Yonas Gorfe Part 2 Interview

  Рет қаралды 12,582

Ecclesia Media - ኤክሌሲያ ሚዲያ

Ecclesia Media - ኤክሌሲያ ሚዲያ

Күн бұрын

Пікірлер: 95
@nanimolshe402
@nanimolshe402 8 жыл бұрын
ቆይ አንድ ነገር ያልገባኝ ምስጋና የሚገባው እግዝያብሄርን ማመስገን እያለ ለአለም አገልግሉ ብሎ ሙግት አለ ጌታን አመስግነን መቼ እረካን እና ነው ሌላው ጋር ግራ የምንጋባው!
@jolememeru471
@jolememeru471 8 жыл бұрын
የኔ ጥያቄ በየወንጌላውያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ብመዝሙር፣በክርስትና ስም የሚደረጉትስ ቅጥ ያጡ ፈንጠዝያዎችን ምን እንበላቸው?
@buddhomi
@buddhomi 8 жыл бұрын
Yonas made strong argument. Ethiopa Protestant theologian should challenging him biblically not condemn as usual
@selamawithabtamu573
@selamawithabtamu573 8 жыл бұрын
በእውነት በጣም ነው የማዝነው ጌታ ማስተዋል ይስጣችው በግ ደብ ለብሰው ከሚመጡ ተጠበቁ በየሱስ ስም ጌታ ሆይ በምህረት ጎብኘን
@solomongizaw7299
@solomongizaw7299 8 жыл бұрын
Hello Abiy, Thank you for your interview with Yonas. Yezih ayinet yetesasate timihirt ina message bewere kemibaza indezih be-gilts be-adebabay wetito amagnu mesmatuna maweku; irassun be-Egziabiher Kal mefetenu betam asfelagi new. Behagerachin, beteleyim be-Wongel zuriya, indezih ayinet gira tegabtew gira yemiyagabu bizu sewoch silalu yihin fit-lefit megafetu betam asfelagi ina wessagn new. Yonas Gorfe yemakbrew sew neber - kemakebrew sew gin yezhin ayinet kit-yata tilacha yetemola ina ke-Egziabiher kal gar yemigach, tiwuldin yemiyasasit ina wede-siol yemineda timihirt isemalehu biye asibe alawukim. Ahunim wondime new - gin begola melku mesasatu linegerew yigebal. Andegnawunu irassun hawariya woyinim nebiy adirgo shumo ........................
@dg.sinamosinamo8000
@dg.sinamosinamo8000 8 жыл бұрын
brother i realy appriciate what u said he cant qoute even single word be cause he dont the realy sources from bible just he know what some peoples saying or doing where he was going around ; actualy he is confused by satan look his style
@mimibiruk8657
@mimibiruk8657 8 жыл бұрын
Are kiya. Sewyew Eko be Geta aymesilegim....Yesu melis. Dereje kebede. .Eko zemar otal. .ye pastor dereje kebede mezmur. .gabizew. ..
@asfawBekelepastor
@asfawBekelepastor 8 жыл бұрын
"...በግ ክርስቲያን ዘፈን ቤት እንዲሄድ ተጎትጉቶም አይሄድም። ፍየሉ ግን በግ አይደለምና ቤተ ክርስቲያን እንዲያውም ይደብረዋል። ለቤተ ክርስቲያን ደወል ደንቆሮ ሆኖ ዘፈን ግን ከሩቅ የሚሰማው ፍየል ትውልድ እያረባች ላለች ቤተ ክርስቲያን የምመክረው ምእመናኗን ከበጎቹ እረኛ ድምጽ ጋር ማስተዋውቅ ግዴታዋ መሆኑን ነው። ዮሐ. 10፥ 3-5 በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ይህ ነው ዐቢይ ነጥብ ብዬ ልደመድምበት የምሻው። " ezra litrature
@betheltamiru9196
@betheltamiru9196 8 жыл бұрын
ሠላም የአቶ ዮናስ ይህን ያህል ሙግት ለዘፈን ገርሞኛል ??። ጬኸታቸውን ሦስት አመት በፈጀ እርሳቸው እንዳሉት መፅሐፍ ማተም ሳያንሳቸው ጭራሽ ወንጌላዊው እና ፓስተሮች ሳይቀሩ ዘፈን እዲያበረታቱ፡ ዘፈን ግጥም እዲመለከቱ አልፎም የዘፈን ክበቦች ቤት እፊት ተቀምጠው ሙዚቀኞችን በርቱ እንዲሉ የበለጠ የዘፈን ቤቶች እንዲደራጁ እና እዲበዙ ብለው ያስረዱን እና እንዲሁም የዘፈን ትርጉም ለማሳየት የደከሙበት ብዙ ቁፋሮ ግራ አጋብቶኛል። እንደ ቀላል ሌላ የቤት ሥራ ሰጡን እኮ! ጨዋ እና ዋልጌ የዘፈን ክበብ እያልን ሌሊቱን ሥንዞር እንደር ለመደሰት ??? እደገና ወደ ሌሊት ??? ለማንኛውም ትውፊትም በሉት ሌላ እርስዎ ሊያብራሩት ከሞከሩት 100 እጥፍ ይሻላል ።መደነቅ ያለበት ፈጣሪ ብቻ ።በየምክንያቱ ስሙን እያነሳን እንደሠትበት ቀርቶ ሌላ ዘፈን ይምጣ ??? ገና ዘለአለም ይዘመርለታል የተባለው እንደ ጤዛ በሆነችው እድሜ ዝፈኑ????? 24/7 ለአምላካችን እንዘምርበት።
@የኢየሡሥደምከሀጥያትሁሉያ
@የኢየሡሥደምከሀጥያትሁሉያ 8 жыл бұрын
gud saysema....!!ohh jesus pls maranata .abat hoy bebeth lalenew endekalh senten menor yihunlin.letefut memeles yihunlachew.lalidanu medan yihunlachew
@seyoumsori4112
@seyoumsori4112 8 жыл бұрын
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 3) ---------- 16፤ በእነዚያ ዘንድ ለማስተዋል የሚያስቸግር ነገር አለ፥ ያልተማሩትና የማይጸኑትም ሰዎች ሌሎችን መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህን ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ። 17፤ እንግዲህ እናንተ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ፥ በዓመፀኞቹ ስሕተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፤ 18፤ ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
@genetgashawabebe8768
@genetgashawabebe8768 8 жыл бұрын
Kiya show I like your studio .
