🔴[NEW] ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ || በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ-Deacon Henok Haile

  Đ ĐľŃ‚ қаралды 73,506

አርጋኖን-Arganon

አርጋኖን-Arganon

Күн бұрын

+ በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ +
ይድረስ ለተከፋኸው ወንድሜ
መኖር ለደከመህ ፣ ሕይወት ለታከተህ ፣ የሚሰማህ ላጣኸው ፣ የሚረዳህ ሰው ላላገኘኸው መከረኛው ወዳጄ!
ከሞት ውጪ ሌላ መፍትሔ አልታይ ካለህ የአንተ ቢጤ መከረኞቹ ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ ሆነው እንዲህ ይሉሃል::
"በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" ሐዋ. 16:28
አውቃለሁ ዙሪያው ገደል ሆኖብሃል:: ምነው ባልተፈጠርሁ እስክትል ድረስ ተጨንቀሃል::
ግን ይህ ስሜት በአንተ አልተጀመረም:: ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ኑሮ ያልመረረው ማን አለ? መሞት ያልተመኘስ ማን አለ?
ሞት ያማረህ አንተን ብቻ መሰለህ?
" ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዓይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ" ያለውን ጻድቅ ኢዮብ አልሰማህም? (ኢዮ. 10:18)
"ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ" ብሎ እንዲሞት የለመነውን ኤልያስን አላየኸውም? 1ነገሥ. 19:4
ዮናስንስ "አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ፡ አለው" ሲል አልሰማኸውም? (ዮናስ 4:3)
ወንድሜ እመነኝ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መኖር ያላስጠላው ሰው በታሪክ ፈልገህ አታገኝም::
ሞት ሞት የሸተተው ልቡ የተሰበረ ብዙ ነው:: አንተ ላይ ብቻ የደረሰ ልዩ ፈተና የለም:: "ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል" ይላል መጽሐፍ:: 1ኛ ቆሮ. 10:13
ምናልባት የልብህን መሰበር የኀዘንህን ጥልቀት አይቶ ምቹ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ራስህን እንድትጎዳ ሰይጣን ሊገፋፋህ ይችላል:: እንዴት እንዲህ ዓይነት ሃሳብ በልቤ ሊመጣ ቻለ ብለህ አትረበሽ:: ሰይጣን ይህንን ክፉ ሃሳብ ላንተ ብቻ ሳይሆን ለክርስቶስም አቅርቦለታል::
"የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር" ብሎ ክርስቶስን እንኳን [ማንነቱን ሳያውቅ] ራሱን እንዲወረውር ሊገፋፋው የሞከረ ደፋር ነው:: የእግዚአብሔር ልጅ የሆነ ሰው ግን ራሱን አይጎዳም:: "ጌታ አምላክህን አትፈታተነው" "ሒድ አንተ ሰይጣን" ብለህ ሰይጣንን ገሠፀው::
ሰይጣን ክርስቶስን "ከሕንፃ ጫፍ በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን አሳይ" ሲለው ክርስቶስ ሰይጣንን ሒድልኝ ብሎ በመገሠጹ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጎ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ::
ወንድሜ ሆይ አንተም ሰይጣንን አትስማው ሃሳቡ ራስህን ጎድተህ ከፈጣሪህ እንድትጣላ ሊያደርግህ ነው:: ሰይጣንን ከገሠጽከው በእግዚአብሔር ቀኝ ከበጎቹ ጋር ትቆማለህ::
አሁን ያለህበት ችግር ያልፋል:: የሚሰማህ ክፉ ስሜት መቼም የማይለወጥ አይምሰልህ:: ኀዘኑም ፣ ብቸኝነቱም ፣ ተስፋ ቢስነቱም ያልፋል:: ጨለማው ይነጋል:: የተዘጋው በር ይከፈታል:: ችግሩ ሲፈታ አንተ ከሌለህ ግን ትርጉም የለውም::
ስለዚህ ለሚፈታ ችግር የማይቀለበስ ውሳኔ አትወስን:: ራስን ማጥፋት ከጊዜያዊ ችግር ለመሸሽ ሲሉ ዘላቂ ችግር ውስጥ መግባት ነው:: ጊዜያዊ ሕመምን ለማስታገስ የዘላለም ሕመምን ለምን ትመርጣለህ? "የሞተ ተገላገለ" ሲሉ ሰምተህ እንዳትታለል ሞት ዕረፍት የሚሆነው ራሱ እግዚአብሔር ሲጠራህ ብቻ ነው::
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ" ያለው ጌታ ሳይጠራህ ራስን ማጥፋት የዘላለም ስቃይ ያመጣል::
ወዳጄ "በራስህ አንዳች ክፉ አታድርግ"
የሕይወትህን ዋጋ ታውቅ ይሆን? አንተ እኮ የእግዚአብሔር ልጅ ለአንተ ሲል የሞተልህ ነህ:: ሊፈውስህ የቆሰለ ፣ ሊያከብርህ የተዋረደ ፣ ሊያረካህ የተጠማ ፣ ሊያለብስህ የተራቆተ ለአንተ እኮ ነው::
ክርስቶስ ስለ አንተ ሞቶአል:: አንተን ግን የጠየቀህ እንድትሞትለት ሳይሆን እንድትኖርለት ነው::
ለሞተልህ አምላክ እንዴት መኖር ያቅትሃል?
ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው:: አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም:: "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል
ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል:: ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ::
"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" 1ኛ ቆሮ. 3:17
ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን?
"አሳያቸዋለሁ ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ:: እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም:: ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም:: ፈጥነውም ይረሱሃል:: ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን:: ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ቁጥር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል :: እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም::
እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም:: አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል:: በምሳሌ ልንገርህ :-
ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ:: ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው:: አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች:: እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ::
ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል:: ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል:: በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍ ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል:: እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም::
"ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም:: ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል:: "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. 18:32
የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም:: ራሱን መግደሉ ነው:: እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው::
ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው:: ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም:: በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ:: አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም:: በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"
"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. 16:27-28
ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው::
ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው?
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"
መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::
ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::
ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::
ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-
"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ

Пікірлер: 141
@habtamunigussie
@habtamunigussie 10 ай бұрын
ይህንን ፅሑፍ ካነበብኩት በኃላ እና አሁን ደግሞ ስሰማው የበለጠ ተፅናናው ፣ ከመጥፎ ስሜቴ ወጣው። ተመስገን አምላኬ።
@etalembekele8831
@etalembekele8831 10 ай бұрын
ተመስገን
@tarikuaengida1131
@tarikuaengida1131 10 ай бұрын
እንኳን እግዚአብሔር አወጣሽ ብዙ የባዘነች ነፍስ አለች ምናለ ወደዚህ ጎራ ብላ ብታርፍ በንፁ ቃሉ❤❤❤
@hayatresto2302
@hayatresto2302 10 ай бұрын
አሜን እግዚአብሔር ይመስገን
@joseyetesfsh6792
