሆነሽ በዚህ ማልፍ ይገርማል በእውነትም እግዚአብሔር በአንቺ ላይ ትልቅ ነገር አይቷል!🙏ስሙ ይባረክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው!❤️❤️
@ahmdhussein159
@ahmdhussein159 4 ай бұрын
ጌታ ስሙ ለዘላለም ይባረክ
@Alemtsehay777
@Alemtsehay777 4 ай бұрын
😭😭😭😭😭😭😭 ኢየሱስ ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ ሌላ ምንም አልልም። የኔ እህት ክርስቶስን መከተል ዋጋ ያስከፍላል። እህህህህህ ኢየሱስ ባንቺ አላማ አለዉ።
@seyaman-
@seyaman- 4 ай бұрын
ኢየሱስ በሷ ላይ ምን አይነት አላማ ኖ ያለው ኢየሱስ እናንተ እንደምትሉት ለናተ ሲል እራሱን ከሰዋ ወይንም ለናተ ሲል መዳንን ከሰጣችሁ ምንድን ኖ አላማው አልሃምዱሊላህ ረቢል አለሚን ኢስላም ከደዚህ አይነት ማስመሰል የጠራ ኖ ለምሳሌ በዚች ዱንያ ላይ ገንዘብ ለማግኘት ብዙ እንደምትደክሙት አኼራንም ወይንም የዛችኛዋን አለም ለማግኘት ብዙ መልፋት አለብህ እናም ኢስላም በነብዩ ኢሳ ያምናል እሱም የመርየም ልጅ ነብይ እንጅ ጌታ አይደለም
@Alemtsehay777
@Alemtsehay777 4 ай бұрын
@@seyaman- ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለዘላለም ያድናል። እህቴ ያለ ኢየሱስ ህይወት መንገድ እዉነት የለም ዮሐ 14÷6ን አንብቢ ያለ ኢየሱስ አብ(አባት) ጋር መግባት አይቻልም። ዮሐ 11:25 ምን ይላል መሰለሽ 👉ኢየሱስም። ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ህያዉ ይሆናል፤ ሌላ ቦታ ደግሞ 1ኛ ዮሐ 5:12 ልጁ ያለዉ ህይወት አለዉ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለዉ ህይወት የለዉም 👉ማር16:16 ያመና የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል። አየሽ? ቁራናችሁ ላይ ሱራ 7:179 አላህ ብዙዎችን ለገሀነም ፈጠረ ይላል ተመልከቺ አላህ ብለሽ የምትጠሪዉ የእሳት እራት አድርጎሻል። ከዚህ ከዘላለም ሞት ብታመልጪ ይበጅልሻል። ኢየሱስ ከሲኦል ያዉጣሽ።
@martasila5996
@martasila5996 3 ай бұрын
Praise God! Keep preaching the good news.
@ህይወቴኢየሱስነውኢየሱስጌ
@ህይወቴኢየሱስነውኢየሱስጌ 4 ай бұрын
እሰይ አሜንንንን ኢየሱስ ጌታ ነው።🙏
@Atonement145
@Atonement145 3 ай бұрын
የዘመኑ ሰማርያዊት ሴት ....እግዚአብሔር ስለአንቺ ይባረክ!!
@solomonmesersha4938
@solomonmesersha4938 3 ай бұрын
Amen Bless you
@Abdulqadr13
@Abdulqadr13 4 ай бұрын
የምትናገረው እውነት ነው ሶማሌዎች ተስፋ ሲቆርጡ ሴቶቹ ጋዝ አርከፍክፈው ነው የሚያቃጥሉት የናዝሬቱ ኢየሱስ ንጉስ ህያው አንደኛ የዘላለም አምላክ በሥጋ የተገለጠ እግዚአብሔር ብቸኛው የአብ ልጅ እልልል እኔም ተስፋ ቆርጩ ሞት ሞት ሲሸተኝ ደረሰልኝ አዳነኝ እህታችን ከውሰር የረዳሽ እግዚአብሔር ከመከራ ያወጣሽ እርሱ ጌታ ኢየሱስ ሥሙ ለዘላለም ብሩክ ይሁን::
@Hani-v9h
@Hani-v9h 4 ай бұрын
Ameen enem andua negn yadangn ke ebdet esu e eysus yenebse nigus new. Haleluja
@HajeraRedi
@HajeraRedi 4 ай бұрын
ክክክክ የምር የነዝሬት ሴቶች ጋዝ ነዉ ሚያርከፈክፉት ??