@eliyasman6753
@eliyasman6753 8 жыл бұрын
የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚሰማውን ሁሉ አስጠነቅቃለሁ ማንም በዚህ ቃል ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚ መጽሐፍ የተጻፋትን መቅሰፍቶች ይጨምርበታል ማንም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፈው ቃል አንዳች ቢያጐድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፋት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ ዕድሉን ያጐልበታል ። እነዚህን ነገሮች የሚመሰክረው አዎ ቶሎ እመጣለሁ ይላል ። አሜን ጌታ እየሱስ ሆይ ና ። የጌታ የእየሱስ ጸጋ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሁን አሜን ። ራዕይ 22 ; 18 - 21
@sarasisay2712
@sarasisay2712 8 жыл бұрын
Ere geta yeker yebleh. Betkerstiayn weste selalu dekamoch abzeth tenkefaleh.ahun zefnu yemtlen yekrestosen akale letanese new dekamon letabeza. Yedabelsosn hasbe ansetewme megadelachen kedme ena kesega gare aydelm. Mehretu yebzaleh.
@Kininet
@Kininet 8 жыл бұрын
By the way you have said some good things at the beginning of Part 1 about church setting ... No .. No .... wegenotch ... Enkuan yemiyamin. Alemawiwim zefen ena Christina aberew endemayhedu bedenb yawikal. By the way I spent most of my life in US and I used to go to American's evangelical church. Please stop to water down the gospel. The reason I mentioned that is because Amharic Bible is not the only one that say about Zefen. 1 Corinthians 10:31 - "So whether you eat or drink or whatever you do, do it all for the glory of God."The bible has clearly indicated that worldly songs, and drinking are fleshly. In this last days we should practice Godliness more and more ... 1 Timothy 4: 7 - 8. You can almost take any verse and take it out of contest and give it wrong meaning. Egziabheren Memsel yitekmenal."And do not be conformed to this world, but be transformed by the renewing of your mind, so that you may prove what the will of God is, that which is good and acceptable and perfect."Romans 12:2 “And have no fellowship with the unfruitful works of darkness, but rather reprove them.” Ephesians 5:11Wendme - Zefen sigawinet new ... silizihim it doesn't bring glory to God. Romans 8:8 “So then they that are in the flesh cannot please God.” Brother Elyas - I pray that the holy spirit who inspired the writers reveal the truth to you. This is the time that we should seek God more, pray more, and read his word more, worship Him only more and more, we should seek to be confirmed to be in His likeness. Yebelete eyakererin ... Christosin eyemeselin bininor legna melka new.We all know that Zefen, Metet, sexuality, ... and much more they are of flesh. Bottom line ... Zefen is sin, so is drinking.
@beuzulon2113
@beuzulon2113 8 жыл бұрын
እንዴ ዬኒ የዘፈን ወንጌላዊና ፓስተርም ይኑረን እያልክ ነው ???
@number1rko
@number1rko 8 жыл бұрын
yonas tebarek yetergum sehtet new enji zefern hatiat aydelem
@lilyboo7257
@lilyboo7257 8 жыл бұрын
😂😂😂😂😂😂 seyitan hedesh club zifegni wesha ahizab
@zoopla710
@zoopla710 8 жыл бұрын
Yonas Gorfe, thanks for enlightening me! now i will go READ my bible and see if it makes sense.
@dawitjekamo1422
@dawitjekamo1422 8 жыл бұрын
Nisaha giba wondime betam betam tesasitahali tolo balina Nisaha Nisaha giba kalihonama yefiridi keni kerbi newu
@lidiyawinta9961
@lidiyawinta9961 8 жыл бұрын
yikir ybelh egziabeher
@WorkWise-2024
@WorkWise-2024 8 жыл бұрын
ወንድሜ ዮናስ በመጽሀፍ ቅዱሳችን የቱ ጋር ነው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ወይም ሀዋሪያው ጳውሎስ በዜማ የተቃራኒን ጾታ ፤ ሀገርን ወይም ሰውን እንድናደንቅ ያስተማሩት። ለምንስ ዘፈን እንድንሰማ ታበረታታለህ?ለእግዚአብሄር ክብር እንዲበዛለት?መልካም ስራ ከማበረታታት ይልቅ ዘፈን ካለሰማቹ ብለህ ጉንጭ አልፍ ክርክር ማስነሳት ትክክል ነው?
