Semere Bariaw| ሠመረ ባርያው | ሰመረ ባሪያው| Bariyaw | ቲክቶክ| Funny Reaction| tiktok V29

  Рет қаралды 94,610

Semere Bariaw

Semere Bariaw

Күн бұрын

Credit:
📌SUBSCRIBE HERE:
/ if The new feature @SemereBariawethiopia
📌Like our facebook page!
www.facebook.c...
Ii 📌Join our facebook group!
www.facebook.c...
📌Join us on Telegram!
t.me/yesamntuo...
📌Reach out on WhatsApp!
call.whatsapp....
📌Drop an email!
semerebariawshow@gmail.com
Semere Bariaw a.k.a bariyaw and baryaw is an Ethiopian lawyer, tv and radio host and social media figure who aims at shaping society with humor, satire and caustic remarks. Semere Baryaw worked at Fana Television with a TV Show called Yesamintu Chewata, Yesamntu Chawota, Yesamentu Chewota, aired for three years and currently runs the same show at NBC Ethiopia TV.
Semere Bariaw also co-hosts, in addition to Yesamintu Chewata, a popular radio show tadyas addis, tadias addis at Ethio FM 107.8 with Seifu on EBS, Seifu fantahun, seifu fantahun. Semere has performed Stand up Comedy shows on ebs KZbin, Fana Television, Ethiopian TV, Amharic chewata, ethiopia, Ethiopian TV, ebc ethiopia, VOA Amharic and DW Amharic. #Semere #Semerebariaw #baryaw
His genere may be cited as Ethiopian Satire, Ethiopian Comedy, Satire, sarcasm, New Ethiopian Comedy Satire, Live Comedy, Amharic chewata. Semere Bariaw is active on tiktok especially with reaction videos "min yilalu" covering issues related to fun #politics #socialmedia, #media #satire #culture #fashion #ethiomusic #history #education #diaspora #newsethiopian #tadyasaddis #ethiofm107.8 #music #news #humor #Semerebariawkassaye #Television #Ethiopia #EthiopianTV #EBC #comedy #ethiopiancomedy #sitcom #ethiopia #amharicfilm #seifuonebs
በጨዋታው ...
#ሠመረ #ሰመረ #ባርያው #ባሪያው #ቲክቶክ
#ፋናቴሌቪዥን #የሣምንቱጨዋታ #የሳምንቱጨዋታ
#የኢትዮጵያፊልም #አማርኛፊልም #ሀበሻፊልም #የኢትዮጵያሙዚቃ #አማርኛሙዚቃ #ዘፈን #ፖለቲካ #ማህበራዊህይወት #ፋሽን #ኢትዮጵያታሪክ #መጽሐፍት #ስፖርት #የኢትዮጵያኳስ #ሚዲያ #ኮንሰርት #ቴሌቪዥን #መዝናኛ #ወቅታዊመረጃ #ወሬ #ኢትዮጵያዊነት #ብሔርብሔረሰቦች #ሙዚቃ #ሃይማኖት #ተከታታይድራማ #ቲቪ #ፍቅር #አንድነት #ገበያ #ኑሮ #መብራት #ውሃ #ቴሌ #ሳምንታዊመረጃ #ሠፈር #ትምህርት #ፍርድቤት #ህክምና #ሆስፒታል #ክሊኒክ #ፌስቡክ #ዩቲዩብ ሌሎችም ይዳሰሳሉ።
#ምንትላለች
#ምንይላል
#ምንይላሉ

Пікірлер: 373
@tigisttewelde5841
@tigisttewelde5841 Жыл бұрын
እግዚኣብሔር ይስጥህ ለባለጌ መድሐኒት ነህ እኮ።
@proudethio1594
@proudethio1594 Жыл бұрын
Exactly
@thomasdemeke8211
@thomasdemeke8211 Жыл бұрын
@@proudethio1594 k
@wondwossenzelekezeleke8197
@wondwossenzelekezeleke8197 Жыл бұрын
ሰምዬ አንተ ተባረክ ምርጥ የኢትዮጴያ ልጅ የአንተ አይነቱን ብቻ ያብዛልን በርታ ወንድሜ
@neimay4696
@neimay4696 Жыл бұрын
Semer you are the best. We need ❤️ more people like you before we lose our culture. may Allah bless you 🙏
@emmy1365
@emmy1365 Жыл бұрын
እንደው ጌታ ይባርክህ ሰመረ ወንድሜ እነዚህን ጋጠወጥ ልጆችን ልጆቻችን ያየዋቸዋል....እግዚኣብሔር እንደዚህ እሚጮህልን ያብዛልን‼
@amazingvideos-ph9rq
@amazingvideos-ph9rq Жыл бұрын