@Taredan77
@Taredan77 4 ай бұрын
ጌታ በሥራ ላይ ነው ጌታ ዘመንሽን ይባርክ🙏🙏
@thabangaleseng9294
@thabangaleseng9294 4 ай бұрын
ጌታ አምላኬክብር ምስጋናላንተ ብቻ ይሁንስለ ኢህቴ
@sebleakelilu4365
@sebleakelilu4365 3 ай бұрын
ኢየሱስ የዓለም ሁሉ አዳኝ ነው። ፀጋ ይብዛላችሁ ። ተባረኪ።
@AbiyeFiseha
@AbiyeFiseha 2 күн бұрын
ገላትያ 1:15-16,ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም:: እህቴ በእናትሽ ማኅፀን ሳለሽ ለለየሽ ጌታ የጸጋውን ጥሪ ሰምቶ ወደ እርሱ ዞር ለማለት ጸጋውን ያበዛልሽ ጌታ ክብር ይሁንለት አሁንም ጌታ ገና ብዙ ምርኮ ይሰጥሻልና በርቺ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው::
@Jesus_is_Lord_stn25
@Jesus_is_Lord_stn25 4 ай бұрын
ኢየሱስ ያድናል።
@BEREKETBOGALE-mr6oh
@BEREKETBOGALE-mr6oh 4 ай бұрын
📖እንኩዋን ጌታ ረዳሽ, ከስቴት አመለጥሽ, ጌታ እየሱስ ያድናል, Glory to jesus
@selamahmedahmed1896
@selamahmedahmed1896 4 ай бұрын
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉
@SinduBeharu
@SinduBeharu 3 ай бұрын
ማን እንደ እየሱስ እየሱስ እኮ የሚያሳረፍ የሚጠብቅን የሚያስመልጠን እውነተኛ ወዳጃ እሰከ ጥግ አፍቃሪ ኡፉ እወነተኛ ወዳጄ እዬሱስ
@NetsiAragawu
@NetsiAragawu 3 ай бұрын
Woooow ይህን ቪዶኦ ያቀረብክልን ወንድማችንም መስክርነት የሰጠሽወም እህት እግዚያብሔር ፀጋን ይጨምርላችሁ።
@user-cg4sd4wr7s
@user-cg4sd4wr7s 3 ай бұрын
ስላቺ ጌታ ይባረክ ዘመንሽ በጌታ ቤት ይለቅ
@solomonaynalem9035
@solomonaynalem9035 4 ай бұрын
እግዚአብሄር በጸናች እጁ ህዝቡን ይታደጋል!!!
@tamratgodebo3759
@tamratgodebo3759 3 ай бұрын
እግዚአብሔር ራሱ ለሶማሊያ ህዝብ አንቺን ይልካልና ተዘጋጂ እግዚአብሔርን ስላንቺ እናመሰግናለን :
@DiresewdikasoDakero
@DiresewdikasoDakero 4 ай бұрын
የጠራሽ ጌታ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ታማኝ ነው ፤ከዘለዓለም ሞት አምልጠሻል አይተውሽም ፤
@YohannesAhmed-r7x
@YohannesAhmed-r7x 3 ай бұрын
ከባዶነት ወደ ሙላት ያመጣሽ ያመጣሽ ጌታ ስሙ ይባረክ እኔም የዛው ወገን ነበርኩ ጌታ ይባረክ ከዛ ከግብፅ ሹንኩርት ያስመለጠን ስሙ ለዘላለም ይባረክ
@Azeb987
@Azeb987 4 ай бұрын
እንዴት ያለ ድንቅ ምስክርናት ናው ጌታ እየሱስ ይባርክሽ ፃጋው ይብዛልሽ ❤️
@mesfinasefa5749
@mesfinasefa5749 4 ай бұрын
ድርሰት ከፈለክ ለዛ መሀይም መሀመድ ሴጣን ይሰጠውን ድርሰት አምብብ 72 ህምስ ስትሞት ትሸለማለክ የሚለውን
@tseheyneshfaniel9066
@tseheyneshfaniel9066 3 ай бұрын
ዋውው ኣምላክ ይመስግን ተባረኩ ❤❤❤
@ZerfuZed
@ZerfuZed 4 ай бұрын
Geta yimesgen wow migerim newu wongel yilewutal ehenin mitsemu geta yibarikachu lelelochim like like adirgu
@ganethailu7156
@ganethailu7156 4 ай бұрын
ኢየሱስ ጌታ ነው ❤😢
@Sabdusha
@Sabdusha 4 ай бұрын
ኢየሱስ ጌታ ነው አሜን:አሜን:አሜን!!!
@SameyMohmmed
@SameyMohmmed 3 ай бұрын
Wow እየሱስ ጌታ ነው
@tadhab3092
@tadhab3092 4 ай бұрын
Jesus is the answer "
@jimmyjimmy5775
@jimmyjimmy5775 4 ай бұрын
Inem Muslim naberku geta adanegn simu ybarek❤
@marthayohannes7309
@marthayohannes7309 3 ай бұрын
Egziabher amlak yibarikish ehite ewnti bileshal kibir Le geta eyesus yihun tsegaw yibizalish ehite esu yeterash Simu yibarek lemilimelign 💕🙏💕🙏 kawser😢😢😢
@tizitagetachew5078
@tizitagetachew5078 3 ай бұрын
ኢየሱስ ጌታ ነዉ እህቴ ተባረኪ
@TejeTigst
@TejeTigst 3 ай бұрын
ድንቅ ጌታ ስሙሁ ይባርክ 😢😢😢
@MohammedAli-cd9go
@MohammedAli-cd9go 4 ай бұрын
አላህ መረዳት እንዳይኖር የሚያደርግ ከሆነ ሰውን አይወድም ማለት ነው። ብታምንም ባታምንም ኢየሱስ አምላክ ; ጌታም ; አዳኝም ; የእግዚአብሔርም ልጅ ነው። አሜን!
@ElduErsumo
@ElduErsumo 4 ай бұрын
Amen 🙏
@HajeraRedi
@HajeraRedi 4 ай бұрын
😁😁😁 አላህን አታዉቀዉም ምን ይደረግ
@selubecca
@selubecca 4 ай бұрын
@@HajeraRedi nigerign Allah manw?
@MisganuErdedo
@MisganuErdedo 3 ай бұрын
ኢየሱስ ያድናል
@mememalase9018
@mememalase9018 4 ай бұрын
Jesus is lord ❤
@HanaBekele-d8k
@HanaBekele-d8k 4 ай бұрын
Bro ትልቁ እግ/ር ይባርክህ በጣም እንወድሀለን❤❤❤❤
@AntenehFeleke-ln2cd
@AntenehFeleke-ln2cd 4 ай бұрын
አቤት የኛ ክፋት ማረን ማረን ንፍግነት ይመታ ከኛላይ ውይ አንቺ መልካም ሴት ያረግሽ ተባረኪ ❤️🙏
@zoretozorito-un1es
@zoretozorito-un1es 4 ай бұрын
ኢየሱሰ የጌቶች ጌታነው አሜን ተባርክል❤❤❤
@thedumbversionofeinstine6245
@thedumbversionofeinstine6245 3 ай бұрын
እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል እግዚአብሔር ይመስገን ስሙ ለዘላለም ይክበር ይመስገን ከጠላት ዲያቢሎስ ጉሮሮ ነጥቆ ያወጣን ዋው ሃሌሉያያያያያያያያያያያያያያ አ ሜ ን አ ሜ ን አ ሜ ን አሜንንንንንንንንንን
@eigtyk82ghir
@eigtyk82ghir 4 ай бұрын
ከፌሬአቸው ይታወቃሉ አለ ጌታችን መዳኔታችን አቤት እስልምና የማፍያ ሀይማኖት ጌታ እንኳን ረዳሽ እናቴ ኢየሱስ እዲ ነው ይገባል ማንንም የማይፈራ የኔ ጀግና አሜን ጌታ ይባርክክ ወድሜ❤
@JOHNFIKRE1
@JOHNFIKRE1 2 ай бұрын
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
@betiadis
@betiadis 4 ай бұрын
ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አፍቃሪ 😢❤
@LidiaEyasu
@LidiaEyasu 4 ай бұрын
ጌታ ሆይ ክብር ላንቴ ይሁን!! ጨለማ ውስጥ የሚመሩ ህዝቦችን ወደምደነቅ አውጣቸው👉🙏👈bro tebarek!!! Anten betselot engizalen!! lebizuwoch eyaberahi new!!እናንተ ለአለም ብርሃን ናችሁ እንደተባለው❤❤❤🎉🎉
@ewnetyasarfal
@ewnetyasarfal 4 ай бұрын
አመሰግናለው🙏
@AlmazKidanemariam-m4b
@AlmazKidanemariam-m4b 3 ай бұрын
WAW! Yes, Lord Jesus you are the Lord of Lord's.
@tsion797
@tsion797 3 ай бұрын
እውነተኛው አሳራፊ የእግዚአብሔር ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ ነው እንኳን ጌታ እረዳሽ እውነት ህይወት መንገድ ወደሆነው ጌታ መጣሽ
@afena100
@afena100 4 ай бұрын
Jesus is LORD !
@ZerihunAyele-zl8lt
@ZerihunAyele-zl8lt 3 ай бұрын
ተባረኪልኝ❤❤❤❤
@trhaskafel6109
@trhaskafel6109 4 ай бұрын
❤❤❤❤❤ AMEN WAWWW BETAM YETEBAREKECH AND LE BEREKET NECH !!!!!!!!!!!!
@TedhomeWoldesemayat
@TedhomeWoldesemayat 4 ай бұрын
ተባረኪ ! አዲስ ዘመን እና ጊዜ ይስጥሽ!!
@HassenNuri-fx5xo
@HassenNuri-fx5xo 4 ай бұрын
ጀለቢያ ለብሼ መስጊድ እሄድ ነበር ያለችው እንኳን ሙስሊም ልትሆን ሙስሊም ጎረቤት እንኳ የላትም ሁሉም እንደሚያውቀው ጀለቢያ ወንድ ነው የሚለብሰው
@حايةاحمد
@حايةاحمد 4 ай бұрын
ቀጣፊ ዉሸታምነች ወላሂ ሀሲቤላህ ወኒእመል ወኪል
@tewachewahadu
@tewachewahadu 3 ай бұрын
አንተ ሰው፣ ጀለብያ መልበስ መዳኛ አይሆንም፣ መዳን በየሱስ ነው። እምነት በፈቃድ እንጅ በሰይፍ አይደለም እና ወደጌታ ና ይወድሀል።
@HassenNuri-fx5xo
@HassenNuri-fx5xo 3 ай бұрын
አማርኛ አምብቦ መረዳት አትችልም እንዴ ሴትየዋ የዋሸችው ሴት ጀለቢያ በፍፁም ለብሳ ወደ መስጊድ አትሄድም ስለዚህ ሙሉታሪኳ ውሸት ነው እየሱስ ብቻ ነው የሚወደኝ አባቱስ አይወደኝም መንፈስቅዱሱስ አይወደኝም ? ሥስት አምላክ ማምለኩን ትተህ ፍጡርን ሁሉ ወደ ሚወደው አባት አምላክ እናት ፍጡር የሌለው የሁሉ ፈጣሪ አላህ የሚመለክበት ወደ እስልምና ተመለስ
@MarizaHusain
@MarizaHusain 3 ай бұрын
Madanyi ba libsi ayidellem,inem musilim nabarku,antem tolo na wandime,iyesuus ifaligahal
@tsion797
@tsion797 3 ай бұрын
​@@HassenNuri-fx5xo ከብርሀን ወደ ጨለማ እንዴት ሆኖ ይልቁኑ ነይ ወደ እውነተኛው ጌታ
@kenessabukuna6937
@kenessabukuna6937 3 ай бұрын
Woooooooooooooooooooow Living Testimony ❤❤❤❤❤ May God bless you more and more❤❤❤❤✝️✝️🌹✝️✝️✝️✝️✝️✝️🌹🌹🌹🌹🙏🙏🙏🙏✅✅✅✅✅ Welcome home Sister✝️✝️You are at right place ✅✅✅✅✅✅✅✅
@Lifeisshort-p5k
@Lifeisshort-p5k 4 ай бұрын
ተባረኪ
@raheltekle4302
@raheltekle4302 3 ай бұрын
አሜን 🙏🙏🙏🔥🔥🔥❤️
@ShitayeMekonnen
@ShitayeMekonnen 4 ай бұрын
Birkk beyilegnn biewunt geta riedtoshall amennn❤
@israelalge
@israelalge 4 ай бұрын
ዮሐንስ 3 ¹⁶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ¹⁷ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና። ¹⁸ በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል። … ³⁶ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።
@birhanuzerga4520
@birhanuzerga4520 4 ай бұрын
እየሱስ ያድናል እየሱስ ክርስቶስ ትላንትና ዛሬም እስከ ዘላለም እስከዘላለም ያው ነው እግዚአብሄር ይባርክሽ ዘመንሽን ይባርክሽ
