Рет қаралды 4,176
መዝሙረ ዳዊት 42:2
2 "ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?"
Lyrics:
..........
የሰማያትን መስኮት ከፍተህ
መንፈስህን በእኛ ላይ አፍስስ
ተጠማን ያንተን መገኘት
ናፍቀናል ፊትህን ማየት
ነፍሳችን ትልሀለች ህያው አምላክ
ሰማይን ቀደህ ምነው በወረድክ
ምነው ቢያበራ ክብርህ በኛ መሀል
እንድታድሰን ፈልገናል
ተጠምተናል ተርበናል
ያንተን መገኘትን ፈልገናል ×3
እንኑር ባለህበት ስፍራ
ቅዱስ መንፈስ እየመራን
ፈቃድህም ይበርታብን
ተከፍተዋል ደጆቻችን( ተነስተዋል እጆቻችን )
ቤትህን እንድትሞላ በክብርህ
ልናይ ናፍቀናል ሁላችንም
ልማድ አይደለም አንተን ተርበናል
ያላንተ አንረካም ተጠምተናል
ተጠምተናል ተርበናል
ያንተን መገኘትን ፈልገናል ×3
የነፍሳችን ባዶነት ክፍተት
ስንጥር በሌላው ለመውጣት
ፍለጋችን ካንተ ርቋል
ዘይታችን በመንገድ አልቋል
እንደ ቀድሞ ዘመን አድሰን
ወደ ሀሳብህ መልሰን
ያላንተ ሁሉ አቅቶናል
መንፈስህ ያስፈልገናል
ሀልዎትህ አብሮነትህ እንዲሞላበት
መቅደስህ ይፅዳና ኑርበት
ከቀድሞውም በላቀ ዛሬ አበርታን
እንጮሀለን መንፈስን ሙላን
(ተጠምተናል...) ድፍርሱ እንዲጠራ
(ተርበናል...) ስራህን በኛ እንድትሰራ
(ተጠምተናል...) ስምህ በምድር ሁሉ እንዲጠራ
(ተርበናል...) ህይወት መሆንህ እንዲወራ
(ተጠምተናል...) እጅ ላንተ እንሰጣለን
(ተርበናል...) እንድትመራን እንለቃለን
(ተጠምተናል...) እንድትሞላን እንለምናለን
(ተርበናል...) መንፈስህን ብለን እንጮሃለን
..........
Follow AASTU ECSF on :
Telegram: t.me/aastuecsf
Instagram: www.instagram....
TikTok: www.tiktok.com...