Рет қаралды 722,276
ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ የውስጥ ሰውነቴም ሁሉ ቅዱስ ስሙን ባርኪ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፤
መዝሙር 103:1 - 2
Bless and affectionately praise the Lord, O my soul, And all that is [deep] within me, bless His holy name. Bless and affectionately praise the Lord, O my soul, And do not forget any of His benefits;
Psalms 103:1 - 2
#DawitGetachew #OhNefse #CornerstoneRecordingStudios
ኦ ነፍሴ
ነፍሴ ሆይ አስቢ ያደረገልሽን እግዚአብሔር
ከጥፋት ከልሎ እዚህ ያደረሰሽን ሆኖሽ ቅጥር
ከደዌሽ በሙሉ የፈወሰሽ በጭንቅ ሰዓት የደረሰልሽ
ጎልማሳነትሽን እንደ ነስር ጉልበት የሚያድሰው
ምኞትሽን ከበጎ ነገር የሚያረካ እግዚአብሔር ነው
ህይወትሽን ያዳነ ከጥፋት መንገድ
ከፊት ለፊትሽ ቀድሞ የሚሄድ
የውስጥ ሰውነቴ ቅዱስ ሰሙን
በቀንም በማታ አክብሩት እርሱን
እግዚአብሔር መሃሪ ይቅር ባይ ነውና
ነፍሴ ሆይ እያሰብሽ አቅርቢ ምስጋና
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ
እርህራሄው እጅግ ብዙ ነው
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ
እርህራሄው እጅግ ብዙ ነው
ለቁጣው የዘገየ ፍቅሩም የበዛ አምላክ ነውና
ለሚፈሩት ሁሉ የምህረት አምላክ ነው የእንደገና
ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚሪቅ መጠን
ከአንቺ አስወገደው የሚያስጨንቅሽን
እንደ ሚራራ አባት ለውድ ልጆቹ
ዘወትር የያዘሽ በሰፊው እጆቹ
ነፍሴ ሆይ አስቢ ታላቅ ውለታውን
ሁልጊዜ አፍልቂ ለርሱ ሚገባውን
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ምህረቱን እያሰብሽ አመስግኚ
እርህራሄው እጅግ ብዙ ነው
ኦ ነፍሴ እባክሽ
ፍቅሩን እያሰብሽ አመስግኚ
እርህራሔው እጅግ ብዙ ነው
በበረሀው ምድር ምንም በሌለበት
ለጥምሽ እርካታ ለድካምሽ እረፍት
ለጠላት ፍላጻ ከቀስተኛም ትኩረት
ከለላ የሆነልሽ ካንቺ ፍቅር ይዞት
በለመለመው መስክ ዘውትር እየመራሽ
በጠላትሽም ፊት በዘይት የቀባሽ
እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ምህረቱን ያበዛልሽ
እግዚአብሔር ነው
እንደ በደልሽ ያልከፈለሽ ቸርነቱን ያበዛልሽ
እግዚአብሔር ነው
ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ
ኦ ነፍሴ እግዚአብሔርን ባርኪ ነፍሴ