ይድረስ መልእክቴ ለ ማከብርዎት አቶ ሰመረ! በመጀመሪያ አንቱ የምልዎት ስለማከብርዎት እንጂ በእድሜ ይበልጡኛል ለማለት እንዳልሆነ ይታወቅልኝ! በመቀጠል በዚህ ቪዲዮ ላይ ስማቸው መምህር ዮርዳኖስ አበበ የሚባሉ መምህር ተችተዋል! እጅግ በጣም ያሳዘነኝ ነገር እኚህ መምህር ይህን ትምህርት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ሆነው በመንፈሳዊ ህይወታቸው ለውጥ ማምጣት ለሚፈልጉ ነው! እኚህ መምህር በቋሚነት ለረጅም ዓመታት ስለ ቅዱሳን መንፈሳዊ ተጋድሎ ዝክረ ቅዱሳን በሚባል ጎንደር የሚገኝ ማህበር የሚያስተምሩ ሲሆን በተጨማሪም ለረጅም ዓመታት በሬድዮ ፋና ስፖርት ጋዜጠኛነት አገልግለዋል! እርስዎ ያልተረዱት ብዬ የማስበው ነገር መምህሩ እንዲሁ ያለ ዕውቀት በጭፍን ጥላቻ ተነሳስተው ኳስ ጨዋታ ማየት ጣዖት አምልኮ ነው ብለው ያስተማሩ የመሰልዎት ይመስለኛል። እኔ ለ 5 ዓመታት የዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ ተማሪ ስሆን የምኖረውም ከኢትዮጵያ ውጪ ነው! የመምህር ዲያቆን ዮርዳኖስንም ሆነ የሌሎች ሊቃውንትን ትምህርት መስማት እና በህይወቴ ለውጥ ማምጣት ከመጀመሬ በፊት እኔም ሆንኩ ባለቤቴ በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ነበርን። ከሱሶቹም መካከል የኳስ፣ የዘፈን እና የፊልም ሱሶች ይገኙበታል። እነዚህ ሱሶች እኛ በቀላሉ የምናያቸው ነገር ግን መንፈሳዊ ህይወታችንን በጣም የሚጎዱ ናቸው። ይህም እንዴት ነው ቢሉ አንድ ክርስቲያን ዕለት ዕለት በመንፈሳዊ ህይወቱ እየጠነከረ ህዋሳቶቹን እየተቆጣጠረ መምጣት አለበት ለምሳሌ እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ማንኛውም ክርስቲያን ለእግዚአብሔር አስራት ማውጣት እንዳለበት ያስተምራል ታድያ አስራት ከገንዘባችን ብቻ ሳይሆን ከተሰጠን ቀንም ከ24 ሰዓት 2 ሰዓት የሚሆነው ቢቻለን በጸሎት እግዚአብሔርን በማመስገን የምንጠቀመው ነው። የእርስዎ ኃይማኖት ምን እንደሆነ ባላውቅም ከ 2 ሳምንት በፊት ግን ትንሣኤ እንደተከበረ ያውቃሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ይህን ያልኩበት ምክንያት በተለይ ከ ትንሣኤ 1 ሳምንት ቀደም ብሎ ያለው የሰሙነ ሕማማት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበላቸው መከራዎች የምናስብበት ነው እንግዲህ ይታዩዎት የሰው ልጅ የተከፈለለት ዋጋ በቃላት እንኳን የሚገለፅ አይደለም ይህ ሁሉ ዋጋ የተከፈለለት የሰው ልጅ ግን ዛሬ የት እና ምን እየሰራ ነው?? እስቲ ያስቡት እነ ቅዱስ ጳውሎስ አራቱ ሰማያት ተከፍተው ያዩበትን አይን እኛ ኳስ እና ፊልም እናይበታለን! ድንግል ማርያም ጌታን ትወልጃለሽ ተብላ ብስራት የሰማችበትን ጆሮ እኛ ሙዚቃ እንሰማበታለን! በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳን የምንላቸው እናቶች እና አባቶች በምንኩስና ብቻ ሳይሆን በትዳርም እንደነ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አይነት ቅዱሳን ልጆችን ወልደው እግዚአብሔርን ያስደሰቱ ሀገራቸውን ከመከራ በጸሎታቸው የጠበቁ ናቸው ታድያ እንደው እንደነሱ መሆን ቢያቅተን እንኳን በአግባቡ ጊዚያችንን ተጠቅመን በአቅማችን ለፈጠረን አምላክ ተገዝተን መኖር የለብንም ብለው ያስባሉ? እርስዎ እጅግ የሚያዝኑባቸው ልጆች የተገኙት እኮ ዘመናዊ ሆንኩ ብሎ ማንነቱን እና አምላኩን ከረሳ ማህበረሰብ ነው ታድያ ከማይጠቅማቹ ነገር ራቁ ብሎ ማስተማር ስህተቱ ምንድነው? ጣዖት አምልኮ ማለት ግዴታ እነ አፖሎ እና አርጤምስን አቁሞ እጣን እያጨሱ መስገድ ብቻ እንዳልሆነ ይጠፋዎታል ብዬ አላስብም ምክንያቱም ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታ እንኳን ቢያዩ ብሔሩ ጣዖት ሆኖበት እርስ በርስ የሚበላላው ሰው ቁጥር እንኳን ቀላል አይደለም። ጣዖት እኮ ምንግዜም የእግዚአብሔርን ቦታ የሚይዝ ነው ለምሳሌ እርስዎ ኦርቶዶክስ ቢሆኑ የ12 ሰዓቱን ኳስ ማየት ትተው ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ? ማታ የሚታየውንስ ኳስ ትተው በጊዜ ተኝተው ሌሊት ለጸሎት ይነሳሉ?? የእኛ ችግርም ይህ ነበር ኳስ ማየትን እንደ ጣዖት አምልኮ ቆጥረን ከህይወታችን ያወጣንበት ትልቁ ምክንያት ለመንፈሳዊ ህይወታችን ትልቅ እንቅፋት ሆኖን ነው! ክርስቶስ እኮ እንኳን ምንም የማይጠቅመውን ኳስ ይቅር እና ከእኔ ይበልጥ እናትና አባቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ብሏል። ታድያ ከጸሎት ከቅዳሴ ኳስን ካስበለጥን ይህ ጣዖት አምልኮ አይደለም ብለው ያስባሉ? የሚገርሞት ለመጀመሪያ ጊዜ የእርሶዎን ቪዲዮ ያየው ጊዜ መጀመርያ ያስታወሱኝ እኝህን መምህር ነበር ምክንያቱም ከእኚህ መምህር እና ከጥቂት የቤተክርስቲያን አባቶች ውጪ ወጣቱ ትውልድ ስርዓት አልባ መሆኑና ጋጠወጥ መሆኑ የሚቆጨው እና የሚያዝን ያለ አይመስለንም ነበር ለዛም ነበር የእርስዎ መቆርቆር ለእኛ ተስፋ ስለሆነ ሀሳብዎን የምንጋራው! እሳቸውም እጅግ በብዙ የሚደክሙት ይህን ከመስመር የወጣ ጋጠወጥ ትውልድ ከእግዚአብሔር እንዲታረቅ ለማድረግ ነው። እንኳን ለእኛ በአውሮፓ ለወለድናቸው ልጆች የአስተዳደግ ጥበብ ማለትም በማንነታቸው የማይሸማቀቁ፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሀገራቸውን የሚወዱ ሆነው እንዲያድጉ የሚያግዝ ጥበብ ያነኘነው የዝክረ ቅዱሳንን ጉባኤ በመከታተል ነው ምክንያቱም የቅዱሳን ታሪክ እና ያለፉበት መንገድ ወደ ራሳችን እንድንመለስ፣ ሀገራችንን እንዲሁም ታሪካችንን አውቀን ከእግዚአብሔር ጋር እንድንኖር በእጅጉ ረድቶናል! ይህንን መልእክት የጻፍኩት ትውልድን በጥሩ መንገድ ለመቅረፅ ብዙ እየደከሙ ያሉ መምህርን አልተረዷቸውም ብዬ ስላሰብኩ ነው! በዚህ መልዕክት እርሶን የሚያስከፋ ነገር ካገኙበት ከልቤ ይቅርታ እጠይቅዎታለው! ያነቡታል ብዬም ተስፋ አደርጋለው! አክባሪዎ ከስዊድን!