@hanafeleke314
@hanafeleke314 8 жыл бұрын
መጨረሻው ዘመን አካሄድ ነው ትውልድን ማደናቀፍ አዲስ ዘመን እንቅስቃሴ ምንም አታመቻምች።
@yoditmartube5766
@yoditmartube5766 8 жыл бұрын
Er leza yelewem anegageru sga sega yilale getan yawkale gen?
@jihalamagb6425
@jihalamagb6425 8 жыл бұрын
አጉል ልፋት ይሏችኋል እንግዲህ ይህ ነው :- ዘፈንን ለማጸደቅ 20 ምናምን የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ማገላበጥ:: ጥያቄ ለሙዚቀኛ ዮናስ:- ለዘፈን ካሳየኸው ትጋት አንፃር ሲተያይ: የክርስቶስን የማዳን ሥራ ላልሰሙት ለማሰማት ግን ምን ያክል ትተጋለህ? የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋትስ እስካሁን ምን ሰርተሃል? ከዚህ ቃለ ምልልስ የቀረልኝ ነገር ቢኖር: ከንቱ መመላለስ ምን እምደሚመስልና ምን ያክል ለተጠራንለት ክቡር ህይወት የማይመጥን የወረደ ስጋዊ አስተሳሰብ በመካከላችን እንዳለ- ያንንም ለምጽደቅ(በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ) ዮናስ እንዴት አራምባና ቆቦ እንደሚረግጥ ነው:: ሰማሁ ለራሴም ተግሳጽን ተቀበልኩ:: እንዲህም አልኩ:- ይህ ዓይነቱ ንግግር እምነትና መንፈስ ቅዱስ: ፀጋም ከሞላበት ክርስቲያን አንደበት ፈጽሞ አይሰማም:: ከጽጋው ከጎደሉ ሰዎች ሰፈር የሚሰማ ቋንቋ ነው:: ስለዚህ ጌታዬ ሆይ ከጸጋህ እንዳልጎድል የክበረውንም ስምህን እንዳላቀልል ጠብቀኝ:: ኣሜን! የሐዋሪያት ሥራ መፅሐፍ: በርናባስ "ደግ ሰውና መንፈስ ቅዱስ እምነትም የሞላበት ነበረ" ይለናል:: ይህ በርናባስ ታዲያ:- "እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።" ይለናል መጽሐፉ:: የምስቀሉ ፍቅር በዉስጡ ሲሞላ: የተደረገለት ዉለታ ሲጎተጉተው:- ንብረቱን መብቱን በገዛ ፈቃዱ ለሞተለት ጌታ ሲል ተወ:: ለእውነት ወንጌል መላ እሱነቱን ሰጠ:: ይኸው መፅሐፍ እስጢፋኖስን "እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበት ሰው" ይለዋል:: እንኳን ያልተፈቀደውን ከዓለም ሊቀላዉጥ ቀርቶ: ለነፍሱ ሳይሰስት ሕይወቱን ላመነበት እውነት በመስዋዕትነት ሰጥቷል:: ታዲያ የኛዎቹ ዘመናዮች ምንም የለበትም ይሉናል:: ዘና በሉ (የምን መጨናነቅ ነው ደግሞ):- ከዚህኛው ዓለም እየቀላወጡ የዘላለሙን መንግስት መውረስ ይቻላል ይሉናል:: ሁለት ፈላጊ አንዱንም ያጣል እንዳይሆኑ ፈራሁላቸው ብቻ:: ቸር ያሰማን እስቲ
@mimibiruk8657
@mimibiruk8657 8 жыл бұрын
Sewyew betam yemigerim. .tekula. new sholiko yegeba.
@dg.sinamosinamo8000
@dg.sinamosinamo8000 8 жыл бұрын
please yezhi kiya show beteseb ehenin sewuyen amelakaaketun indekeyir belew ende westernochena awuropawiyan kes be kes ewunetun endenlek felego new beterefa afetachenm
@yodityodit6499
@yodityodit6499 8 жыл бұрын
Bro yonas are u ok atimeselegnim wyen rasehin or lesiga michot sitel ye metsfun Ewnet atiberez yehe sewigna ena aganitawi temeheret new mechew manim geta gebitognal ewdewalew yemil sew lezich alem ayezefinim demo egna yeminamelikew endemitasebew ye 5 amet lij adelem aneten bejochu yesera hulun fetari new yesiga megnotin atiketel yehe degimo mebesibesin yametal Lemanignawem gin feten nisaha giba ay kalik gin eske timeret teworedale ke e/hr gar yemitalu yedekalu endemil yehe kal banet yefetsemal feten ke Ewnet gar tesemama!!
@seyoumsori4112
@seyoumsori4112 8 жыл бұрын
" የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2) " እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11:1) you are trying to a knowledge your duties. we are called to magnify our Lord Jesus Christ. Shame on you.
@hanabiranuhana3805
@hanabiranuhana3805 8 жыл бұрын
erf wedm geta mastewalun ysth zefenn yemiyaberetatu pastoroch mechem aynesu beyesus sim yhe ewket/flsfna ayketl legeta kbr yalhone mangnawm muzika hatiyat new
@hanamellese5694
@hanamellese5694 8 жыл бұрын
Amenn
@FocusRBX279
@FocusRBX279 8 жыл бұрын
Yehin Hulu kematrat Lemn kezefen aywetam etetalew gen atsker new emilew endemalet eko new erasin asamemegni uffffffff kalat atahu Egz endit mahari new
@bbyetopia8650
@bbyetopia8650 8 жыл бұрын
ene meleh yone biyonese lalechek ende ?atbey betkirseteyn endetkafet minawu makera balake zefen kalzefenachu beleh?
