የተዛባው የሚዲያ እይታ በእስልምና ላይ ዶ/ር ዛኪር ናይክ |ክፍል አንድ| Media & Islam by Dr. Zakir Naik

  Рет қаралды 4,263

Reyan Tube

Reyan Tube

Күн бұрын

Пікірлер: 6
@reyantube
@reyantube 2 жыл бұрын
kzbin.info/door/iu8hHABHOFFUE0gicD4TKQ
@nseid6460
@nseid6460 2 жыл бұрын
Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል, «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» በአሕመዲን ጀበል!!!! 💞💞👏👏
@reyantube
@reyantube 2 жыл бұрын
በትክክል
@reyantube
@reyantube 2 жыл бұрын
የስም ማጥፋት ዘመቻን ከሚያካሂዱት አንዱ የሆነውን ግለሰብ በህግ አግባብ እንዲጠየቅልኝ ስል ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክስ ባቀርብም መርማሪው ፖሊስ ቃሌንና ማስረጃዎቼን ከተቀበለና ከመረመረ በኋላ «ጉዳዩ ያስከስሰዋል»ብሎ ተቀበለኝ። ቀጥሎም መዝገቡን «አጠናቅሬ ወደ ዐቃቢ ሕግ መርቼዋለሁ» ካለ ሁለት ዓመት ሊሞላው እየተቃረበ ቢሆንም ዛሬም ድረስ አንዳች የተደረገ ነገር የለም።ይህ ሁኔታ ፖሊሱ ቃል ሲቀበለኝ ስለግለሰቡ «እርሱ እኮ በማህበራዊ ሚዲያ በየእለቱ የሚናገረው አብዛኛው እኮ የሚከስ ካለ በወንጀል የሚያስከስስ ነው።» ያለኝ ነገር በአዕምሮዬ ላይ ደጋግሞ ያቃጭልብኛል።እውነትም «የሚከስ ካለ»። በሰሞኑ በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ ንጹሃን ሙስሊሞች ላይ ታቅዶበት የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት ሕዝበ ሙስሊሙን ሲያስቆጣና ጉዳዩ ወደ ተቃውሞ ሲያመራ የቆሙለትን አካል ወንጀል ለመደበቅ፥ሙስሊሞችን መልሰው በመወንጀልና በማጠልሸትና አጀንዳ ለማስቀየስ መንገድ ሲፈልጉ የነበሩት የሰጠመችው ደሴት ናፋቂዎች አህመዲን «የሚዲያ ስልጠና ሰጠበት» ያሉትን ሰነድ ተጠቅሞ ማወናበድ ጠቃሚ መስሎ ታያቸው።ወዲያው ከዚህ በፊት በሞጣው የሽብር ጥቃት «ተጠያቂው አሕመዲን ጀበል ነው።» ብለው ለማጠልሸት እንደሞኩሩት ሁሉ ጎንደር በሙስሊሞች ላይ የተፈጸመውንም የሽብር ጥቃትም «አሕመዲን ጀበል ለሽብር ዓላማ ሲያሰለጥናቸው ከነበሩት ሕቡዕ ቡድን አባላት በኩል ያስፈጸመው እርሱ ነው ።» በሚል ቅኝት «ይኀው ያሰለጠነበት ሚስጥራዊ ሰነድ» ብለው ወደ ሚዲያዎቻቸው ብቅ አሉ። አባላቶቻቸውም በማህበራዊ ሚዲያዎቻቸው ተቀባበሉት።ባለፉት ሁለት ሳምንታት የነርሱ መደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች መሪ ቃል «አሕመዲን ጀበል» ሆኖ ሰነበተ። ለሰጠመችው ደሴት አንዴ በሃይማኖት፣ሌላ ጊዜ ደግሞ በብሄር፣ሲያሻቸው ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ስም እንደየአስፈላጊነቱ በተለያዩ ማሊያዎች የሚጫወቱት ወገኖቻቸው አንዳንዶቹ ሰነዱን በማጋራት፥ ሌሎቹ ደግሞ «አሕመዲን ጀበል ያሰማራቸው አካለት ቤተክርስቲያን አቃጠሉ።» እያሉም ተቀባበሉ። በሚዲያዎቻቸው በኩል «አሕመዲን ለሕግ ይቅረብልንም» አሉ።