@joseyetesfsh6792 10 ай бұрын
የመፅሐፉ ስም ምንድነዉ
@tarikuaengida1131
@tarikuaengida1131 10 ай бұрын
@@joseyetesfsh6792 ስም የለውም እኮ መፅሀፍ አይደለም አርጋኖ ላይ ነው ያጋራው መምህር ዲያቆን ሄኖክ
@Agenda-2016
@Agenda-2016 10 ай бұрын
እንዲህ በእናንተ አድሮ ህይወት የሚሰጥ ቃሉን እንድንሰማ ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን ። ቃለህይወት ያሰማልን።
@meherat938
@meherat938 10 ай бұрын
የዕዮብን ትእግስት ለሁላችንም ያድለን ምንም ፈተና ቢገጥመን የቅዱስ ዕዮብ አምላክ የእኛም አምላክ ነው እኔ ግን ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለው!!! ቃለ ሕይወት ያሰማልን
@calltech5706
@calltech5706 10 ай бұрын
አሜን
@naajanojaa7
@naajanojaa7 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ልቤ ተረጋጋ መኖር ታክቶኘ ነበር ኑሮየ ታደሰ
@tsega1200
@tsega1200 10 ай бұрын
አሜን ቃለ ህይወት ያሰማልን❤❤❤
@etalembekele8831
@etalembekele8831 10 ай бұрын
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏ለሁላችን የሰላም አምላክ ሰላሙን ይስጠን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Natiye23
@Natiye23 7 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን የተሰበረውን ልብ ቸሩ መድሃኒዓለም 💝🙏☦️🕊 ልብ ያሰበሩኩ ይቅር በላኝ 😢 ይቅር እንድሉ ልቦና ይሰጧቸው 🙏🥰💐
@seblekahsay6417
@seblekahsay6417 10 ай бұрын
ትክክለኛ ፅሑፍ በትክክለኛው ወቅት ቃለ ህይወትን ያሰማልን::
@SerkalemAklik
@SerkalemAklik 10 ай бұрын
እባካችሁ ሼር አርጉት ለብዙዎች ይድረስ ቃለ ህይወትን ያሰማልን በእዉነት😢
@user-yr8qp6zw6k
@user-yr8qp6zw6k 8 ай бұрын
AMEN AMEN AMEN ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@helen37993
@helen37993 10 ай бұрын
ቃለ ሂወት ያሰማልን ለንሰሀ ሞት ያብቃን
@ccvcf7964
@ccvcf7964 4 ай бұрын
ቃለሄወት ያሰማልን ❤
@yalemworkAtalel-ok7wg
@yalemworkAtalel-ok7wg 8 ай бұрын
አሜን❤❤❤❤❤❤❤❤
@user-dk2qr6wz7r
@user-dk2qr6wz7r 10 ай бұрын
ቸሩመድሀኒአለም.ከአሳሳች.ከሰይጣን.ዳቢሎስ.ሁላችንም.በምህረቱ.ይጠብቀን.ለአስተማራችሁን.ለገሰፃችሁን.አባቶቻችን.ቃለህይወትያሠማልን.ለእኛም.ለአዳመጥነው.ቃሉተግባሪያድርገን.አሜን፫🙏
@birhaneshetugashaw9852
@birhaneshetugashaw9852 10 ай бұрын
እናመሰግናለን
@user-ih1bd6lc3p
@user-ih1bd6lc3p 4 ай бұрын
ፍቅርነዉእግዚአብሄርለኔምንያልሆነዉአለአምላካችን
@BirkieSitotaw-ko2vc
@BirkieSitotaw-ko2vc 10 ай бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን
@TeketeleLerago
@TeketeleLerago 4 ай бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን ወንድማችን❤
@mihretsisay9347
@mihretsisay9347 10 ай бұрын
ቸሩ መድኃኔዓለም እሚጠላው ሀፅያትን ብቻ ነው እና በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እምንሰራውን ሀፅያት በንስሀ እያሶገድን በማስተዋል ፅድቁን መንግስቱን እንድናስብ ይርዳን
@kedstdanikedstdani7592
@kedstdanikedstdani7592 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን
@askalemariyam8253
@askalemariyam8253 10 ай бұрын
Kale hiwotn yesrmaln memeherachn🤲💒🤲🙏🏻🙏🏻🙏🏻
@SenaitTilahun-zk6il
@SenaitTilahun-zk6il 8 ай бұрын
ቃለሂወትያሠማልን🙏🙏🙏ለንሠሀሞትያብቃን
@17media-516
@17media-516 10 ай бұрын
ለጻፈም ላነበበም ቃለ ሕይወት ያሰማልን..
@bizualemtefera3038
@bizualemtefera3038 10 ай бұрын
አምላከ ዕዮብ ትእግስትን ስጠኝ!!!
@user-dl8bs5pl2e
@user-dl8bs5pl2e 10 ай бұрын
እናመሰኛልን
@mekdelawittariku7211
@mekdelawittariku7211 10 ай бұрын
Egziabher yakbrln memhrachn ketay demo orthodox honew yelela emnet mezmur lemisemut ena lk new blew lemiyasbu wendmna ehtoch tmrt bisetln
@user-ch3yc9vp8c
@user-ch3yc9vp8c 10 ай бұрын
ማን ነበር በተከፋሁ ጊዜ ባላሻሁ ለመኖር 😢ሀዘን ሲበዛብኝ ወዳጅ ኋላ ሲቀር የመንገዴ መሪ የመኖሬ ተስፋ ክርስቶስ እያለ ስለምን ልከፋ