@SemereBariawethiopia
@SemereBariawethiopia Жыл бұрын
እጅግ በጨዋነትና በመልካም እሳቤ ለጻፉት መልዕክት እግዚአብሔር ያክብርልኝ። በዕውነቱ መምሕሩ በጭፍን ያለ እውቀት ተናገሩ ብዬ አላስብም፤ በስፖርት ላይ ይሰሩ እንደነበርም አውቃለሁ። እናም ንግግሬ ግላዊ የማጥላላት ዘመቻ እንዳልሆነ እንዲገነዘቡልኝ እለምናለሁ። የእኔ ነጥብ ምን መሰለዎት መቼም ሰዎች መዝናናትና አእምሮአቸውን ማሳረፍ መፈለጋቸው የተፈጥሮ ነው። ከማህበራዊ ፋይዳ አንጻር ሲታይ በተለይ በዚህ ወጣቱ እና ታዳጊው ትውልድ መዝናኛውን በስካር፣ በእፅና በመሰል ጥፋት ላይ ባደረገበት ዘመን የስፖርት ውድድር መመልከት ጤናማ መዝናኛ ነው። በመንፈሳዊ ህይወትም ቢታይ በሳምንት አንድ የዘጠና ደቂቃ ጨዋታ ቤቴ ተቀምጬ በመመልከቴ የሚደርስብኝ ጉዳት የለም። ፈጣሪዬን አምናለሁ፣ ጠንካራም ባልሆን ከነጉድለቴ ቃሉን ለመስማት እጥራለሁ፣ በመንገዱም ለመጓዝ እሞክራለሁ። እኔ የመምህሩንም ሆነ የእርስዎን ያህል እውቀት ባይኖረኝም በመረዳቴ ልክ ግን ጣዖት ወይም ባዕድ አምልኮ ማለት ለአንድ ግዑዝ አካል (OBJECT) ወይም ለአንዳች ተግባር (PRACTICE) የፈጣሪን ቦታና ክብር ሰጥቶ፣ ልክ እንደ ፈጣሪ አድርጎና በፈጣሪ ምትክ ተክቶ ማምለክና መከተል በውጤቱም እግዚአብሔርን መካድ ማለት ነው። እስከ ዛሬ እግር ኳስ አዳኛችንና የነብሳችን መድሀኒት ነው የሚል የኳስ ተመልካች አልገጠመኝም። እግዚአብሔርን ክዶ ፈጣሪዬ እግር ኳስ ነው የሚል ሰውም አይቼ አላውቅም። ስፖርቱን የሚከታተሉ ሰዎች እኮ በፈጣሪ ጽኑ እምነት ያላቸውና የሚያገለግሉትም ጭምር ናቸው። እንዲያው በምን አግባብ አንድ የ90 ደቂቃ ወይም የጨረፍታ የኳስ ግጥሚያ መመልከት ከሀዲ እግዚአብሔር ያስብላል? ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ማንም የለምና ለፈጣሪ ከሚገባው የጸሎት እና የምስጋና ጊዜ አጉድላችሁ ወደ ግል ፍላጎታችሁ አትሂዱ ወይም ከደብር ቀርታችሁ ወደ ሌላ ጉዳያችሁ አትሂዱ የሚል ትምህርት አግባብና ትክክል ይመስለኛል። በተረፈ ግን በመጽሀፍ ላይ ኳስ ተብሎ በግልጽ የሠፈረ ይመስል ለይቶ በጣዖት አምልኮነት መፈረጅና መወንጀል ከእውቀትነቱ ወደ ስሜታዊነቱ ያዘነብላል ብዬ አስባለሁ። ካጠፋሁ ጉልበት ስር ወድቄ በይቅርታ እታረማለሁ። ከታላቅ አክብሮት ጋር ! ከአዲስ አበባ
@abeldesta6546
@abeldesta6546 Жыл бұрын
አንድ ነገር ጣኦት ሆነብን የሚባለው የግድ አንተ አምላኬ ነህ ፣ፈጣሬዬ ነህ በማለት አይደለም ሙሉ ትኩረታችንን ፣ሙሉ ጊዜአችንን ፣እኛነታችንን ከተቆጣጠረ ፣ወሬአችን ፣ሃሳባችን፣አገባብ አወጣጣችን ሁሉ ያ ነገር ብቻ ከሆነ አቁመን ባንሰግድለትም አንተ አምላኬ ነህ ባንለውም ግን ገዝቶናል አምላክ ሆኖብናል ጣኦት በለው!!! ኩአስን በተመለከተ ቤት ይቁጠረው አንተ እንዳልከው ዘጠና ደቂቃ ብቻ ታይቶ በቃ በቃ መዝናኛ ነው ቢሆን ጥሩ ነበር ክለቤ ተሸነፈ ብሎ ቤተሰቡን አኩርፎ ሰላም የሚነሳ ፣እራሱን በሽታ ላይ ጥሎ ሁለት ሶስት ቀን አልጋ ላይ የሚውል ፣የቁማሩ ፣የንትርኩ ፣የክርክሩ ብቻ ምን አለፋህ አንዳንድ ሰው ጨዋታ መሆኑን ሁሉ እረስቶታል ሃሳቡን ሀሉ እሱ ተቆጣጥሮታል እናም በቃ ጣኦት ሆኖበታል
@Queen_Queen34
@Queen_Queen34 Жыл бұрын
​@@SemereBariawethiopia በጣም እወድክ ነበር ኣሁንም በጣም ኣከበርኩህ , ክብር ሰጠሁክ ፡ እድሜ እና ጤና ይስጥክ , የ መምህር የርዳኖስ ሁሉም ኣስተምህሮ ሲላልሰማህ ነው ምትሆነው የሚወደው መምህር ነው 🎉🎉
@YordanosDemelash-w4h
@YordanosDemelash-w4h Жыл бұрын
​@@SemereBariawethiopia ይቅርታ ወንድሜ የአንተ እይታህ የግልህ ነው በራስ ልክ ሊሆን ይችላል ያየኸውም ካልተሳሳትኩ ከስጋዊ አንፃር ብቻ ነው በዛ ላይ ሙሉውን ስብከት ያየኸው አልመሰለኝም ሙሉውን ብታዳምጠው እመክርሃለሁ ።ነገር ግን እኛ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በብዛት ኑሮአችን የልምድ ነው የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ስርዓቷን በተለየ ፍትሀ ነገስት ስለ ቤተክርስቲያን ስርዓት የሚያትተውን መፅሐፍ አናቀውም ለምሳሌ አንተ ከጠቀስከው ውስጥ ትያትር መመልከት ለአንድ ክርስቲያን በፍትሀ ነገስት ክልክል ነው።አብዛኞቻችን ይህንን አናዉቅም እኛም ትኩረት ሰጥተን አንማርም አባቶችም አተኩረው አያስተምሩም(በተለይ አዲስአበባ ላይ )የሚያስተምሩ መምህራን ጥቂት ናቸው።ሲያስተምሩም ጠጠር ይልብናል ስለማናውቀው። ዲያቆን ዮርዳኖስ አንዱ ናቸው። በመጀመሪያ ጣዖት አምልኮ ቤተክርስቲያናችን የምታስተምርበት መንገድ ይለያል በመቀጠል በስብከታቸው በተደጋጋሚ ከፀሎት በኋላ ስፖርት መስራት ይመክራሉ ነገር ግን ካስ ማየትን የተቃወሙበት ምክንያት ግን ከኳሱ በስተጀርባ ያለውንየምዕራባውያን አላማ እንዲሁም መንፈሳዊ ህይወታችን እየጎዳው ስለሆነ ነው። ስብከቱን ሙሉውን አዳምጠው ከምን አንፃር እንደሆነ ለሌላጊዜ ደግሞ ከመተቸትህ በፊት ከምን አንፃር ተነገረ ፤አስተምህሮቱ፣ስርዓቱ ምን ይላል እይታው መንፈሳዊ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ። አመሰግናለሁ ።
