ለህይወቴና ዒባዳዬ ቅለት ከፈጠረልኝ የጥቂቶችን አስተያየት መከተል እችላለሁን?

  Рет қаралды 113

Afroza Tube

Afroza Tube

Күн бұрын

ሸይክ አክረም ነደዊ- ሸይክ አክረም ነደዊ የእንግሊዝ እስላማዊ ዓሊም ሲሆኑ የካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ እስላማዊ ኮሌጅ ዲን እና የ Al-Salam ተቋም ፕሪንሲፕል ናቸው፡፡
ሙፍቲ የዒልም ጉዞውን የጀመረው በእንግሊዝ አገር የመጀመሪያ ደረጃ የዐረብኛ እና የእስልምና ኮርሶችን በመውሰድ ነበር፡፡ ከዚያ በሸይክ ሐምዛ ዩሱፍ በመመሰጥ በዘጠናዎቹ መጨረሻ ወደ ሶሪያ አቅንቷል፡፡ የማሊኪ መዝሃብ ተከታይ የሆነው በዚያ ነበር፡፡ ከሞሮኮ፣ አልጄሪያ እና ቱኒዚያ በማሊኪይ ፊቂህ ተመርቀው ከመጡ ተማሪዎች ጋ አብሮ በመኖር መቅራት ጀመረ፡፡ ከዚያ በደማስቆ መዓሃድ አል-አማኒያ ዩኒቨርስቲ በመግባት መሠረታዊ የእስልምና ሳይንሶችን ተማረ፡፡
ወደ ፓኪስታን በመሄድ በኢስላማባድ ጀምዓህ ሙሐመዲያ ተቋም በመግባት በሸይክ አሚኑልሐሰናት ስር ቁርአንን ሐፍዟል፤ ተፍሲርንም ተምሯል፡፡ ሸይክ አሚኑልሐሰናት የታዋቂው ሱፊ ከረም ሻህ አል-አዝሃሪ ልጅ ናቸው፡፡
ከዚያ ወደ ሶሪያ በመመለስ ለሸይክ አብዱልሐዲ አጥ-ጠብዓዕ ቁርዓንን ተወጥቶላቸዋል፡፡ ሸይክ አብዱልሐዲ በቅዱስ ቁርአን ጠቢብነታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸው የሸይክ በክሪ አል-ተረቢሺ ቁልፍ ተማሪ ናቸው፡፡ ሸይክ አብዱልሐዲ ሙፍቲን ካዳመጡት በኋላ እስከ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶዐወ) የሚደርስ ሰንሰለት ያለው ኢጃዛ ሰጥተውታል፡፡
ሙፍቲ በዒልም ጉዞው ከጠቀሙት ጉምቱ ሰብዕናዎች መሃከል፡ ሼክ አብዱረዛቅ አል-ሐለቢ አል-ሐነፊ፣ ሸይክ ረመዳን አል-ቡጢ እና ሸይክ አብዱልገኒ አል-ዲቅቃር ይገኙበታል፡፡ ሸይክ አብዱልገኒ አል-ዲቅቃር ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የሰዋሰው ምሁር ሲሆኑ በሶሂህ ቡኻሪ ላይ ሳምንታዊ ትምህርት ይሰጡ ነበር፡፡ ሙፍቲ ከሸይክ አብዱልገኒ ጋ የቅርብ ግንኙነት እስከ መፍጠር ደርሶ ነበር፡፡ ምንም ቢሸመግሉም ጨዋታ አዋቂነታቸው ተፅዕኖ አሳድሮበታል፡፡
ኢጃዛውን ካገኘ በኋላ ወደ ፓኪስታን በመመለስ በካራቺ በሚገኘው ታዋቂው ጃሚዓህ ቢኖርያ የዓሊም ትምህርቱን (ደርስ-ኢ-ኒዛሚ) ቀጥሏል፡፡ በዚያ ተፍሲር፣ ሐዲስ፣ ዑሱል፣ የንፅፅር ፊቅህ፣ የዐረብኛ ቋንቋ፣ ዐረብኛ ሰዋሰው፣ ታሪክ እና ዐቂዳህ ትምህርቶችን እስከ ከፍተኛ ደረጃ ተምሯል፡፡
በመጨረሻ የትምህርት ዘመኑ እንደ መድረሳው ልማድ ዋና ዋና የሐዲስ መፅሐፍትን (ሙወጣ፣ ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ አቡ ዳውድ፣ ነሳዒ፣ ኢብን ማጃህ እና ሸርህ መዓኒ አሰር) ከነአረዳዳቸው ተወጥቷቸዋል፡፡ ወደ ሐዲሶቹ መሥራቾች የሚተረተር ሰንሰለት ያለው የማስተማር ኢጃዛ ተሰጥቶታል፡፡ ከ90 ተማሪዎች ሶስተኛ ነበር የወጣው፡፡