@HasetGanta
@HasetGanta 10 ай бұрын
ቃለህወይት ያሰማልን😴
@talakituaethiopia1119
@talakituaethiopia1119 10 ай бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን በጣም ግዜውን የጠበቀ የተሰበረው የትውልዱን ልብ የሚጠግን የሚታደግ ነው አስፈላጊ ትምህርት ነው ዲያቆን ሄኖክ እና ዲያቆን ክሳቴብርኃን እድሜ እና ጤና ይስጥልን❤💒❤
@kidusanabew12
@kidusanabew12 10 ай бұрын
ቃል ሂወት የስምዓልና❤❤
@Haregi849
@Haregi849 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን ወንድማችን❤
@selamtadesse6872
@selamtadesse6872 10 ай бұрын
ደስ የሚል መልክትም ትምህርትም ነው ልብ ካለን እናስተውል ፈጣሪ ሁሌም አብሮን ነውና ሁሉም ያልፋል እንበል እናመስግናለን
@zewduaddisu7966
@zewduaddisu7966 9 ай бұрын
አሜን ✝️ አሜን ✝️ አሜን ✝️+✝️ አባታችን አሜን ቃለ ሂወትን ያስማልን አባታችን ተመስገን አወ እወነትነው አመላኬ ✝️ አመላኬ አቤቱ አመላኬ ተመስገን ሁሌም ተመስገን ጌታይ ለዘላለሙ አሜን ✝️⛪️⛪️⛪️✝️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🙏✝️✅
@rahelalamerew6369
@rahelalamerew6369 10 ай бұрын
ድንቅ የሆነ ቁምነገር ያለው መልክት ነው እና ወንድም እህቶቼ በጭራሽ ተስፋ እዳትቆርጡ ወዶ እና በአምሳሉ የፈጠረን አምላክ መቼም አይተወንም እና ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችው🙏
@user-pi1xp9ch7m
@user-pi1xp9ch7m 10 ай бұрын
i love you
@FiraBeke-nf7nc
@FiraBeke-nf7nc 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ይስጥህ።
@tayekafisseha2254
@tayekafisseha2254 10 ай бұрын
Tebekeh nber tenagereken Memeher enamesegenalen
@user-rc3kl5is6w
@user-rc3kl5is6w 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለ ህይወትን ያሰማልን ጸጋውን ያብዛልን የሰማነውን በልቦናችን ያኑርልን ለመምህራናቻችን
@sabadessalegn4090
@sabadessalegn4090 10 ай бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን
@Musiclayricbyribka
@Musiclayricbyribka 10 ай бұрын
Why am I crying 😢
@surafelhabte
@surafelhabte 10 ай бұрын
በተስፋ ደስ ይበላችሁ መከራን ታገሱ በፀሎት ፅኑ ሮሜ 12:12 ቃለህይወት ያሠማልን መምህራችን ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውሮ በቤቱ ያቆይልን
@coffeerelax3455
@coffeerelax3455 10 ай бұрын
kale hiwot yasemalin
@yapiweekend4523
@yapiweekend4523 10 ай бұрын
Amesegnalew 🙏
@marytheegyptian
@marytheegyptian 10 ай бұрын
ካነበብክልን ሁሉ "አባትህ ነውና ከምትሞት ከነ ኃጢአትህ እንኳን እንድትኖር ነው የሚፈልገው" ያልከው ሳላስበው አስለቀሰኝ ...በዚህ ክፉ ዘመን ላይ ውድ ወንድሞቻችን እንዲኖሩልን አንተ ውድ ወንድማችን በርታልን ቃለ ሕይወት ያሰማልን በረከቱን ይስጥህ 💖💖💖🌹🌹🙏🙏
@user-ml7hg6bk3l
@user-ml7hg6bk3l 10 ай бұрын
ቃልህይወቴ ያሰማለን ወንደማችን ❤❤❤
@eyerussurur9363
@eyerussurur9363 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን! ረጅም የአገልግሎት ዘመን ያድልልን
@atsede7592
@atsede7592 10 ай бұрын
Kalhiwoten yasemalen
@tigistshimeles7
@tigistshimeles7 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያስማለን
@user-mg5xl1vc7o
@user-mg5xl1vc7o 10 ай бұрын
ቃለ ሂወት ያሰማልን ወንድሜ
@SaraSara-rl6pd
@SaraSara-rl6pd 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን አሜን
@Godislove727
@Godislove727 10 ай бұрын
❤️‍🔥God is good❤️‍🔥
@TadiyosGetnet
@TadiyosGetnet 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን
@shetamenesh8833
@shetamenesh8833 10 ай бұрын
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ጸጋውን ያብዛልህ መምህራችን❤❤❤
@user-uu2un1sm7c
@user-uu2un1sm7c 9 ай бұрын
❤❤❤❤ተዋህዶዬ
@user-qx9qh2ib5h
@user-qx9qh2ib5h 10 ай бұрын
እግዚአብሔር መልካም ቀን ይጨምርልን
@abeybawe
@abeybawe 6 ай бұрын
This is so beautiful, thank you.