@mHret-ntnsaie
@mHret-ntnsaie Жыл бұрын
@@SemereBariawethiopia ሰሜ እኔ ምን ለማለት እንደፈለግህ ተረድቻለሁ። ጣኦት እና ሱስ የሚያስይዙ ነገሮችን ለይተን እንወቅ የማለት ያህል እንደሆነ። ኣባ ደግሞ ወጣቱ ውድ ጊዜውን ይህንን ለመኖር ኣስቸጋሪ የሆነውን ጊዜ ለማሸነፍ ሊወራበት ሲገባ ኳስን በመመልከት ( ከመመልከቱም ባለፈ ) ጥልቅ ስሜት ተገብቶ ኣልስፈላጊ ሁኔታዎች ኣስኪፈጠሩ ኣንደሚደርሱ በውርርድ በብሽሽቅ ስንት ጸብ ጥል እና ኣምባጓሮ እንደሚፈጠር የሳትከው ኣይመስለኝም። ሽንደው ቁጥር መጥቀሱ ጥናት ስለሚያስጠይቅ እንጂ በጣም በርከት ያለው ማህበረሰባችን ከጫቱ ባልተለየ ሁኔታ በጥልቅ ስሜት እስከ ሱስ መድረሳቸው ለመግለጽ ከድፍረት ግር እንገራለሁ። ኣንተ የተቸህበት ኣንድ ነገር ነው እሱም ጣኦት ለሚለው ቃል ትርጉም ብቻ ነው። የኣባ ጭንቀት ደግሞ በሱስ ለታወሩ ሰዎች ነው። ለማንኛውም የኣባን ኣውድ ብትረዳ ኖሮ ጭንቀታቸውን ተረድተህ ተጨማሪ ሃሳብ በመስጠት ኣንተ ላምትጨነቅለት ግብረገብነት ድጋፍህ እንደሆኑ ትረዳ ነበር። መቼም ብዙ ነገርህን ስለምወድልህ ሰው ደግሞ ፍጹም እንዳልሆነ ስለምረዳ እና በተለይ በዚህ ወቅት እንዳንተ ያለ ሰው ማግኘቱ እራሱ በ ጣ ም ውድ ስለሆነ በጣም ኢምንት ግድፈትህን ተረድቼ ኣሁንም ለምትሰራው ስራ ደጋፊ ሆኜ እቀጥላለሁ። በነገራችን ላይ እኔ እንዳንተው ግብረገብነት ላይ እየሰራሂ ነው ። ልዩነቱ የኔ 'VIP' የኣንተ ደግሞ በብዙኅን መሆኑ ነው። እኔ እንደዘነቡ ጴንጤዎች በየቦታው በኣኣካል ኣና ስሜትን በቅርበት በመረዳት በትራንስፖርትም ሆነ በሻይ ቤቶች ነው። እንደሚያዳምጡኝ ፈቃዳቸውን ካገኘሁ በኋላ ኣስተምህሮየን ማስተላለፍ ነው። የማህበራዊ ሚድያ መጥፎ ነገሮች ናቸው ቶሎ ተቀባይነት የሚያገኙት። ኣንደ የኣንተ ዓይነት መልካም ነገርች፡' "ኣዎን ሰመረ እኮ ልክ ነው እውነቱን ነው" ብሎ ከማለት ባለፈ ተግባራዊ የሚያደርግ ብዙ ኣይሆንም። እንደሚገጥሙህም ኣስተያየቶች ኣድናቂዎች ኣንጂ ደጋፊዎች ኣንደማታገኝ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ። ከኣስተያየታቸውም ልትረዳ የምትችለው ነው። ከኣንተ ስራ በመለሳት እንዲህ ኣደረግሁ የድርሻየን ተወጣሁ ወይም እየተውጣሁ ነው የሚል ኣታገኝም። በሬዲዮ ክብሮም ወርቁም ለእኛ መልካም ናቸው ብሎ የሚላቸውን ጧት ይነግረናል። ኣብዛኛው ሰው ትራንስፖርት ላይ ሆኖ ነው የሚሰማው ልክ ሲወርድ ግን መልእክቱ ወይም ምክሩ ኣዛው መኪናው ላይ ይቀራል። የሚተገብር ኣታይም። እንዲህ ለማለት እንዴት ደፈርክ እንዳትሉኝ። ለውጦችን ስለማላይ ነው ወዳቾቼ። እንደእኔ ነገሮችን ተግባራዊ መሆን በሚችሉበት መንገድ ብንሞክራቸው ውጤታቸው የተሻለ ይሆናል ብዬ ነው። ከታላቅ ይቅርታ ጋር የጽሁፍ ወይማ የሃሳብ ኣሰካክ ለጸሃፊዎቹ ትቼ ሃሳቤ እንዳይቆራረትብኝ ብቻ የመጣልኝ ነው ያፈሰስኩት። የቻልኩትን እንጂ የፈለግሁትን ያህልም ኣልጻፍኩም። ሃሳብ ከመጻፍ በጣም ስለሚፈጥን እጄ የቻለውን ያህል ብቻ ነው የጻፈው። ዋናው ነገር ሲጠዋለል መልእክቱ ኣንድ ነው ሰው ለሰው እንከባበር ስነ-ሥርዓት ይኑረን ከሁሉም በላይ ግብረገብነት!!! ሰሜ ከኣንተ የምማረውን እኔ ኣጠገቢ ላሉት በኣካል ኣስተምራለሁ። በርታልኝ እግዚኣብሄር ሁላችሁንም ኣብዝቶ ይባርክልኝ። ኣመሰግናለሁ።
@fitzhabte1323
@fitzhabte1323 Жыл бұрын
ሰሜ አንጀት አርሱ ሁሉም ምክርህን ቢቀበል በጣም መልካም ነበር በተለይ ለወጣቶቹ ፈጣሪ ማስተዋልን ይስጣቸው ተባረክ እናመሰግናለን🙏🙏🙏
@mikeberhanu55
@mikeberhanu55 Жыл бұрын
የማናት ጣረሞት እራሷ የተጋጠ በቆሎትመስላለች😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂😂
@binitadesse504
@binitadesse504 Жыл бұрын
ተባረክ ዘርህ ይባረክ እንደ አንተ ወጥቼ መናገር ባልችልም ልጄኝ ቤተሰቤን ጠብቃለው! ምን ጉድ ነው ዘንድሮ ግን
@newlife2805
@newlife2805 Жыл бұрын
ባርችዬ ትለያለህ ስወድህም በምክንያት ነው እንደው ጨምሮ ጨማምሮ ፀጋውን ያብዛልህ የኔ ልክ ነጋሪ እንደው ብልግና እንደዚህ ኖርማል ይሁን አፈርን እኮ ከየት ነው ግን እንዲህ የተፈለፈሉት ልጆቻችን እንዚህን እያዩ ነው የሚያድጉት?የዝቅጠት ጥግ ይብላኝ ለወለዳቸው ተቃጥሎ ያልቃል🫢🫢🫢 ባርችዬ🙏🙏🙏🙏 አትጥፋብን ቃል የለኝም ላንተ 👌👌👌👌👌👌👌 ዲያቆኑ ግን ክፉ አታናግረን አመክንዮህ አይሰራም የገባንን ብቻ ብናስተምር ባንዘባርቅ sorry to say that ,with respect!