እዚህ ላይ ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው እኔ ለሕግ እንድቀርብ የሚፈልግና «አሕመዲን ጀበል ወንጀል ሰርቷል።ማሰረጃ አለኝ።» ብሎ የሚያምን የትኛውም አካል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለማስረጃ ስሜን በማጠልሸት ሳይሆን «አለኝ» የሚለውን ማስረጃውን ይዞ ወደ ሕግ እንዲሄድ አበረታታዋለሁ። እነርሱ ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ የተቀባበሏቸው ሰነዶች በግልጽ እንደሚጠቅሱት ስልጠናው “የሚዲያና አክቲቪዝም” ነው። በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው ሰነድ አንድም ስፍራ «በአህመዲን ጀበል የተዘጋጀ» የሚል የለበትም። እንዲያውም ሰነዱ እንደሚያሳየን ጽሁፉን ያዘጋጁት ስዎች ጽሑፉ የጻፉት ለአህመዲን እንዲደርስ መሆኑን «ለአህመዲን ጀበል» ሲል ሰነዱ ይገልጻል።እነርሱ ሕዝቡን እንደናቁት ሕዝቡ ደብዳቤ ሲጻጻፍ «ከእገሌ… ለእገሌ» የሚለውን የላኪንና ተቀባይን ማንነት ገላጭ ቃላትን የማያውቅ ባለመሆኑ ብዙዎች ይህን ነጥብ ብቻ እያነሱ ሞግተዋቸዋል።
@reyantube
@reyantube 2 жыл бұрын
ሰነዱም አንድም ስፍራ ላይ እነርሱ ሊያሳዩ የፈለጉት ሚስጢራዊ ወይም የተንኮል ነገር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚገልጽ አንዳች ነገር የለበትም።ሰነዶቹን አያይዘው በማሳየት በሰነዶቹ ዉስጥ የሌለና የማይገናኝ ርዕስ ሰጥተው ሚዲያን ተጠቅሞ ተራ የዉንብድና ተግባር ፈጸሙ። ጀርባዬም፥ ተግባሬም ሆነ ሂደቶቹ ፍጹም ህጋዊና ሰላማዊ ስለሆነ እንኳንስ በዚህ ተራ የቀሽም ፕሮፓጋንዳ እኔን ልታሸማቅቁ ይቅርና እንደቁም ነገር ወስጄ ምላሽ ለመስጠት ጊዜ የማባክንበት አልነበረም። አንዳንድ ሙስሊምና ክርስቲያን ወዳጆቼም «ንጹሕነትህ ላይ ፍጹም እርግጠኞች ብንሆንም በሚዲያቸው ስለተቀባበሉት የዋሆች ሰለባ እንዳይሆኑ ስትል የሆነ ነገር ብትልበት» ብለው ስለጠየቁኝ እንዲሁም ጊል ከርቲማንቺ«ፕሮፓጋንዳ እንደ ሄሮይን አደገኛ ነው። ሰዎች ሳያጤኑት ሙሉ የማሰብ አቅማቸውን ያሟሟል።›› እንዳለው የሰዎቹን ሴራና የፕሮፓጋንዳን ምንነት በቅጡ ያልተረዱ የዋሆችን ለመታደግ ስል በጉዳዩ ላይ ጥቂት ነገር ለማለት ወደድኩ። እርግጥ ነው እንኳንስ «ሚስጥራዊ» የሚል ታፔላ(ርዕስ) የተለጠፈለት ሰነድ ተያይዞ አይደለም ያለምንም ማስረጃ የተጻፈውን ብቻ ለማመን ቅርብ የሆኑ ስለሚዲያ ቁማር የማያውቁ ወይም በስከዚህ ቀደሙ ሚዲያውን በተቆጣጠሩት አካላት አማካኝነት በተሠሩ ፕሮፓጋንዳዎች ምክንያት አሕመዲን ላይ ጥርጣሬ ቢጤ የገባቸው ጥቂት የዋሆች ሊታለሉ እንደሚችሉ እሙን ነው። ምክንያቱም ስቴፈን ሞሊኒዬክስ እንዳለው‹‹የፕሮፓጋንዳ አጠቃላይ ዓላማ ግልፅ የሆነውን ነገር ደብዛዛ አልያም አስፀያፊ አድርጎ ማቅረብ ነው።›› ነውና። Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል, [5/10/2022 12:43 AM] [In reply to Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል] ባለማገናዘብ የፕሮፓጋንዳዎቻቸው ሰለባ የሆኑትም ሚዛናዊ ሆነው በቅንነት ማገናዘብ ሲጀምሩና ሚዲያዎችን እንደ ወረዱ ማመን ሲያቆሙና ነገሮችን ምክንያታዊ ሆነው «ለሚሉት ነገር ምን ማስረጃ አቀረቡ? ማስረጃ ቀርቦ ከሆነም ማስረጃዎቹስ የሚታመኑ ናቸው ወይ? የሚታመኑ ከሆኑስ ማስረጃዎቹ እንዲያስረዱ የቀረቡትን ጭብጦችንና ነጥቦችን ምን ያክል የሚያስረዱ ናቸውን?›› እያሉ መጠየቅና ማመዛዘን ሲጀምሩ ሚዲያውን በተቆጣጠሩ ቁማርተኞች እንደተታሉ በቀላሉ ይረዳሉ። ጥቂት ሙስሊሞች ስለሚዲያ ስልጠና መውሰዳቸውን ሲረዱ ስርቆት ፈጽሞ ሊደበቅ እየሞከረ ያለ ሌባ ፖሊስን ሲያይ እንደሚሸበረው ሁሉ «በገለልተኛ ሚዲያ» ስም «ደሴቲቷን ለሚናፍቀው» ቡድን ዓላማ የቆሙና የአማርኛውን ሚዲያ የተቆጣጠሩት አካላት የሚዲያ የበላይነታቸው ያጡ፥ሚስጢራቸው የተጋለጠባቸው መሰላቸው። ደነገጡ። ከድንጋጤያቸውም የተነሳ የሚያሸማቅቁን መስሏቸው ያቺ የተለመደችውን «አሸባሪ፥ አክራሪ፥ሚስጢራዊ እንቅስቃሴ ፥ጂሃ*ዊ» የሚሉ ማጠልሻና ማሸማቀቂያ የጅል ካርዳችቸውን መዘዙ።ተቀባበሉትም። «በገለልተኛ ሀገራዊ ሚዲያ» ስም የመረጃ ፍሰቱን፥ የዜና ምንጭነቱን፥የትርክትና አጀንዳ የመስጠት ሂደቱን የተቆጣጠሩት አካላት እነርሱ ሚዲያዎችን በመቆጣጠር ሀገራዊ አጀንዳ የማስረጽ ሂደትን እንዴት እንደተቆጣጠሩ እንደታወቀባቸው ሲረዱ እንኳንስ ሚዲያዎችን ሊቆጣጠር ቀርቶ ከማህበራዊ ሚዲያ አካውንቱ ዉጭ አንድም ሚዲያ የሌለውን አሕመዲን ጀበልን ወይም «ሕዝበ ሙስሊሙን ሚዲያ ተቆጣጥሮ ሀገርን ሊቆጣጠር ነው» ብለው የሰመጠችው ደሴት አቀንቃኞች የራሳቸውን ተግባር ገልብጠው የኛ አስመስለው ባለሚዲያዎቹ አጀንዳ ሊያደርጉን በግልጽ መጡ። እነርሱ ለሰነዶቹ የለጠፉባቸውን ርዕስ ሳይሆን ያያያዙትን «ሾልከው ወጡ» ያሏቸውን ሰነዶችን በጥሞና ላነበበ ሰው ሰነዶቹ አንዳች ምስጢር ወይም ተንኮል ያዘሉ አይደሉም። እንዲያውም በሚዲያ በኩል በሀገራችን የሚሰራውን ተንኮል የሚያጋልጡ ይዘት ያላቸው ናቸው።እነርሱ ካነሱት አይቀር ስለሰነዶቹና ከሰነዶቹ እነርሱን ያበሰጯቸውን ይዘቶቻቸውን ለሕዝቡ ግልጽ እንዲሆንና እንዲማርባቸውና ሕዝባችን በነርሱ ተንኮል እንዳይታለል ስለሚረዱ በቀጣይ ክፍል በዝርዝር እንመለከታቸዋለን። 🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊 «ሚዲያን የተቆጣጠረ አካል የሕዝብን አዕምሮ ይቆጣጠራል።»(ናኦም ቾምስኪ) 📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣📣 ይቀጥላል…
@reyantube
@reyantube 2 жыл бұрын
Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል, [In reply to Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል] «ሚዲያን መቆጣጠር ሀገርን መቆጣጠር ነው» በአሕመዲን ጀበል ክፍል አንድ 📻📻📺📺📡📡📢📢🔊🔊🔊📱📱🎤🎤📹 «በምድር ላይ እጅግ አደገኛው ነገር መገናኛ ብዙሃን(ሚዲያ) ነው።የብዙሃኑን አእምሮ ስለሚቆጣጠሩ ንፁሀንን ጥፋተኛ ፣ጥፋተኛውን ደግሞ ንፁህ የማድረግ አቅም አለው። ይህም ኃይል ነው።» (ማልኮም ኤክስ) 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 እንኳንስ በዚህ ዘመን ያኔ ጥንትም ቢሆን ኋላ ቀርና ልትወገድ ተገቢ በመሆኗ የሰጠመችውን ደሴት ከባህሩ ዉስጥ ፈልገው ዳግም ሊያቆሟት እየተጉ ያሉ «የሰመጠችው ደሴት ናፋቂዎች» እኔን «እንቅፋት ሆነብን» ብለው በማሰብ በማሳጣትና በማሸማቀቅ አፍ የሚያዘጉበት አንዳች ማስረጃ ብናገኝ ብለው ማስረጃ ፍለጋ ብዙ ለፍተዋል።እየለፉም ነው። እስካሁን አንዳች ለማጠልሸት የሚሆን ነገር በማጣታቸው ያለማስረጃ የማጠልሸቱ ጉዳይ በተለይ በሙስሊሙና ምክንያታዊ በሆኑት ክርስትያኖች ዘንድ ዳገት ሲሆንባቸው ዉንጀላቸውን በማስረጃ ማስደገፍ ከቻልን ብለው ብዙ ጥረዋል።እየጣሩም ይገኛሉ። የግል ኢሜይሎቼን ከአዲስ አበባ አምስት ኪሎ፥ከካዛንቺስ፥ ከአሜሪካ፥ከጀርመንና ከዱባይ ሀገር በተደጋጋሚ ጊዜ ለመጥለፍ ሞክረዋል። ተንቀሳቃሽ ስልኬንም አሰርቀዋል (ዘመናዊውን አይፎን ስልኬን የሰረቀው አካል ስልኬ እጁ ላይ እንደገባ ወዲያው ከስልኩ ይልቅ በስልኩ ላይ ተከፍተው (Signin) ሆነው የነበሩ የማህበራዊ ሚዲያና የኢሜይል ፓስወርዶቼን ለመለወጥና የራሱ ለማድረግ ሲታገል እንዲያሳውቀኝ ለጥንቃቄ ያደረግኩት የሲስተሙ አላርም በሌላኘው ስልኬ ላይ «ፓስወርዶቹን ለመለወጥ የፈለግከው አንተ ነህን? » ሲል በጥያቄ እየተደረገ ያለውን ሙከራ አሳወቀኝ።እናም ጥረታቸውን ስንዝር ሳይጓዙ ተኮላሸ)። እስካሁን በዚህና በሌሎች መንገዶች የኢሜይልና የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶቼን ለመቆጣጠር ጥረዋል። የፌስቡክ ገጼን ለማዘጋት ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር ጠልፈው ለመውሰድ ብዙ ጥረዋል።ለጊዜው እውነትነቱን ማረጋገጥ ባልችልም በሁለት ግለሰቦች አማካኝነት ሰዎቹ በመንግስት መዋቅር ዉስጥ ባሉ አባሎቻቸው በኩል የስልክ ግንኙነቶቼን ሲያደምጡ እንደነበር ተነግሮኛል። ይህ ሁሉ ልፋታቸው አንዳች የተጨበጠ ነገር አላስገኘላቸውም። በኔ ላይ በሀሰት በሚያቀርቡት ዉንጀላ ላይ እንዲታመኑ ዘንድ ማሰረጃ ለማቅረብና ለማስረዳት እስከ ዛሬ በየትኛውም መድረክ ከተናገርኳቸው ንግግሮች መካከል አንዳች የድምጽ ወይም የቪዲዮ ማስረጃ ማቅረብ አልቻሉም። ስላልቻሉም ያለአንዳች ማስረጃ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ገፉበት።
Caleb Pressley Shows TSA How It’s Done
0:28
Barstool Sports
Рет қаралды 60 МЛН
LOFI Quran • Get Instant Relief From Mental Fatigue and Overthinking ✦ NOOR
3:04:08
Dr Zakir Naik ቁርአን የአሏህ ቃል ነዉን? Full Amharic Dawa
1:55:50