@mahiafrika7596
@mahiafrika7596 8 жыл бұрын
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 4) ---------- 3፤ የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና። 4፤ በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤ 5፤ ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።
@yeglleshemlis2774
@yeglleshemlis2774 8 жыл бұрын
ሰውየው የራሱን አመለካከት ተናግሯል ግን የፕሮግራሙ አዘጋጅ ግን ምን መልስና በመፅሐፍ ቅዱስ እውቀትና ባለሙያዎች እይታ በምን መልኩ አየው?? ምክንያቱም ለክርስቶስ ተከታዮች ጥሩ የደውል ማንቂያ ነው!
@abiydesta4392
@abiydesta4392 8 жыл бұрын
Right person to wrong place ,need to pray for him 😂
@FocusRBX279
@FocusRBX279 8 жыл бұрын
😂😂😂😂 beaynu yaye rasu amenezere new eko emilew yegelebem yaw so zefenn teru yelewm uff Tera neger yzeh new yetenesahew gen endew lemetewaek ytekmhal 😴😴😴😭😭😭😭
@adiad3072
@adiad3072 8 жыл бұрын
ኪያ ሾዎ የአቶ ዬናስን ንግግር እንደ እግዚአብሔር ቃል ከመቃወም ይልቅ እየደገፍከው ነው! እባክህን የጌታን አሳብ ሳይሆን የጠላትን አሳብ ማስተላለፊያ መንገድ እንዳትሆን ብትጠነቀቅ ጥሩ ነው።
@berhanulibdibakare6338
@berhanulibdibakare6338 8 жыл бұрын
እኔ በጣም ነው የማዝነው እንዲህ መስመር/ልዩነት እንዳይኖረው አድርገህ የተውከው ዘፈንና አካባቢውም አንድ/ብዙ ሰው ነገ ስመቸው አንተ እንዳልከው ኦርጂ በሌላ በኩል ደግሞ ማህበረሰባዊ ዘፈንን እያጣቀሰ መሔድ ለምፈልግ ምን መስመር ታደርጋለህ? ሌላው ደግሞ ኢትየጵያ ውስጥ ለአለማዊ/ማህበረሰባዊ ለሆነው "ዘፈን" ለእግዚአብሔር ክብር የምቀርብን ደግሞ "መዝሙር" የምል ልዩነት ያለው ተደርጎ ነው የምታውቀውና አንተ ችግርህ ምን ስለሆን ነው እነዚህን መቀላቀል የፈለክበት ምክንያት? አዎን በ ኢንግልዝኛ/ በሌሎች ቋንቋዎች እንደዚህ ልዩነት ሳይኖረው ቀርቶ ነገር ግን ስፍራ በመለይት ከእኛ ባልተለየ ሁኔታ ልየነቶቻቸውን ጠብቀው ኖረዋልና አንተ ግን ዘፈንንና መዝሙርን ማገናኘት የፈለክበት ምክንያት የራስህን ጥቅም እያሰብክ ለሌሎች ሕይወት ደንታ ሳይኖርህ ልሆን አይችልም ውይ?
@addisulapiso7288
@addisulapiso7288 8 жыл бұрын
ye ziegnet kber zefen new weys ??????mkniyatum???
@wakeup2503
@wakeup2503 8 жыл бұрын
ቄስ ፍቃዱ ቦረና ለአቶ ዮናስ ጎርፌ ምላሽ አለው ይነበብ -----ቤት ያጣው ቤተኛ ፤ወይስ ቤቱ የጠፋበት ሰካራም----- ‹ሁሉ አይነት ኪነጥበብ፤በተለይም ሙዚቃ ለእግዚአብሔ ክብር ሲውል ማየት እመኛለሁ፡፡› ዶ/ር ማርቲን ሉተር፡፡ ምዕመናን በቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈሳዊ ቅኔ እርስ በርሳቸው እንዲዘምሩ የእግዚአብሔር ቃል የሰጣቸውን ነፃነት በመንፈግ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በመካከለኛው ዘመን ታራምደው የነበረውን ክልከላ በመቃወም እና ሙዚቃን እና መንፈሳዊ ቅኔዎችን በቤተክርስቲያን ውስጥ ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውሉ በማድረግ አሁን ላለንበት የዝማሬ በረከት ፈር ቀዳጅ በመሆን ታሪካዊ ስራ በመስራት የሚታወቀው እና ጥበብን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር ማዋል ጉጉቱ እንደሆነ በመናገር የሚታወሰው የተሀድሶ መሪ ቄስ ማርቲን ሉተር በቤተክርስቲያን እና በሙዚቃ መካከል ስላለው ቁርኝት ስራ ውስጥ ስማቸው በታሪክ ከሚጠራ አባቶች መካከል ዋነኛው ነው፡፡ በሐገራችንም ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የቅዱስ ያሬድ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ቤት ያጣው ቤተኛ በሚል ርዕስ በተፃፈው መፅሐፍ ሽፋን ላይ በቤተክርስቲያን በራፍ ላይ ተገፍትሮ የወደቀ የሚመስል ሰው ስዕል ቢታይም ፀሐፊው ይህ ስዕል ውክልናው ለሙዚቃ ይሁን ለሙዚቀኛ ወይም ለሚሟገቱለት ዘፋኝ እና ዘፈኑ ብቻ ለማናቸው እንደሆነ ለይቶ ለመዳት አስቸጋሪ እንደሆነ የተረዳሁት የመፅሀፉን እያንዳንዱን ገፆች አንብቤ እንደጨረስኩ ነው፡፡ የስዕሉ አስቂኝ አወዳደቅ ደግሞ ዘፈን ቤተኛ ከነበረበት ከቤተክርስቲያን ማንነታቸው ባልታወቀ የዘመኑ ፓስተሮች ወደውጪ ተጎትቶ የተጣለ ማስመሰሉ እና ቤተኛ በሚል ደረቅ ስም መጠራቱ ነው፡፡ በመሰረቱ ዘፈን ቤት አላጣም የራሱ የሆነ ቤት አለው፡፡ ቤተክርስቲያን ዘፈን ተወልዶ ያደገባት ቤቱ ናት የሚለው አስተሳሰብ ፀሐፊው ስለ ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካልነት እና ስጋን ከክፉ ምኞቱ ጋር አውልቀው በሰቀሉ ቅዱሳን የተገነባች የቅዱሳን ህብረት መሆንዋን ያለማወቅ ችግር ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም በፅሁፋቸው ውስጥ ባገኙት አጋጣሚ ቤተክርስቲያንን እና ስርአትዋን ሲዘረጥጡ ይታያልና፡፡ ግለሰቡ ዘፈንን ብቻ ሳይሆን በቁጥር ሁለት ድርሳናቸው /ቤት ያጣው ቤተኛው ስካር/ በሚል ርዕስ መጠጥ ወደ ቤተክርስቲያን ይግባ በማለት ስለመጠጥ እንደሚሟገቱ ጥርጥር የለውም ምክንያቱም በመፅሐፋቸው ገፅ 69 ሶተኛው አንቀፅ ላይ/ ሁሉም የተሓድሶ መሪዎች በመጠጥ ላይ ያላቸው አቋም አንድ ነው፡፡ መስከር እንጂ መጠጣት ኢ- መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብለው አያምኑም/ በማለት ከዘፈን ቀጥሎ መጠጥን አሾልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ለማስገባት ዳር ዳር በማለት ላይ ያሉ ይመስላል፡፡ ለነገሩ ዘፈን እና መጠጥ ታላቅ እና ታናሽ ወንድም በመሆናቸው ቅድሚያ ዘፈን ቦታ ካገኘ መጠጥ ደግሞ በተራው የቤቱን በር ያንኳኳል፡፡ ፀሐፊው ዘፈን ለሚለው ቃል የአማርኛው መፅሐፍ ቅዱስ ከግሪኩ ቃል በትክክለኛው ፍቺው አልተተረጎመም በማለት ሲሟገቱ፡፡ ዘፈን ለሚለው ቃል ትክክለኛው እና ተስማሚው ቃል /ቅጥ ያጣ ፈንጠዥያ/ የሚለው መሆኑን ለማስረዳት ሞክረዋል፡፡ ችግሩ ቅጥ ያጣው ፈንጠዝያ ምንድነው የሚለው ብቻ ሳይሆን ቅጥ ያለው ፈንጠዝያ እንዴት ነው? ቤተክርስቲያንስ እንዴት ነው መፈንጠዝ ያለባት? የሚለውን ጥያቄ በመስመር ለይተው ለማቅረብ ሲቸገሩ እና ከአንድ ዘፋኝ የተወሰዱ ሁለት መልዕክት ባላቸው ዘፈኖች መካከል ስላለው ልዩነት ሊያስረዱን ሲሞክሩ እንጂ እንደ ክርስቲያን በመዝሙሮቻችን ውስጥ ክርስቲያን ሙዚቀኞች እና ዘማሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲያስተምሩ አያታዩም፡፡ ለነገሩ ጥብቅና የቆሙት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት ሙዚቀኞችም ሆኑ ዘማሪዎች ወደ ውጪ በመዝፈን በቅጡ ሳይበዛ እንዲፈነጥዙ እንጂ እርሳቸው እንደ ማስረጃ እንዳቀረቡአቸው የቤተክርስቲያን አባቶች ሙዚቃን እና ሙዚቀኛውን ለእግዚአብሔር ክብር የማዋሉ ጉዳይ እንቅልፍ ነስቷቸው አይመስለኝም፡፡ ፀሐፊው ሐጥያት ተለዋዋጭ ባህሪ የለውም በማለት ለማስረጃነት የሚያቀርቡልን በተለያዩ ዘፋኞች ስለተዘፈኑ በጎ ምክር ያዘሉ በሚመስሉ ግጥሞች ነው፡፡/ ተማር ልጄ ወገን ዘመድ የለኝ ከእጄ፤ ሙሽራዬ የወይን አበባዬ፤/ የመሳሰሉትን ለማስረጃነት ካቀረቡ በውሃላ በድፍረት ከነዚህ የተሻለ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የጋብቻ ዘፈን ይገኝ ይሆን በማለት ይጠይቃሉ፡፡ መልሱ ሞልቶ!! በደንብ እንጂ!!! የሚል ሲሆን በተለያዩ ዘማሪያን የተዘመሩ ድንቅ የጋብቻ መዝሮችን እንደ ቃናው ዘገሊላ ሰርግ ሙሽራው እና ሙሽሪት ብቻ ሳይሆን የጋብቻ መሰረት የሆነውም ክረስቶስ አብሮ የሚደምቅባቸው መዝሙሮች ሞልተውናል፡፡ ወደፊትም ትኩረት በመስጠት እንደዚህ ባሉ ጉዳዮችም ላይ የሚያጠነጥኑ መዝሙሮች ልናበዛ ይገባል፡፡ ወደ ዋናው ጉዳይ ስንመለስ ፀሐፊው ዘፈን የሚለውን ቃል ከተለያየ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በመልቀም ለአላማው በሚመቸው መልኩ ተርጉሞ ትውልዱን ያመከነውን ክፉ መርዝ በቤተክርስቲያን ጉሮሮ ለማጉረስ የሚሞክር አስመስሎታል፡፡ ለመሆኑ መዝሙር /ዘፈን/ ስንል ምን ማለታችን ነው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ግጥም፤ ዜማ እና ሙዚቃ/መሳሪያ/ ማለታችን ሲሆን መንፈሳዊ ለሆንን ለእኛ ደግሞ የመፅሐፉ ደራሲ ልብ ያላሉት እና ተሳስተው እንኳን ሊያነሱት ያልፈለጉት ከነዚህ ነገሮች ጀርባ ስላለው መንፈሳዊ አካል ማንነት እና ድርሻ ነው፡፡ በመሰረቱ ሰይጣን ከዘፈን ጀርባ የለም ብለን ስለተሟገትን አናመልጠውም እንደውም አለ በማለት ከምናደርገው ጥንቃቄ ይልቅ የለም በማለት በምናደርገው ቸልተኝነት ውስጥ ይበልጥ አትራፊ የሚሆነው ሰይጣን ነው፡፡ እስቲ አንዳንድ በፀሐፊው ለማስረጃነት ከተጠቀሱት ጥቅሶች የተወሰኑትን በማንሳት ከታሪካቸው አንፃር የግጥማቸው ይዘት ምን ሊሆን እንደሚችል ከአውዱ እየተንደረደርን እንመልከት፡፡ በመቀጠል የምናያቸው ጥቅሶች በፀሐፊው ድርሰት በገፅ 156 ላይ የቀረቡ ናቸው፡፡ 1/ እስራኤል ድንግል ሆይ እንደገና እሰራሻለሁ አንቺም ትሰሪያለሽ፤እንደገናም ከበሮሽን አንስተሸ ከዘፋኞች ጋር ወደ ዘፈን ትወጫለሽ፡፡ኤር 31፤4 በዚህ ክፍል ለእስራኤል ድንግል ከበሮን አንስቶ ለመዝፈን/መዘመር/ መሰረታዊ ምክንያት ምን ነበር ብለን ራሱን ክፍሉን ብንጠይቀው የወንድማችንን መልስ ባላውቅም ትክክለኛው መልስ የሚሆነው የወንድ ወዳጅዋ ቁመና ውበት እና ቁንጅና ሳይሆን በሐጥያት እና በአመፃዋ ምክንያት ደርሶባት ከነበረው ስጋዊ እና መንፈሳዊ መፍረስ በእግዚአብሔር ምህረት ዳግመኛ በመሰራትዋ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ ይህ ምላሽ ካስማማን በእግዚአብሔር ምህረት ታግዞ ከውድቀት የተነሳ ሰው ሊዘፍን/ሊዘምር/ የሚችለው አምላኩን ማድነቅ እንጂ የቴዲ አፍሮን ነይ ማታ ማታ የሚለውን መዝሙር ሊሆን እንደማይችል እሙን ነው፡፡ 2/ የአሮን እህት ነብይቱ ማርያምም ከበሮን በእጅዋ ወሰደችሴቶችም ሁሉ በከበሮ እና በዘፈን በኋላዋ ወጡ፡፡ ዘፀ15፤20-21 ስለዘፈን ተሟጋቹ ፀሐፊ በዚህ ክፍል ውስጥ ሊለን የፈለገው ነብይቱ ማርያምም ዘፍናለች ነው፡፡ የሚገርመው ጉዳይ ማርያም ምን ብላ ዘፈነች ተብሎ ክፍሉ ቢጠየቅ መልሱ ደራሲው እየበጠበጠ ያለውን መርዝ በግልፅ የሚያረክስበት በመሆኑ በመፅሐፉ ላይ ክፍሉን ቆርጦ አስቀምጦታል፡፡ ዝፈኑ ባዩ ደራሲ የክፍሉን ምእራፍ እና ቁጥር አስፍሮ ነገር ግን ቆርጦ ያስቀረው ምንባብ እንዲህ የሚል ነው፡፡ ‹ ማርያምም እየዘመረች መለሰችላቸው፡፡በክብርከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔርዘምሩ፤ፈረሰኛውን በባህር ጣለ፡ዘፃ15፤20-21 እንግዲህ እውነታው ይህ ቢሆንም ወንድማችን ነብይቱን ማርያምን እርሱ የመሚሟገትለትን ዘፈን እንደዘፈነች በማድረግ ነብይቱን አዝማሪ ሊያደርጋት ቢሞክርም እርስዋ ግን ለእግዚአብሔር ዘምሩ በሚል ቅኔ ባህሩን በመክፈል ተአምር ለሰራው ጌታ ዘፍናለች፡፡ አሁንም ወንድማችን በጠቀሰው ክፍል የእግዚአብሔርን ቃል የበላይነት የሚያምን ከሆነ ማርያም ለእግዚአብሔር ዘምር!! የሚል ጥሩ ምክር ያስቀረችለት ይመስለኛል፡፡ 3/ ዳዊትም በሙሉ ሓይሉ በእግዚአብሔርፊት