@mimiofarah4565
@mimiofarah4565 4 ай бұрын
እየሱስ ጌታ ነው እኔም እንድ ህዕቴ ከውሰር አርጌሳ ነው ጌታን ተቀብዬ የተጠመኩት
@tina-lv4pz
@tina-lv4pz 4 ай бұрын
Amen
@YordiTedla
@YordiTedla 3 ай бұрын
ጌታ ይባርክሽ
@Mimi-d7u3v
@Mimi-d7u3v 3 ай бұрын
ጌታ ደርሶልሻል ❤❤❤❤❤
@fikirtehailu1431
@fikirtehailu1431 4 ай бұрын
Tebareki, Jesus is Lord
@ህይወት4502
@ህይወት4502 4 ай бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን 🎉🎉🎉🎉
@romangebremedehin8087
@romangebremedehin8087 3 ай бұрын
አሜን፣እንኳን፣ጌታ፣ረዳሽ፣ክርስትና፣በእንደዚህ፣ነው፣የሚያሰደሰተው፣
@Bally-hy6zk
@Bally-hy6zk 4 ай бұрын
Kebre Legeta Yihun Tebarki❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@thionlema7724
@thionlema7724 4 ай бұрын
የገረመኝ ኦርቶዶክሶቾ ሰው በክርስቶስ ሲድን ምን እንደሚያንጨረጭራቸው ለነገሩ አንዳንድ የደብተራ እና የመሪጌታ መንፈስ የተጠናወታቸው ፀረ ክርስቶስ አሉ በናዝሬቱ ክርስቶስ እየሱስ ሰም መንፈሱ የተመታ የደቀቀ ይሁን ሙስሊሞች ደሞ ማመን ስለከበዳቹ ሙስሊም አይደለችም እያላቹ ነው እሷ ግን በስልጣን ክርስቶስ እየሱስ አምለክ እንደሆነ እየሰበከች ነው ብዙ ሙስሊሞች እየሱስ ክርስቶስን እየተቀበሉ እያመኑ ነው ሃሌሉያ እየሱስ ጌታ ነው አመረን
@kalkidangetnet6464
@kalkidangetnet6464 3 ай бұрын
Hallelujah geta hoy min libelih Man libelih
@basazin-hb5ow
@basazin-hb5ow 4 ай бұрын
Tebark bebzu yetewdedeshe meet jegena neshi berche ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@kalkidangetnet6464
@kalkidangetnet6464 3 ай бұрын
Sile achi geta yibareki Isin tetegito yafera man newu ??? Simu yibareki geta hoy ewodewalewu abba ewodewalewu Ante liyu neh geta hoy Hallelujah erefitachin hoy simih yibarek🎉🎉🎉🎉🎉
Зу-зу Күлпаш 2. Бригадир.
43:03
ASTANATV Movie
Рет қаралды 587 М.
pumpkins #shorts
00:39
Mr DegrEE
Рет қаралды 94 МЛН
规则,在门里生存,出来~死亡
00:33
落魄的王子
Рет қаралды 30 МЛН
Bike Vs Tricycle Fast Challenge
00:43
Russo
Рет қаралды 112 МЛН
መሃመድ አበባው ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጣባቸው ምክንያቶች
1:00:52
እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal
Рет қаралды 9 М.
የዘር እርግማንን እንዴት እንስበር?
36:48
Prophet Jossy Elijah Ethiopia official
Рет қаралды 18 М.
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ (ክርስቶስ) የሆነው መቼ ነው?  በወንድም ዳዊት ፋሲል
27:11
Зу-зу Күлпаш 2. Бригадир.
43:03
ASTANATV Movie
Рет қаралды 587 М.