@tarikuaengida1131
@tarikuaengida1131 10 ай бұрын
በፁፍ አንብበው እጅጉን ደስስስ ብሎኝ ነበር አሁን ደግሞ በትረካ ስሰማው ነፍስን ያለመልማል ያለካል ለፃፊው ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ያድልልን ለተራኪው ቃለ ህይወትን በህድሜ በፀጋ ያቆይልን ❤❤❤❤❤❤❤
@yetariksewyetariksew6709
@yetariksewyetariksew6709 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለሕይወት ያሰማልን
@user-nc3om7qy5o
@user-nc3om7qy5o 10 ай бұрын
ወይ ደቅ ትህምርት ነዉ
@user-tq6qm5xe7c
@user-tq6qm5xe7c 10 ай бұрын
ቃለህይወት ያሠማልን በዝህዘመን አሥፈለጌቃልነዉ እግዚአብሔር በቸርነቱ ምህረቱን ይሥጠን የኛእንቁመምህር❤❤❤⛪️⛪️🙏🙏🙏🙏
@user-tu6zu6wj5p
@user-tu6zu6wj5p 10 ай бұрын
Amen Amen Amen ❤❤❤🙏🙏🙏
@user-zo1zt5vm1n
@user-zo1zt5vm1n 10 ай бұрын
ላነበብከውም ለጻፍከውም እግዚአብሔር ያክብርልን
@assilaselefechbedeke3292
@assilaselefechbedeke3292 10 ай бұрын
Amen Amen Amen KALE Hiwotin Yasemalen wondimachin 💒💒💒🌻🌻🌻🙏🙏🙏
@naajanojaa7
@naajanojaa7 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን❤
@user-qn1kx2wm1q
@user-qn1kx2wm1q 10 ай бұрын
ውድ መምህራችን ቃለ-ህይወት ያሰማልን... ሁሌም ቢሆን የበላያችንን ሳይሆን የበታቾቻችንን እያየን ባለን ነገር ተመስገን እንበል በተለይ ንፁህ አየር መተንፈስ ከቻልን፣ ቆመን የፈለግንበት ቦታ መሄድ ከቻልን፣ በራሳችን መመገብ መፀዳዳት ከቻልን፣ ካለ ህመም ማስታገሻ መድሀኒት መተኛት እና መነሳት ከቻል ከዚህም በላይ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ከቻልን ታድያ እንዴት እግዚአብሔርን እያመሰገንን መኖር ያቅተናል ካጣነው ይልቅ ያለን እጅግ ብዙ ነው እና ሁል ጊዜ በየሴኮንዱም ክብርና ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን እንበል
@mihretsisay9347
@mihretsisay9347 10 ай бұрын
እውነት ነው እግዚአብሔር የሰጠንን ዕድሜ እና የመኖር ዕድል በአግባቡ እንድንጠቀም የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ማስተዋሉንም ጥበቡንም ያድለን ይክበር ይመስገን❤❤❤
@kiyayeasellawatube4721
@kiyayeasellawatube4721 10 ай бұрын
Egziabher yemesegen Uffffff nefesi arefechi leka seleq bezu adekemit neber benet adero yeregegegn amelek yemesegen 😢😢😢😭😭😭 Kelehiwoten yesemelen 🤲🤲
@yezinamulumengsit771
@yezinamulumengsit771 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ጌታ ሆን በእምነታችን አፅናና ቃለ ህይወት ያሰማልን❤❤❤❤❤
@hanatamrat6967
@hanatamrat6967 10 ай бұрын
😢😢😢😢😢😢
@kegetahun3445
@kegetahun3445 10 ай бұрын
በእውነት ቃለህይወት ያሰማልን አሜን አምላካችን ለአባቶቻችን ትግስት ጥበብ ማስተዋል ያደላቸውን ለእኛም ለደካሞቹ ልጆቹ አሜን❤🙏🌾🌻👏
@ltilahun
@ltilahun 10 ай бұрын
🙏🏽🙏🏽🙏🏽
@jemayenshreta8146
@jemayenshreta8146 9 ай бұрын
ቃለሂወት ያሰማልን መምህራችን ፀጋን ይስጥልን አምላክ ከክፉ ሃሳብ ይጠብቀን አመቤቴም ልጆቿን አሳልፋ አትስጥ አሜን!!