@emebetmoges6095
@emebetmoges6095 Жыл бұрын
ሰመረ እግዚአብሄር ይባርክህ በእውነት ትምህርት ነው የምትሰጠው ለሚገባው ቀጥል አትጥፋብን
@MareyamawitTadesse
@MareyamawitTadesse 4 ай бұрын
አይ ሰሜ እግዚአብሔር እንደአንተ አይነት ኢትዮጵያዊ ያብዛልን እኔ ማለት እንዳንተ ነው የሚበሰጨኝ ባህል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሲጣስ ያመኛል ኑርልን
@mebrathhergu1690
@mebrathhergu1690 Жыл бұрын
ዕድመን ጥዕናን የሃብካ ካማካ ዝበለ ሰብ የብዝሓዮ ቀፅለሉ ❤❤❤❤እንደንተ ሰው ነው ልሃገር ያስፍልጋል እነ በርታ❤❤❤
@yedenethio4670
@yedenethio4670 Жыл бұрын
እረ ቲክ ቶክ ይህን ትዉልድ ትተክ ይሂድ ፈጣሪ ይርዳን ማፈር ወፍ የለም በቃ አረ በስመ አብ😢😢😢
@nigistayalew8959
@nigistayalew8959 Жыл бұрын
ሰመረ ተባረክ አቦ ለነዚህ ጨምላቆች በኩርኩም ብለህ አጥፋልኝ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ
@SarahKonjo
@SarahKonjo Жыл бұрын
እኦኦኦኦኦኦኦ😂😂😂😂😂
@sabrinaa4383
@sabrinaa4383 Жыл бұрын
I love you Semere Baryaw you make my day🤩 I was worried about my bills here in London, here it comes watching ur video besak motku🤣🤣 the 1st lady bale bekolowan yalkew "Cher fit maya ye duro melk" hahahahah ante kifu🤣🤣
@enjeratube2676
@enjeratube2676 Жыл бұрын
Semye welcome brother please continue working on this social issue. Hopefully, very soon, people realize your point of view. I personally appreciate your efforts and concern. Thank you so much
@SarahKonjo
@SarahKonjo Жыл бұрын
የድሮ ሰው ጌታን ሳመዬ አድሜ ጠና የስጥ
@morat795
@morat795 Жыл бұрын
ሰሜ 😂😂😂😂 ታናሽ ወንድምህ ቢሆን አሰብኩት እንዴት ወልዉለህ እንደምታንፀዉ 😂😂 በሳቅ ገደልከኝ ሰሜ በርታልን !
@giftitesfaye9784
@giftitesfaye9784 Жыл бұрын
ሰሜ ኑርልኝ
@noahabraham7168
@noahabraham7168 Жыл бұрын
❤❤❤
@kassa6220
@kassa6220 Жыл бұрын
ጌታዬ በርታልን:: አያስተማርከንና አያዝናናሀን ያለህ አንተ አንጂ ሰዎቹ አይደሉም::
@Abitiy80Yoha
@Abitiy80Yoha Жыл бұрын
እኔና እናቴ በጣም ነዉ የምንወድክ በርታ
@bulgaw
@bulgaw Жыл бұрын
Seme, I think the guy who commented on football has got an element of truth. I am not spiritual, but I have got some clue how the demonic spirit operates. The Holy bible describes what Idol worshipping means in great detail, but in simple terms, the bible defines idol worshipping as an overwhelming obsession on things that divert your focus from the spirit of God. It could be the extreme love of money, addictions, women/man...you name it. So, those maniacs who spent all their golden time by watching football, they are indeed worshipping Idol.❤❤❤ You shall love the Lord your God with all your heart and with all your soul and with all your might. Deutronomy 6:5
@SemereBariawethiopia
@SemereBariawethiopia Жыл бұрын
Azebina What do you mean I don’t look professional on this one? I am not a professional in the first place; I am an ordinary person you see on the streets who just uses KZbin to express his personal opinion on things. If you can respect a different opinion then that seals it. No professionalism here; we are just normal people sharing ideas. The man said football is pagan worshipping and I say it is a lovely sport and whether you give your full attention to it or not it is a 90 minutes game that has nothing to do with God or with any spiritual thing what so ever. We have different ideas, that’s all. But I look unprofessional to you because I don’t agree with him ???
@azebtsegaye3591
@azebtsegaye3591 Жыл бұрын
@@SemereBariawethiopia Sam I think you took it out of context I wasn't categorized you as professional. I meant it's not what you say it's how you say it for the guy who commented about the football. As I said I respect your opinion if I agreed or not.But the way how you say it make me to say unprofessional. Other than that for me no hard feeling you seem very cool guy your reaction and remarkable thoughts make me laugh.
@azebtsegaye3591
@azebtsegaye3591 Жыл бұрын
@bulgaw Thank you I Couldn't Have Said it Better Myself.
@azebtsegaye3591
@azebtsegaye3591 Жыл бұрын
Semer, agreed 100% with the guy preaching about football he is telling the truth agreed or disagreed. But if you don't agree with him that's fine we accept your opinion as well but you look very unprofessional with this one the guy was saying if you loss of control over something or obsessed your brain is controlled and you can get out off it that mean something is controlling you period.
@SemereBariawethiopia
@SemereBariawethiopia Жыл бұрын
Azi How was I supposed to say it? I said it just the same way as I say to others on my reaction videos. Why did you expect I should say it in different manner? My question is totally from curiosity by the way.
