Рет қаралды 2,075
በልጅነት ካገር ወጥቼ
ስኖር ከ እናቴ ተለይቼ
ስንገላታ ብይን ናፍቆት
ህልም ነው ወይ ቅዥት የምሰማው በድንገት
ህልም ነው ወይ ቅዥት የሚነግሩኝ በድንገት
እንዴት አድርጌ ልመናቸው
አይን አይናቸውን እያየኃቸው
አይዞህ ብለው እያጽናኑኝ
እንባየ አልፈስ አለ እንዴት አርጎ እሽ ይበለኝ
እንባየ አልፈስ አለ እንዴት አምኖ እሽ ይበለኝ
ሳልከፍለው ውለታሽን የ ዘጠኝ ወር ጭንቅሽን
ሄደች አሉኝ ሳልሸኛት ዳግም ላላያት
አምላኬን አላማርርም ያለ ነው በዚህች ምድር
ይከብዳል በሰው ሃገር የ ማምየ ነገር
እማምየ እማምየ የኔ አለኝታ
ስናፍቅሽ ስናፍቅሽ ጥዋት ማታ
የ ማስብሽ የማስብሽ ጥዋት ማታ
የንግስቶች ንግስት ነሽ
ከ አምላክ በታች የማይሽ
ከቶ እንዳንች በዚህች አለም
ማንም አይደርስብሽ እማምየ ለዘላለም
እግዜር ብሎት ከሃገር ስገባ
ሳጣሽ ከቤቱ ሆዴ ባባ
ፈሰሰ እንባየ እንደ ጅረት
አይሞቅም አይደምቅም ቤትና ሃገር ያለ እናት
የ ትብዕቴ የደም ውርስ ነሽ
እማምየ በምድር አንድ ነሽ
ዘጠኝ ወር ተሸክመሽ ወለድሽኝ እህህህ ብለሽ
አንድ ነው የኔስ ምኞቴ
ከሰማው የኔን ጸሎት
አምላኬ ነብስሽን ምሮ ያኑርሽ ከገነት