ከዚያ በዚያው ተቋም ለሁለት ዓመታት የቆየ የሙፍቲነት ትምህርት ወስዷል፡፡ በተለያዩ መዝሃቦቸ ፊቅህ ላይ ይብልጥ ዕውቀቱን አጥርቷል፡፡ የሙፍቲነት ትምህርቱን የተከታተለው የሐነፊይ መዝሃብን ከሙፍቲ አብደላህ ሹኻት (የሙፍቲ ተቂ ዑስማኒ ቁልፍ ተማሪ ናቸው)፤ የማሊኪ መዝሃብን ደግሞ ከሙፍቲ ሰሊም ስር ነበር፡፡
ካጠናቸው መፅሐፍት መሀከል፡ ሙደውወናት (በሰህኑን)፣ ረድ አልሙህታር (በኢብን ዓቢዲን)፣ መዋሂብ ዒጃሊል (በሐጥጣብ)፣ ፈዋኪህ ደውአኒ (በነፍራዊ) እና ሙወፈቃአት (በሻጢቢ) ይጠቀሳሉ፡፡
ሙፍቲ የዒልም ጉዞውን በዚህ ሳያበቃ ወደ አል አዝሓር፣ አል-ቀረዊዪን እና ዳሩል ሐዲስ ሐስሳኒያህ አቅንቷል፡፡
በ2005 ወደ እንግሊዝ ተመልሶ የመምህርነት ዕውቅና ተሰጥቶታል፤ የማስተርስ ዲግሪውንም አግኝቷል፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የአረብኛ እና እስላማዊ ትምህርቶችን አስተምሯል፡፡ ፍልስፍናንም በኮሌጅ ደረጃ አስተምሯል፡፡ ለሳይኮሎጂ ያለው ፍቅር ዳግም ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገባ አድርጎት የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡
በ2015 ወደ ተቲዩን ተጉዞ ሌላ ተፅዕኖ ካሳደሩበት ሸይክ ሙሐመድ ቡኹብዛን ጋር የመገናኘት ዕድል አግንቷል፡፡ እንዲሁም የሸይክ አብዱልሐይ አል-ቀጥጣኒ፣ ሸይክ አሕመድ አል-ጉማሪ እና ሸይክ ኢብን አሹር ተማሪ አግኝቷል፡፡ ሸይክም በሐዲስ፣ ፊቂህ እና በርካታ ብዙ መስኮች ላይ እንዲያስተምር ኢጃዛ ሰጥተውታል፡፡
ሙፍቲ አቡ ለይሥ አሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ የማሊክ መዝሃብ ዓሊሞች ጋር ይመካከራል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሸይክ ሙሐመድ ሩጊ (የቀረዊዪን ታላቅ ሸይክ)፣ ሸይክ አሕመድ ጠሃ ረይያን (በአል-አዝሃር ዋና አስተማሪ ሲሆኑ፣ በግብፅ የማሊኪ መዝሃብ ታላቁ ሙፍቲ ናቸው ይባላሉ)፣ ሸይክ ናጂ አል-ዐረቢ (በባህሬይን የማሊኪ ሙፍቲ ናቸው)፣ ሸይክ አብዱልሐሚድ አዓለ ሙባረክ (በሳዑዲ ዐረቢያ የአህስአዓ ክልል ቁልፍ የማሊኪ መዝሃብ ዓሊም ናቸው) ይጠቃለላሉ፡፡

Пікірлер: 1
@endobrindo
@endobrindo 3 ай бұрын
ድንቅ ቪዲዮ 😊👌 ሰውዬው ከሙፍቲ የበለጠ አድክም ናቸው 😅
ቤዛ በጓደኞቿ ሰርፕራይዝ ሆነች Baby shower
8:18
Beza & Seife (ቤዛ እና ሰይፈ)
Рет қаралды 19 М.
БЕЛКА СЬЕЛА КОТЕНКА?#cat
00:13
Лайки Like
Рет қаралды 2,2 МЛН
LIFEHACK😳 Rate our backpacks 1-10 😜🔥🎒
00:13
Diana Belitskay
Рет қаралды 3,9 МЛН
Players vs Corner Flags 🤯
00:28
LE FOOT EN VIDÉO
Рет қаралды 67 МЛН
Zıkr - Salawat 1000  times
1:45:35
Nashid Records
Рет қаралды 6 МЛН