@Dare_smart_tube
@Dare_smart_tube 10 ай бұрын
በትክክለኛው ሰዓት የደረሰ መልዕክት ቃለ ህይወት ያሰማልን
@helenbaryagabr9964
@helenbaryagabr9964 10 ай бұрын
ናይ ብሓቂ ማሃሪ ጹሑፍ እግዝኣብሄር ኣብዚሑ ይባርካ ንኣንባቢን ንጽሓፊ ድያቆን ሄኖክ ጸጋ ጥዕና ይሃብኩም
@mekdestesfaye5647
@mekdestesfaye5647 10 ай бұрын
መምህራችን ቃለህይወትን ያሰማልን አሜን አይዞን ወገኖቼ ሁሉም ያልፋል 🙏🏾🙏🏾🙏🏾🤲🏽🤲🏽🤲🏽
@Astela-bh1ei
@Astela-bh1ei 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ልቦና ይስጠን ቃለህይወትን ያሠማልን
@sisayineshikase5859
@sisayineshikase5859 10 ай бұрын
🤲🤲🤲
@choosengeneration2470
@choosengeneration2470 10 ай бұрын
Egziabher abzuto tsegawun yabzalih.
@bisratberhane4457
@bisratberhane4457 10 ай бұрын
Ewneten edmena tena yesteh tbark
@astermekuanint6713
@astermekuanint6713 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወትን ያሰማልን
@ednaabel4465
@ednaabel4465 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን መካሪ ወንድም አያሳጣን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@berktizersenay2298
@berktizersenay2298 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ቃለሕይወት ያሰማቹ ፃሐፌም አንባቢም በጣም የሚያበረጣ የሚያፅናና ቃል ነው እግዚአብሔር ፀጋውን አብዝቶ በቤቱ ያፅናቹ 🙏🙏🙏
@almaz8petros75
@almaz8petros75 10 ай бұрын
Ledge lenbab kalhwet yasmanl
@user-sn2jn1jg3t
@user-sn2jn1jg3t 10 ай бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን በእውነት ጥሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው ተባረኩ
@ይኩነኒ
@ይኩነኒ 10 ай бұрын
የሕይወትን ቃል ያሰማልን
@marthachane9777
@marthachane9777 10 ай бұрын
እግዚአብሄር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ መምህር ሔኖክ ሐይሌ
@ayinalem5002
@ayinalem5002 10 ай бұрын
ቃለሒወትን ያሰማልን🙏🙏🙏
@Musse-bx9me
@Musse-bx9me 10 ай бұрын
Amen Amen Amen qale hiwet yasemaln
@kalaebhailu6232
@kalaebhailu6232 10 ай бұрын
Kalehiwet yasemalin❤
@ethiopianfoods8038
@ethiopianfoods8038 10 ай бұрын
አሜን አሜን አሜን
@eskenderamare9515
@eskenderamare9515 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏
@ganiifichee8412
@ganiifichee8412 10 ай бұрын
Kale hiwot yasemalen 😢❤❤❤
@hanamarhayle
@hanamarhayle 2 ай бұрын
❤❤❤
@tg-wf7sy
@tg-wf7sy 10 ай бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን ከጸሐፊው አንባቢው አመሰግናለሁ አድማጮ ያስታውል
@selamawitadugna5671
@selamawitadugna5671 10 ай бұрын
Enamesgenalen memhir. Fetenaw yesega newena begzihabher kal yabertan. Amen.
@kidistdibekulu4019
@kidistdibekulu4019 10 ай бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን ፀጋውን ያብዛልህ🙏
@luwamberhane3956
@luwamberhane3956 10 ай бұрын
Amen 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 🙏 fitari yebarkh kale Hewet yasemalen wendeme .
@user-ih1bd6lc3p
@user-ih1bd6lc3p 4 ай бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
@ensratube
@ensratube 10 ай бұрын
እውነት ነው ቃለሕይወት ያሰማልን 😢
@Sekim_seminesh_Kidanemhret
@Sekim_seminesh_Kidanemhret 10 ай бұрын
እግዚአብሔር ያክብርልኝ 🙏❤
@user-ih1bd6lc3p
@user-ih1bd6lc3p 4 ай бұрын
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤
مسبح السرير #قصير
00:19
سكتشات وحعكات
Рет қаралды 11 МЛН
I Took a LUNCHBAR OFF A Poster 🤯 #shorts
00:17
Wian
Рет қаралды 16 МЛН
У ГОРДЕЯ ПОЖАР в ОФИСЕ!
01:01
Дима Гордей
Рет қаралды 7 МЛН
Throwing Swords From My Blue Cybertruck
00:32
Mini Katana
Рет қаралды 11 МЛН
🔴ትሑት ልቦና [NEW VIDEO] ||  ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
20:56
አርጋኖን-Arganon
Рет қаралды 406 М.
10 ጥያቄዎች ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጋር
43:40
አርጋኖን-Arganon
Рет қаралды 192 М.
مسبح السرير #قصير
00:19
سكتشات وحعكات
Рет қаралды 11 МЛН