@abu5523
@abu5523 Жыл бұрын
ሰሜ ብዙ ኮሜንቶችህን እወዳቸዋለው። ነገር ግን ሰባኪው ላይ የሰጠኸው ኮሜንት ግን ደግመህ ስማው። ጣኦት አንተ የገለፅከው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የስጋ ፈቃዳችንን ለመግለፅ ነው። እውነት ነው ከአምላክ ፍቅር የኳስ ፍቅር ከበለጠ ኳሱን ማየት ጣዖት ነው። ምንም የሚያስት ነገር የለውም ስላልቻልን ነው እንጂ ብንችል ወደ አምላካችን ብንቀርብ መልካም ነው። እኔም ብሆን አርሴ ስል እውላለው መድኃኔዓለም ስል ብውል ግን በስጋም በነፍስም እቀርባለው። ትምህርቱ የገባው ሰው ካለ ይውሰደው ወደ አምላኩ ይቅረብበት እንደኔ ያልገባው ደግሞ እድሜ ልኩን አርሴ እና የኢትዮጵያ ቡድን ሲል ለንስሀ ሞት ሳይበቃ ሊወሰድ ይችላል። ስለዚህ "ምን ይላሉ" ከሚባሉት ዉስጥ ባይመደቡ። አመሠግናለው።
@girmachemere683
@girmachemere683 Жыл бұрын
ከበቂ በላይ መልስ ሰጥቷል በጣዖት እና በእግር ኳስ መካከል ያለውን ልዩነት የግድ የምንደግፈው ሰው ስለሆነ ስህተቱ ሊነገርብኝ አይገባም ማለት ልክ አይደለም ፍፁም የሆነውን ፈጣሪ ስለሰበኩ ፍፁማዊ እኮ አይደሉም ይሳሳታሉ ሰዎች ናቸው እኮ ስለዚህ ስህተትን ስህተት ነው ብለን ሃሳባቸው እንጂ የሚመዘነው ስብዕናቸው በግል ወይም ጠቅላላ ጨስተምህሮታቸው አልተተቸም በነገራችን ላይ መሰል ትችቶች(ሂሶች)በአግባቡ ከተነገሩ ሰዎችን ያንፃሉ እንጂ በየትኛውም ጎን ቢታዩ ጎጂ ሆነው ሊታዩ አይገባም
@sematbefikadu3913
@sematbefikadu3913 Жыл бұрын
ትክክል❤
@AnaAna-mr1zc
@AnaAna-mr1zc Жыл бұрын
የባለጌ መድሐኒት ሰሜ ጀግናው ተባረክ
@SofieBayana
@SofieBayana Жыл бұрын
ባርዬ ስወድህ በርታ በተቻለህ እንደዚ ትዉልድ አድን ተባረክልን
@saraahmed293
@saraahmed293 Жыл бұрын
አገሪቱኮ የሚመራት ስለሌለ ነው በሁሉም ተቋማት ተቆጣጣሪ ጠፋ ሌብነቱ ሙስና ጋጥ ወጥነት ተሰራፋ ለነገሩ እንደዚህ እንድንሆን ስለተፈለገ ነው ሁሉም ዝም ያለው
@blackstone07
@blackstone07 Жыл бұрын
ይገርማል ለካ በጣም በጣም ዘቅጠናል!
@mariaethiopia9867
@mariaethiopia9867 Жыл бұрын
ምን ላርግክ ወንድሜ ተባረክ❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤ አንጀት አርስ😊
@MeseratAsefa-m6i
@MeseratAsefa-m6i Жыл бұрын
Araa mini yilaluu setochuu seme bertaa indazaa nigarachuu❤❤❤
@abelteshome3450
@abelteshome3450 Жыл бұрын
I like all of your reactions. keep it up !
@tejealene2386
@tejealene2386 Жыл бұрын
👍😄እውነትህን ነው ሰመረ እሰይ እንደዝህ ልካችንን ማሳወቅ✅
@wendetesfaye375
@wendetesfaye375 Жыл бұрын
ሰመረ መምህሩ ላይ ተሳስተሃል...ለምሳሌ ለሁለት ጌቶች አትገዛ ይላል መጻፍ ቅዱስ...እግር ኳስም ይሁን ማነኛውም አለማዊ ነገር ስሜታዊ ሆነን ከወደድን ጣኦት ይሆናል...ገንዘብ ከወደድክ ጣኦት ነዉ...ቤተክርስቲያን ሜሄጃ ሰዓት ላይ ኳስ አለብኝ ካልክ ኳሱ ከእግዚአብሔር በለጠብህ እና አመለከዉ ጣኦት ነዉ...ስለዚህ መምህሩ ያለዉ በአመዛኙ ትክክል ነዉ!
@enanuenanu1239
@enanuenanu1239 Жыл бұрын
ተባረክ ወንድም ንገርልን ልከልክአቸዉን 🙏🙏
@ayele.tesema6229
@ayele.tesema6229 Жыл бұрын
ባለጌዋች እንደ አሸን በዙ ኢትዮጵያ ውስጥ
@thegreathiddenpower9773
@thegreathiddenpower9773 Жыл бұрын
ፈጣሪ ይባርክክ🎉 በርታ ሰሜ ያንተ አይነቶችን ፈጣሪ ያብዛልን
@hannatefera6995
@hannatefera6995 Жыл бұрын
አይ ሰመረ ወንድሜ እንደው ድካም ሲልክ ነው !! መስሚያም የላቸውም ህብረተሰቡ ነው ከነዚህ መራቅ ያለበት !!አይ ሀገሬ 😢
@ethio-zemenmedia8217
@ethio-zemenmedia8217 Жыл бұрын
ሰመረ ባርያው ስራህ ፍሬ አፍርቷል ....ጋጥወጥ በጣም ቀንሷል " ለባለጌ ጌታው ሰመረ ባሪያው "😂😂😂
@jics297
@jics297 Жыл бұрын
ፊትሽ ሞዴሉ በዘንድሮ ልጅ ፊት አይመጣውም😂😂😂
@tsegagab7644
@tsegagab7644 Жыл бұрын
የኔ ጀግና ሰሜ በልልኝ ምድረ ጋጠወጥ አግድም አደግ
@ethiopiafirst7076
@ethiopiafirst7076 Жыл бұрын
Semere Sle Bahd Amlko Sle Taot Amlko Lemabrarat Ymokerkew Neger Tnsh Manbeb Endemitebekbh Yamelektal. Menfesawi Yehonu Negerochn Berasachn Aredad Banteregumachew Tru Ymeslegnal. Tinsh Manbeb Ytebekbhel Belelochu Videochh Lay Gin Berta Maletn Eshalew
@bman9910
@bman9910 Жыл бұрын
Egziaber yeseteh 😅😅😅😅
@meazadawit4009
@meazadawit4009 Жыл бұрын
ወንድሜ እነዚ እኮ ምክር ቀርቶ ዱላ አይገባቸውም።
@nahomguta3516
@nahomguta3516 Жыл бұрын
ስሜ ሃሳብህ ከሱ አንደሚሻል አያጠያይቅም ነገር ግን ጣኦት ማለት የግድ ተክቶ act ምያረግ ብቻ አይደለም አይን አንኩአን ለ ፈጣሪ ክምትሰጠው ፍቅር ከበለጠችብህ ጣኦት ናት :: ፈጣሪን ደሞ ምትሰጠው ፍቅር ከ አለማዊ ደስታ ቀንሰህ ጊዜህን ለምስጋና ስታውለው ነው :: ለዛም ነው እውነት ለ አምልኮ ሚገባን ሰዓት ለ ኩዋስ አይደለም ለ የትኛዉም ነገር ቅድምያ ከሰጠን ያኔ ጣኦት ሆኖብናል ማለት ነው :: ነገር ግን በዚ fallacy ሌላ ነገር match አርጎ ማውራቱ ተገቢ አልነበረም :: ሰሜ በርታልን respect you so much
