Рет қаралды 61,893
ፍትህ የፍርድ ቤትና የፍትህ ተቋማት ጉዳይ ብቻ አይደለም። ፍትህና ምህረት ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል/ይፈለጋል - ፍትሀዊ ሳንሆን ፍትህን መፈለግ ግብዝነት ነው። ፍትህና ምህረት የአንድ ክርስቲያን የዕለት ተዕለት ኑሮው ነው። ፍትህ በየስፍራው ትፈለጋለች። ስንምር እናበላለን፣ ስንምር እናለብሳለን፣ ስንምር እንራራለን - እናም እንማራለን። ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዲል መፅሀፍ ይህ የዝማሬ መልዕክት የማይደርሳቸው ፍትህና ፍቅር ግን የናፈቃቸው ብዙ ናቸው።
ፍትሁንም/ፍቅሩንም መዝሙሩንም እናካፍላቸው።
ሁላችሁም እንድታደምጡት፣ ራሳችሁንም 'ቻሌንጅ' እንድታደርጉ በአክብሮት የቀረበ!
#challenge
እነሆ ቃላቱን!
ፍትህን ላድርግ ምህረትን ልውደድ
እርዳኝ አምላኬ ካንተ ጋር በትህትና ልሂድ
ፈቃድህን ላገልግል በሰጠኸኝ ዕድሜ
የሰማዩ ሃሳብህ አይቁም በድካሜ
ለተጠቃው ልድረስ ድምፁ በኔ ይሰማ
የላላውን ላበርታ የጎበጠን ላቅና
ልጋፈጥ ካንበሳ ከፊቱ ቀድሜ
ይሰማኝ ጥቃቱ ህመሙም ህመሜ
ይሄ ችግረኛ አብዝቶ ይጮሃል
አምላኩ እግዚአብሄር ግን ከሰማይ ሰምቶታል
ዘምሬ ሰብኬ ላንቃዬ ተላቋል
ብዙ ጨፍሬያለሁ ለካስ ልቤም ወልቋል
መች አጣህ ዝማሬ ጭፈራስ መች ጎድሎ
ልብህን የሰበረው የድሀው ልጅ ውሎ
መቼ አስደሰተህ መስዋዕትስ በዝቶ
ችግረኛውን መስማት ወደኋላ ቀርቶ
የቀረኝን ዕድሜ ለኔ ብቻ አታርገው
ልብህን የሰበረው የኔንም ይስበረው
ለሆዱ እንጀራ ለስጋው ልብስ አጥቶ
አብሮኝ ይዘምራል ከመቅደስህ ገብቶ
የቅንጦት ኑሮዬን ወደኋላ ትቼ
ልመልከት ግራ ቀኝ እህት ወንድሞቼን
የፀሎታቸው መልስ ልሁን ልቆረስ
የራበውን አብልቼ ራቁቱን ላልብስ
ከሰጠኸኝ ልሰጥ ገብቶኛል ስሌቱ
አላጣም አልጎድልም ብዙ ነው ውጤቱ
በርሱ ኖራለሁ ስል ስገበዝ በፅድቄ
ማድረጉ ተስኖኝ መልካሙን አውቄ
ወድቆ በተገኘ ባልንጀራ ስቄ
አልፌ እንዳልሄድ አንገቴን ነቅንቄ
ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እንድጠይቅ
ድሃ አደግ ባልቴቱን አይቼ እንዳልንቅ
ታዝዣለሁና እንዲህም ላምልከው
ቅዱስ መስዋዕቴ እርሱን ደስ ያሰኘው
በሰዎች በመላዕክት ልሳን ብናገር
እንደሚጮህ ናስ ነኝ የሌለኝ ፍቅር
ትንቢት ምስጢር ዕውቀት እምነት ቢኖረኝ
ሁሉ ያለፍቅር ከቶ አይጠቅመኝ
ስጋዬ ቢቃጠል ከእሳት መሃል አድሮ
ለድሆች ቢታደል ያለኝ ተመንዝሮ
ርህራሄ ምህረት ፍቅር ከጎደለኝ
ለሌላው ብጠቅም ለራሴ ባዶ ነኝ