Рет қаралды 6,460
በእስያ ካሉት አገሮች ሁሉ ውብ የነበረችው ጴርጋሞን ነበረች፤ ሮምን ሲሰሩ ከብዙ ዘመን በኋላ ብዙ የህንጻ ስራ ኩረጃ ከጴርጋሞን ወስደዋል። ከተማይቱ ሃብታምና የአገረ ገዢው መኖሪያ ነበረች፤ ከምስራቅ የሚመጣ ጠላት እንዳያጠቃት 50 ኪ.ሜ ራቅ አድርገው የጦር ካምፕ ነበረባት።.
ትያጥሮን እንደ ጴርጋሞን የንጉሠ ነገሥት አምልኮ የሚካሄድባት ትልቅ ማዕከል ባትሆንም
አረማውያን አማልክት የሚመለኩባቸው መሰዊያዎችና ቤተ መቅደሶች ነበሩባት። በጣም የታወቀች የንግድ ማዕከል ነበረች። በሁለት ወንዞች ሸለቆዎች መጋጠሚያ ላይ የተቆረቆረች ትያጥሮን በመቄዶንያ ከሚገኙት ከተማዎች መካከል በዘመኑ በልብስ ማቅለሚያ፥ በነሐስና በብር ሥራ ዕደ ጥበባት ሙያ የሠለጠኑ ባለሙያዎች ያፈራች በእነዚህ የምርት ውጤቶች ላይ በተመሠረተ ንግድ ምክንያት በጣም የከበረች ከተማ ነበረች።