@konjobelete8746
@konjobelete8746 Жыл бұрын
ወይ አለመታደልሽ በራስሽ ነው የቀለድሽው ስንት ከንቱ አለ ?🙄🤭🤫 አረ ስንት ከንቱ ተወለደ በአመቱ መጨረሻ ውጤቱ ይታያል አቤትጉዳቸው🙄 ወይ አገሬ
@mehammednure
@mehammednure Жыл бұрын
የምርጥ ምርጥ ነክ
@mimiaklile7079
@mimiaklile7079 Жыл бұрын
Ufff tebarek abo ❤
@Alam-k6l
@Alam-k6l Жыл бұрын
😂😂😂😂 በጣም ነው ያስደሰትከኝ
@kelemlove4937
@kelemlove4937 Жыл бұрын
አይ ሰሚ የማታመጣብን ነገር የለም
@osmanhasen
@osmanhasen Жыл бұрын
ሰመርየ አቦ ለባለጌ መዳኒም ብቻ ሳትሆ መርዝ ሆነህልኝ የነዚህን ልጆች ብቻ ሳይሆን ዘረቻውን ጥፍት ያርግልኝ
@firatesfaye3980
@firatesfaye3980 Жыл бұрын
ሪአክት የምታደርግባቸው ነገሮች ጥሩ ናቸው በርታ ነገር ግን የ ቤ/ክ/ን መምህራን በሚናገሩት ሪአክት ባታደርግ ጥሩ ነው እላለሁ ምክንያቱም ቤ/ክ/ን አምናባቸው ነው እንዲያስተምሩ የፈቀደችው የቅርብህ ባይ ነኝ።
@eyerussurur9363
@eyerussurur9363 Жыл бұрын
Semere እንደአንተ አይነቱን ያብዛልን:: ሰው መስመሩን ከሳተ ቆይቷል:: ዘንድሮስ ጉድ ነው
@ሰላም-ዐ1ሐ
@ሰላም-ዐ1ሐ Жыл бұрын
ሰሜ እዬን ፅንፈኛ ሰባኪ ነኝ ባይ ተወው ማርያምን ደብረብርሀን ብትመጣ በየ ክለቡ በድብቅ ሲልከሰከሰ ነው ሚውለው በኩዋስ መጣብን እሄ ጅል
@getahunbogale8590
@getahunbogale8590 Жыл бұрын
ሰሜ ጀግና ነህ
@azebkifle5342
@azebkifle5342 Жыл бұрын
እረ ይቅር ይበለህ ጣኦት ምን አመጣዉ እግር ካሰ በማየት በመጫወት ደሰ ይላል ተሰባሰበዉ በማየት ይደሰታሉ እናቃለን ብለህ የጌታ ቃሉን አታዉሳሰብ የፍቅር ጌታ ሰንት ሐጢያት እያለ ጌይ ሊዘብያን ዉሸት በማዉራት ማሰተማር እያለ
@Kamiliya-r5b
@Kamiliya-r5b 9 ай бұрын
ሠመረዬ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ
@AhmedMohammed-bs8mb
@AhmedMohammed-bs8mb Жыл бұрын
ሰሜ 😂 የዝችስ በቆሎ ምናምን ያለችውስ ስትቀልድ ነው መቼም በቆሎ ለሰርግ አይቀርብ ራቁቷን ሆና አልቆላት ቪዲዬ ባሰራባት መልካም ነበር ባሪችዬ ያው አስተያየት ነው።
@Ethiohabtina
@Ethiohabtina Жыл бұрын
thank you Same enezihin chemlakawech lis masgebat yasfeligal.
@cookiese6013
@cookiese6013 Жыл бұрын
Thank you so much. 📯you are The best💯‼️
@nassersaee1515
@nassersaee1515 Жыл бұрын
semere the golden journalist
@mikeberhanu55
@mikeberhanu55 Жыл бұрын
ምንድነዉ አደባባይ ላይ ሴክስ አርጉ ነዉ ምንድነዉ የፈለግሺዉ
@hareguadesta2612
@hareguadesta2612 Жыл бұрын
ተባረክ አባቴ
@girmashegute6587
@girmashegute6587 Жыл бұрын
Bravo Semere!!!! You really expressed my ideas.
@tigistalemu1021
@tigistalemu1021 Жыл бұрын
Thank you very much Semere
@mHret-ntnsaie
@mHret-ntnsaie Жыл бұрын
ኣይ ሰሜ እንደው ትደክማለህ እንጂ ነገሮች ሁሉ መሰረት ለቅቀው ከሄዱ እኮ ቆዩ። የምታነሳቸው ሃሳቦች ሁሉ መልካም ናቸው። ነገር ግን ለመፍትሔው በጣም ብዙ ዓመታት ሊያስፈልግ ነው ምክንያቱም ለማበላሸቱ ድፍን የወያኔ የኣገዛዝ ጊዜ የወሰደ ለማስተካከሉ ምን ያህል ሊወስድ እንደሚችል መገመቱ ቀላል ነው። የሆነ ትውልድ መሳቱን ከተግባባን በኣዲሶቹ ትውልዶች ላይ ለመስራት እንትጋ። መፍትሔውንም ከሌላ ኣላክ ሳይሆን ከራሳችን ብቻ ነው። ልጆቼን እጅግ በጣም ክትትል በማድረግ ለማሳደግ በጣም እየጣርኩኝ ነው። ፈጣሪ ኣግዞኝ ውጤታማ እንድሆን ይርዳኝ
@لينامحمد-ك4ف
@لينامحمد-ك4ف Жыл бұрын
😂😂😂😂ማያ😂😂😂😂
@ሀሊማመሀመድ-ተ6ዘ
@ሀሊማመሀመድ-ተ6ዘ Жыл бұрын
ሠመራች እባክህ እተማሪወች ላይ በደብ ስራልን
@AmanTewabe
@AmanTewabe 11 ай бұрын
ውይ ሰሜ አጀት አርስ እኮነህ💚💚💚
@meseretteshome9843
@meseretteshome9843 Жыл бұрын
Enamesegnalen Semere 🙏
@user-onJonaz5533
@user-onJonaz5533 Жыл бұрын
👍semusha enezin ye Ethiopian gatetoch asarflin esti.
@liverpoolfan4368
@liverpoolfan4368 Жыл бұрын
Welcome Seme
@mekedeswinter4454
@mekedeswinter4454 Жыл бұрын
እግዚአብሔር ይባርክ መያ 😅😅
@senigi530
@senigi530 Жыл бұрын
አይ ሰሜ ኑርልን
@fanteshfantesh5684
@fanteshfantesh5684 Жыл бұрын
ሠመረ ተባረክ ።
@zehara53o
@zehara53o Жыл бұрын
ሰሜ አባንገር እስኪ ንገራት ይችን ለፍዳዳ 😂😂😂
@konjobelete8746
@konjobelete8746 Жыл бұрын
ያልታደልሽ ገልቱ " ባለጌን ከወለደ የገደለ ፀደቀ " አስተሳሰብ ነጎደለሽ ንዝላል 🤐🤬🤯🤭🤫
@samlsd9711
@samlsd9711 Күн бұрын
😂😂😂😂😂 "የድሮ መልክ" 😂😂😂😂😂 ስንት ነች? 40 ምናምን? ኢትዮጲያ ምንድነው ይሉኝታ ጠፋ ማለት ነው? እኛ በሱ አድገን ተገርፈን?
@hussent1482
@hussent1482 Жыл бұрын
Minaw tefak Barechi Eid mubark lemen alalekem muslimun mahbreseb Respect bro😢😢
@bereketwolde1129
@bereketwolde1129 Жыл бұрын
thank you seme🙏
@efremwoldu4513
@efremwoldu4513 Жыл бұрын
አውነት ነው
@dawityohanes6333
@dawityohanes6333 Жыл бұрын
ሰሜኮ አንጀቴን ነው እምታርሰኝ ኡፍ በርታልኝ እንዳንተ አይነት አስተማሪ ተቺዎች ቢበዙ ኢሔ ጋጠወጥ መልጋጣ ሰዎች ስርዓት ይይዙ ነበር 🙏🙏 በርታ ብቻ
@HH-nn7rd
@HH-nn7rd Жыл бұрын
Effffuuuyyyee agebahilat!!!
@asmaretesfie8583
@asmaretesfie8583 Жыл бұрын
ሰሜ በሞቴ ከሌቱ ሰባት ሰዓት ተነስቶ እግር ኳስ አንድ ኪሎሜትር ድረስ ሄዶ ማዬት መዝናናት ከሆነ! ወጣቱ ስራውን ትቶ ኳስ ሲመለከት ይዋል ሚጠቅመው ከሆነ🤔 ሲበዛ ስኳርም ይመራል ስለራሱ እማያቅ ወጣት እድሜዉን ስለኳስ ሲያወራ ይኑር መቼም ተፈርዶለታል🤔🤔🤔🤔🤔
@ethioruhma2613
@ethioruhma2613 Жыл бұрын
እውነት ነው 👍
@yednek30tessema
@yednek30tessema Жыл бұрын
ቢመቸኝም እኔ ነኝ አዋቂ አለ። ቢቻል መምህሩ ሊል የፈለገውን ተረድቶ ሚዛናዊ ትችት መስጠት ጣኦቱ ስህተት ከተባለ እሺ ኳሱ ደሞ በቀን 21 ሰዓት በ40 ጋዜጠኛ በሬዲዮ ሲቀደዱ ይውላሉ አረ እኔ የምኖርበት ከተማ ትልልቅ ሚዲያዎቻቸው 20 ደቂቃ ሁላ አይሰጡሃቸውም ኢትዮጵያኮ ስለ ኦዚል የእህት ልጅ ሙሉ ቀን ስለ ፖግባ የዘር ሃረግ ስለ ሮናልዶ ሚስቶች አረ ሰሜ በጫት ዞሮበታል ቃጢራ ቅሞ እየመጣ አዛገን
@SemereBariawethiopia
@SemereBariawethiopia Жыл бұрын
ስለ ኦዚል ሚስት ታሪክና ስለ ሮናልዶ ጫማ ቀኑን ሙሉ መለፍለፍ እጅግ ነውር፤ አድማጭንም መናቅ እንደሆነ ከአንድም አራት አምስት ጊዜ በቴሌቪዥን ሳይቀር ኡኡ ስል የከረምኩት እኔ ነኝ። አሁንም ደጋግሜ ስህተት መሆኑን እናገራለሁ። በዚህ ቪዲዮ ላይ ግን ጉዳዩ ሰዎችን በእግር ኳስ ስፖርት ወዳጅነታቸው ብቻ ከአምላክ የመነጠልና ወደ ሌላ አምልኮ የመፈረጅ ተግባር ነው። አግባብ አይደለም ነው ያልኩት። በተረፈ ሰዳቢ መልኩ አይታይም ስሙም አይታወቅምና ከራሱ አእምሮ ውጪ ሌላ ዳኛ ስለሌለው ስድብህን ላንተው ፍርድ እተወዋለሁ። ''ኧረ ስቀልድ ነው'' ብለህ ልክ እንደ ዘመኑ አካሄድ ከምንም ሳትቆጥረኝ ማለፍ ነው። እግዚአብሔር ያክብርልኝ ለማንኛውም!
@meronberhanu4772
@meronberhanu4772 Жыл бұрын
እንኳን አደረሰህ
@eyerusalemewnetu
@eyerusalemewnetu 11 ай бұрын
Endew Be MARYAM Kbe new yekbahnge tebark KDUS GEBRELN
@abufariskemal1711
@abufariskemal1711 Жыл бұрын
ሰካራሞች ከየትነው የምታገኛቸው ጀግናው
@YonasFishatsion-cw9bh
@YonasFishatsion-cw9bh Жыл бұрын
ወድሜ ሰመረ ልባችንን ጠቡት ያሁኖቹ ባሱ አዶ ጡቷን ኳስ የሰይጣን ጉድ እኮ ነው 🤣🤣
@Emblba
@Emblba Жыл бұрын
😂😂 ገደልካት ሚያውዬን
@abelcrazy6472
@abelcrazy6472 Жыл бұрын
ግጥም አድርጌ ነው ምናገርሽ ፓርት 👌😂😂😂
@TigistAbcd
@TigistAbcd 5 ай бұрын
አይ።ሰሜ የባለጌ መድሀኒት
@joewellajoe5377
@joewellajoe5377 Жыл бұрын
Yemeche Bro !!!!🤣🤣🤣
@Getahun845
@Getahun845 Жыл бұрын
Semeren 1M subscrib እናስገባው
@hana.6956
@hana.6956 Жыл бұрын
አቤቱ አድነን ፈጣሪ ትውልዱ ጠፍቷል
@elekelet
@elekelet Жыл бұрын
ሰሜ ይዙርብሽ/ህ እላለሁ ሁሌ when i saw some crappy videos on tiktok 😂
@yared2112
@yared2112 Жыл бұрын
ተማሪ ነች መምህርት መስላ የቀረበችው ጋጠወጥ
@marthahidego7902
@marthahidego7902 Жыл бұрын
Semera betam enamesegenalen
@yuliyaafewerke348
@yuliyaafewerke348 Жыл бұрын
ኦ ያንቺ ሠርግ ላይ ነው እኛስ አያርግብን
@shemeleslegesse3189
@shemeleslegesse3189 Жыл бұрын
ሰሜ ሰሜ እንኳንም መጣህልኝ ጠፋህብን ምነው ሰሜ ለዚችማ ምን መልስእንደምትሰጣትና እንዴት እንደምስቅ አጠይቀኝ ምችት ይበልህ ሰምዬ
@samiraseid9324
@samiraseid9324 Жыл бұрын
Thank you so much for telling them the saddest truth this people are out of this world especially those to ladies
Seja Gentil com os Pequenos Animais 😿
00:20
Los Wagners
Рет қаралды 89 МЛН
ROSÉ & Bruno Mars - APT. (Official Music Video)
02:54
ROSÉ
Рет қаралды 269 МЛН
小路飞还不知道他把路飞给擦没有了 #路飞#海贼王
00:32
路飞与唐舞桐
Рет қаралды 58 МЛН
Seja Gentil com os Pequenos Animais 😿
00:20
Los Wagners
Рет қаралды 89 МЛН