Рет қаралды 2,130
ህፃን ተወልዶልናል
(ኢሳይያስ 9:6-9፣ ሉቃስ 1:30-33)
ህፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል
አለቅነትም የእርሱ ይሆናል
ህፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል
ንጉስነትም የእርሱ ይሆናል
ስሙ ድንቅ መካር ሀያል አምላክ
የዘላለም አባት ነው የሰላም ልኡል
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም
ለመንግስቱ ስፋት፣
ለሰላሙም ብዛት ፍፃሜ የለም
መንግስቱ የፍትህ የፅድቅ ነው
በእርሱ ተደግፎ የፀና ነው
በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል
አገሩን ይገዛል
የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል
ብፅእት ማርያም ሆይ ተመርጠሻል
በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻል
የአለምን አዳኝ ትፀንሻለሽ
ልጅን ትወልጃለሽ
ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ
ህዝቡን ከሀጢአት ያድናቸዋል
ታላቅ የልኡል ልጅም ይባላል
የዳዊትም ዙፋን ይሰጠዋል
በያእቆብም ቤት ላይ
የዘለላለም መንግስትን ይወርሳል
አምላክነቱን ትቶ ነው ወደ ምድር የመጣው
ክብሩን ከላይ ትቶ ነው በበረት የተወለደው
እኔን ሀጢአተኛውን ለማዳን
ራሱን ባዶ አረገ
ፍቅር ግድ ብሎት ተወለደ
To us a child is born
New Amharic Mezmur
2020