Рет қаралды 52,000
የራሴን የነጋ ጠዋት አጣኹ፥ በሰው በነጋ ጠዋት ውስጥ እባዝናለሁ። "ሄሎ ነይ እስቲ የሆነ ቦታ ልንሄድ እኮ ካሉኝ" የራሴን ጠዋት ትቼ በሰው የጠዋት ፀሐይ ልሞቅ እኳትናለሁ። ራሴን ገዝቼ መምራት ተሳነኝ ምን ላድርግ? እስከ መቼ ?
መኪና ጎማ ብቻ ሳይሆን ማብረጃ ፍሬን አለው፥ ማብረጃ ባይኖረው መኪና አደጋ ብቻ ይሆን ነበረ። ፈረስ ልጓም መኪናም ፍሬን አለው። ሰውም ራሱን የሚቆጣጠርበት ትዕግሥት ሊኖረው ይገባል የኔ ተወዳጆች ራስን መግዛት ይባላል ሃሳቡ። ይገባኛል መግዛትና መሸጥ የሚባሉ ቃላት የገበያ ቋንቋ ናቸው፥ ግን ሰው ንብረቱን ሊሸጥ ይችላል ራሱን ግን መግዛት ነው ያለበት። ራስ አይሸጥም አይለወጥምና። የተሸጠን ነገር የገዛው ሰው እንደ ፍላጎቱ ይጠቀምበታል። ራስን አለመግዛት ፍጻሜው ይህ ነው። ገዝተውናልና እንዳሻቸው ይጠቀሙናል።