Рет қаралды 25,504
ክፍል 2 👉 • ሾተላዩ ሰላይ | ክፍል 2
ደራሲ ማሞ ውድነህ
አቶ ማሞ ውድነህ ጥቅምት 12 ቀን 1923 ዓ.ም በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሃገር በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ከአባታቸው አቶ ውድነህ ተፈሪና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ ተወለዱ;; በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ጊዜ ወላጆቻቸውን አጥተዋል። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በ 15 አመታቸው የጀመሩት አቶ ማሞ በተለያዩ ችግሮች ምክኒያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መጨረስ ባይችሉም በአዲስ አበባ እና አስመራ ውስጥ የሚታተሙ ፖሊስ እና እርምጃው፣ህብረት እና የዛሬይቱ ኢትዮጲያ የተሰኙ ጋዜጦች ውስጥ አገልግለዋል።
አቶ ማሞ ውድነህ የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ለ12 አመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ነበሩ ። በአቡነ ጳውሎስ በሚመራው የሃይማኖት ኮሚቴ ውስጥ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን ለማምጣት ጥረት ካደረጉ ሰዎችም አንዱ ነበሩ። የ54 መጻህፍት ደራሲና ተርጓሚ የነበሩት አቶ ማሞ በማስታወቂያ ሚኒሰቴር ስር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በጋዜጠኝነት የሰሩ ሲሆን የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ መስራችና ተባባሪ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆነዉ በተመደቡበት የጋዜጠኝነትና የፖለቲካ ስራ በተጨማሪ ህብረት በተሰኘዉ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዘገባዎችና ትንታኔዎች ያቀርቡ ነበር።
አቶ ማሞ ከባለቤታቸዉ ወይዘሮ አልማዝ ገብሩ 06 ልጆችና 10 የልጅ ልጆችን አፍርተዋል፡፡
አቶ ማሞ ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸዉን ሲከታተሉ የነበሩት ሲሆን ዓርብ የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ፀሎተ ፍትሐቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት ተፈፅሟል፡፡ አስክሬናቸውም በደራሲ ሐዲስ ዓለማየውና ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን መካነ መቃብር አጠገብ አርፏል፡፡
አቶ ማሞን ይበልጥ ታዋቂና ተወዳጅ ያደረጋቸው በሥነ ጽሑፉ መስክ ያበረከቱት መጠነ ብዙና ዘርፈ ሰፊ የድርሰት ሥራዎቻቸው ናቸው፡፡ 53 መጻሕፍት ያሳተሙ ሲሆን፣ 54ኛው ‹‹ጣጣኛው›› ልብወለድ በሕትመት ላይ ነው፡፡ ሥራዎቻቸው በስለላ፣ በታሪክ፣ በልብለወድና በተውኔት ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡
#shotelayuselay#mamowudneh#tsegayeaberar#1
Spend enjoyable and educational time together with this video, Thanks for watching. If you have any personal questions or comments about this video you can contact me via links mentioned below.
ፌስቡክ 👉 / tsegaye.aberar.1
ኢንስታግራም👉 / tsegayeaberar
ቴሌግራም 👉t.me/tsegayeaberar