Рет қаралды 244,645
የዝማሬው ግጥም እነሆ...
📖መሰንቆዬን በአሃያ ዛፎች ላይ ሰቅዬ
የእንቢልታዬ ቅኝት ዜማው ቀርቶ ከኌላዬ
በአደባባዩ በደርቡ ዜማዬ ባይወጣ
ቢታቀብ አንደበቴ ቃል ከአፌ ሲታጣ
የምስጋናን ቃል የፈለጉብኝ
አመስግን እንጂ ዘምር ቢሉኝ
ልቤ ተነሳ ሊያዜምልህ
ቅኔዬ ነቃ እንዲህ ሊልህ🗣
🌎ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🌅
🌌አንተ አይደለህም ወይ የኪዳን ሃገሬ
ሞት እንዳያገኘኝ ከለላ የሆንኸኝ የሕይወት ድንበሬ
አንተ አይደለህም ወይ ያዘመትኸኝ መሪ
በጸናች እጅ እና በተዘረጋች ክንድ ሆነህ ፊት አውራሪ
አንተ አይደለህም ወይ እንዴት ይዘነጋል
ውለታህ ልቤ ውስጥ ዘለአለም ላይጠፋ በጣትህ ተፅፏል✒️
🌏ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🏞
🌄ክንድህ አይደለም ወይ ትላንቴን የረታ
ዛሬን የሚያኖረኝ የነገ ተስፋዬ የነፍሴ መከታ
እጅህ አይደለም ወይ ያጎረሰኝ ቆርሶ
ያጠጣኝ ስጠማ ከልዑላን ማዕድ በክብር አቋድሶ
እጅህ አይደለም ወይ ያከመኝ ታምሜ
አቅፎ ያባበለኝ እንባዬን ያበሰው ጣትህ ነው ሰላሜ 🌅
🌎ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🏞
🎙አንተ እኮ ነህ ጌታ የዜማዬ ቃና
የቃላቴ ሞገስ የስብከቴ ርዕስ የንግግሬ አርማ
አንተ እኮ ነህ ጌታ የልጅነት ሕልሜ
የጉብዝና ሃሳቤ የምኞቴ አልፋ ርስቴ አለሜ
በአንተ እኮ ነው ጌታ መሻገር መትረፌ
የጭንቄን ማለዳ የእንባዬን ሌሊቶች የቆምኩት አልፌ🌅
🌏ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ
ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ
ገነቴ ነህ መኖሪያዬ🌅
🌎ላምጣ በገናዬን መወድሱን ላንሳ
የልሳኔን ጩኸት ሳልገድብ ሳልሳሳ
ታጥቄያለሁ ቅኔ ስምህ ነው ዜማዬ
ለክብርህ እኖራለሁ መዝሙር ነው ስራዬ
ዜማን በልቤ አርገህ ፈጥረኸኛልና
ማምለክ ነው ስራዬ አንተን በምስጋና 🗣
🙏 ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና
ኸረ እኔስ አለኝ ምስጋና ለሕይወቴ ጀግና
ቀኜ ትርሳኝ ብረሳህ ምላሴ ይጣበቅ ባላስብህ
የምወድህ ደስታዬ ገነቴ ነህ መኖሪያዬ📖
ግጥም እና ዜማ ዲያቆን ሐዋዝ ተገኝ