የዶ/ር አረጋ ይርዳው የመሪነት ተሞክሮ @Addischamber

  Рет қаралды 736

SAK Training & Consultancy

SAK Training & Consultancy

5 ай бұрын

አዲስ ቻምበር ከ ኤስ ኤ ኬ የስልጠና እና የማማከር ተቋም ጋር በጋራ በመተባበር የስራ መሪዎች መድረክ / Forum for ExEcutive Leaders (FEEL) የተሰኘ አዲስ የመማማሪያ፣ የልምድ ልውውጥ እና የግንኙነት መረብ (Networking) ማዳበር ላይ መሰረት ያደረገ አገልግሎት ነው።
የመጀመርያው ዙር ላይ ልምዳቸውን ያካፈሉት ዶ/ር አረጋ ይርዳው የቀድሞ የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስራ አስፈጻሚና በአሁኑ ወቅት የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንተ ናቸው፡፡ ዶ/ር አረጋ 26 ድርጅቶችን እና ከ8000 በላይ ሰራተኞችን የመሩ ሲሆን በመሪነታቸው ወቅት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች፣ ምቹ አጋጠሚዎች፣ የተከተልዋቸው የአመራር ፍልስፍናዎች እና ስልቶች እንዲሁም ጥበቦችን ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡ በመክፈቻ ዝግጅቱ ላይ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በመሪነት የሚሰሩ ከ150 በላይ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡
መድረኩም በዋነኛነት፣
• በተለያየ መስክ ለተሰማሩ የሥራ መሪዎች ምቹ የመማማሪያ ሁኔታ ለመፍጠር፣
• መልካም ተሞክሮ ካላቸው መሪዎች ተግባር ተኮር እና አዳዲስ ሐሳቦችን እንዲያገኙ ለማስቻል፣
• በመሪዎች መካከል የግንኙነት መረብ እንዲዳብር እና የመሪነት ሙያ እንዲጎለብት ማስቻል፣
• ወደፊት የመሪነት ቦታ ለመያዝ የሚታጩ ወጣት መሪዎች ከአንጋፋ መሪዎች የመሪነትን ጥበብ እንዲላበሱ ማገዝ፣
በአመራር ላይ ስኬታማ በመሆን ታዋቂ የሆኑ ታላላቅ ዜጎች (senior citizens) ለስራቸው እውቅና የሚሰጥበት መድረክ እንዲሆን ማድረግ፣ የሚሉትን ዓላማዎች ለማሳካት ነው፡፡
በዚህ መድረክ የታላላቅ የስራ አስፈጻሚዎች የቢዝነስ አስተሳሰብ እንዲቃኝ በማድረግ ምርጥ ተሞክሮዎቻቸውና ስኬቶቻቸው ለአሁኑ ትውልድ እንዲተላለፉ ይደርጋል፡፡ ታላላቅ የሀገራችን የስራ መሪዎች ባለፉባቸው የአመራር ዘመናት ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ሲገጥማቸው የነበሩ የኢኮኖሚና የቢዝነስ ተግዳሮቶች እንዴት እንደተወጡ ለሥራ መሪዎች አቅጣጫም ይጠቁማሉ፡፡
መድረኩ በወር አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሆኖ ለሁለት ሰዓት የሚቀይ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ከ11፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 በቋሚነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የንግድ ተቋማት መድረኩ አቅም ግንባታን ለማዳበር ያለውን ፋይዳ በማወቅ በአሁኑ ወቅት ስራ አመራር ኃላፊነት ላይ ያሉ መሪዎችን ወይም ወደፊት መሪ ለመሆን የታጩትን ወጣቶች ወደ መድረኩ በመላክ ብቃታቸውን እንዲገነቡ እድል እንዲያመቻቹላቸው አዘጋጆች መልእክት ያስተላልፋሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም የአላማው ደጋፊ፤ የስራ መሪ፤ የንግድ አከናዋኞች እና የስራ ፈጣሪዎች የዚህ መድረክ አካል፣ ተሳታፊ እና አጋር መሆን እንደሚችሉ አዘጋጆቹ በአክብሮት ይጋብዛሉ፡፡

Пікірлер: 2
@FinoteTech
@FinoteTech 4 ай бұрын
እጅግ በጣም አስተማሪ ነው። እናመሰግናለን! በርቱ!
@silas8349
@silas8349 2 ай бұрын
ለዚህም ጥያቄ ፓወር ፖይንት ያስፈልጋል አታውቅም ከደመና በላይ ፀሐይ የሚሞቅ ጭንቅላት እንዳለኝ !+!
I'm Excited To see If Kelly Can Meet This Challenge!
00:16
Mini Katana
Рет қаралды 30 МЛН
Mama vs Son vs Daddy 😭🤣
00:13
DADDYSON SHOW
Рет қаралды 50 МЛН
Can A Seed Grow In Your Nose? 🤔
00:33
Zack D. Films
Рет қаралды 29 МЛН
ስራ አመራር 1 1
1:37:32
Alliance Consultancy PLC
Рет қаралды 2,9 М.
I'm Excited To see If Kelly Can Meet This Challenge!
00:16
Mini Katana
Рет қаралды 30 МЛН