ይዘፍን ነበር፡፡2ሳሙ 6፤14 ወንድማችን ዘፈን የሚለውን ቃል ከእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በመልቀም ሊያስቆጥረን ቢሞክርም ደፍሮ ሊነግረን ያልቻለው በእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ምን ተብሎ ተዘፈነ የሚለውን እውነታ ነው፡፡ ንጉስ ዳዊት በህይወቱ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የዘፈናቸው ዘፈኖች ምንነት በእጃችን ባለው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍረው እናገኛቸዋለን፡፡ ታዲያ ይህ ደራሲ ዋና አላማው የነ ጥላሁን ገሰሰን፤ ቴዲ አፍሮንና እርሱ የሚያዳምጣቸውን ሌሎችን ዘፋኞች ዘፈን የክርስትና ስም ለማስነሰሳት በሚሟገትበት መፀሐፍ ውስጥ የዳዊትን ግጥም እና ቅኔ ለማስረጃነት ለማቅረብ መድፈሩ ደፋር ባያስብለውም ብልጣብልጥነቱን ግን አጋልጦበታል ምክንያቱም ዳዊት በእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላ ፤እንደልቤ ተብሎ በመለኮት ሚዛን ተመዝኖ የከበረ ዘማሪ እንጂ ከነ አሳ በለው ተርታ የምናሰልፈው ተራ አዝማሪ አይደለምና፡፡ 4/ ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ የሄሮድያ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፡፡ማቴ 14፤6 እንደሚታወቀው ወንድማችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልቀም የፈለገው ዘፈን የሚለውን ቃል ቢሆንም አላማው በአለም ያለውን ዘፈን በብልጠት እያስከፈተ ባለው የማርያም መንገድ አሾልኮ ወደ ቤተክርስቲያን ማስገባት እንደሆነ የመፅሐፉ ጭብጥ ያስረዳል፡፡ እርሱ ከላይ በጠቀሰው ክፍል ውስጥ ዘፈን የሚለውን ቃል ብቻ እንድናይለት ቢፈልግም መጠየቅ ያለበት ዋና ጉዳይ ምን ተዘፈነ የሚለው ጉዳይ መሆን ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡ በመሰረቱ በዚህ ክፍል ውስጥ የዘፈኑ ምክንያት የሄሮድስ ልደት መሆኑ እና በተዘፈውም ዘፈን መደሰቱ የሚያስረዳን የዘፋኝዋ የዘፈን ግጥም ንጉሱ ሄሮድን የሚያሞካሽ መሆኑን ሲሆን በተጨማሪም ዘፋኝዋ የሚስቱ የሄሮድያዳ ልጅ የተዘፈነለት ደግሞ ሮማዊው ንጉስ መሆናቸው በራሱ የሚሰጠን ግልፅ መረጃ አለው እርሱም ሰዎቹ አህዛብ እና እግዚአብሔራዊ ህግ የሌላቸው መሆናቸውን ነው፡፡ የዘፈኑም ፍፃሜ የዬሐንስን ጭንቅላት ማስቆረጥ ነበር፡፡ ደራሲው የዬሐንስን ጭንቅላት ያስቆረጠችው ልጅትዋ እንጂ በቦታው መዘፈኑ አይደለም በማለት በመፅሐፉ ውስጥ ለመከራከር ሞክሮአል ይሁን እንጂ የልብዋን ክፋት ለማስፈፀም የተጠቀመችበት ብቸኛው መንገድ ዘፈን መሆኑን ለመደበቅ እና ለመጋረድ የዘረጋው መጋረጃ አልበቃ ብሎት መቸገሩን የሙግቱ ጭብጥ ያስረዳል፡፡ የደራሲው ሌላ የመከራከሪያ ሀሳብ ደግሞ ዘፈን የእግዚአብሔርን ክብር አይሸፍንም የሚል ሲሆን ‹ ወላጆቼን አከብራለሁ ስላልኩ አምላክ ከሰማይ ሆኖ ክብር ሁሉ የእኔ ነው ክብሩን ሁሉ ጠቅልለህ መስጠት ያለብህ ለእኔ ብቻ ነው ብሎ መልአኩን ልኮ አንገቴን አይቀነጥሰውም› በማለት እንደ ሕፃን ልጅ ሊያታልለን ይሞክራል፡፡ ለመሆኑ ወላጆህን አክብር በማለት ከሁሉ ቀድሞ ያዘዘ እግዚአብሔር ትዕዛዙ በመከበሩ ተናዶ አንገት ሊቆርጥ እንደሚነሳ የሚያስብ አማኝ እንዳለ አድርጎ ማቅረብ ንቀት ቢሆንም ቤተክርስቲያን በዘመናት መካከል በትጋት ከምታስተምራቸው መሰረታዊ ትምህርቶች መካከል እርስ በርሳችን መባበር እንደሚገባን እና ክብር ለሚገባው ሁሉ ተገቢውን ክብር መስጠት እንደሚገባ የምታስተምረው ትምህርት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሙግታችን በመፅሐፉ ገፅ ላይ እንዳለው ስዕል ከቤተክርስቲያን በራፍ ውጪ ተገፍትሮ የተጣለውን ሰዋዊ እወድሻለው እና እወድሃልው ፆታዊ ቅብብሎሽ እንዴት አድርገን በቤተክርስቲያን መሰዊያ ላይ ደጋግፈን እንዲቆም እንርዳው የሚል ነው፡፡ ቤት ያጣው የነ መሐሙድ አህመድ ዘፈን ቤቱን ይፈልግ እንጂ በክርስቶስ ሙሽራ መድረክ ላይ የሚቆምበት እግር የለውም ባይ ነን፡፡ በጣም የሚገርመው ወንድማችን / ወንድም ከሆነ/ ከዘፈኖች መካከል እየመረጠ ሊያባብልበት የሚሞክረው በደጋግ ቃላት እና በሐገራዊ በጎ ታሪኮች ላይ ያተኮሩትን የዘፈን ግጥሞች በማስረጃነት በማቅረብ መሆኑን ስመለከት ስለ ፀሐፊው የተረዳሁት ነገር በትክክል ዳግም የመወለዱን ጉዳይ ነው፡፡ በቃ ይህ ሰው ትክክል የተነገረ ቃል ሁሉ እግዚአብሔራዊ የሚመስለው የዋህ ይመስላል እርግጠኛ ነኝ በፊሊጲሲዩስ ከተማ የሟርት መንፈስ ያለባት ሴት ስለ እነ ጳውሎስ እውነተኛ አገልጋይነት በትክክል ስትናገር ቢሰማት ነብይት እንትና በማለት ጥሩ ንግግርዋን ብቻ ተከትሎ በቤተክርስቲያን ውስጥ በነብይነት ሹመት ካልተሾመች የሚል ሙግት የሚገጥም ሰው ይመስላል፡፡ በመፅሐፉ ውስጥ፤ መርቆ ሸኝቶ ሐገር አስይዞ ሰንደቅ አላማ መርዶ ነው ለወገናችን ማሸነፍ ካቃተንማ የሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን ለማስረጃ ቀርቧል፡፡ በማያያዝ ነይ ማታ ማታ የሚለውን የራሱን የቴዲ አፍሮን ግጥም ለማቅረብ አልደፈረም፡፡ ለምን? የሚለው ጥያቄ ይቆይ እና ፀሐፊው ይህንን ዘፋኝ ቤተክርስቲያን ቤት አልባ አድርጋ ወደውጪ መወርወር የለባትም በማለት ለመሟገት ያበቃው ግጥሙ ነው ወይስ የዘፋኙ መንፈሳዊ ማንነት? የሚለው ጥያቄ ቅድሚያ መልስ ማግኘት ያለበት ይመስለኛል፡፡ መቼም በደጋግ ግጥሙ ዘፋኙን ወደ ቤተክርስቲያን አስገብተን ነይ ማታ ማታ ሲል ደግሞ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ ብለን ከበር ውጪ በማቆየት ግለሰብን እንደ ግጥሙ አይነት በፈረቃ እንጠቀምበት እያለን ይሆን? ለእኛ አማኞች ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ በመንፈሳዊነት እና በአለማዊነት መካከል፤ በመዝሙር እና በዘፈን መካከል ፤ በዘማሪነት እና በዘፋኝነትም መካከል ሰፊ ልዩነት እና ገደብ አለ ብለን ማመናችን ሲሆን ከሁለቱ ክልሎች መርጦ ማንኛውም ግለሰብ ወደፈለገው ራሱን መቀላቀል ምርጫው መሆኑን እንረዳለን፡፡ እንደ ቤተክርስቲያን ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ መሞዘቅን፤ መቀኘትን፤ መዘመርን ምርጫችን በማድረግ ለዚሁ አላማ ብቻ እንዲውል ቤቱን አፅድተነዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ምርጫችን ሊከበርልን እና ለዘፈን እና ለዘፋኙ የሚሆን ቦታ እደሌለን ቤት ያጣውም የዮናስ ጎርፌ ዘፈን ቀድሞውንም ቤተኛ ስላልሆነ ወይ ቤቱን ይፈልግ ወይ መስቀሉን ተሸክሞ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ለመፈንጠዝ ከወሰነ አምኖ ተጠምቆ ቤተኛ የመሆን እድሉን መጠቀም ብቸኛው አማራጭ እደሆነ እንመክራለን፡፡ በመጨረሻም፤ ዶ/ር ማርቲን ሉተር የፕሮቴስታንቱን የወንጌል ዕሳት ለማቀጣጠል በክርስቶስ ኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ላይ ያለውን ቁርጠኛ አቋም እንዲለውጥ ከተቃዋሚዎች ለቀረበለት አስፈሪ ትዕዛዝ ስለወንጌል እውነት ሲል በፅናት እና በድፍረት ሐሳቤን አልቀይርም ውጤቱ ሞትም ከሆነ ይኸው በፊታችሁ ቆሜያለሁ በማለት የተናገረውን የፅድቅ አቋም መግለጫ ከዘመናት በውሐላ ዘፈን ሐጢያት አይደለም የሚል አቋም ይዞ በሉተር ካባ ቅበሩኝ ማለት አጉል ጀብደኝነት ወይም በገበያው ውስጥ ዋጋ ለማውጣት በበሬው ቆዳ ላይ ተጣብቃ እደተሸጠችው መዥገር መሆን ይመስለኛል፡፡ ፍቄ ዘሉትራን ይቀጥላል፡፡
@jesuslovelove703
@jesuslovelove703 8 жыл бұрын
yonas ene ka ant gar cheger ylegnm temertkenm zare new yesemawet, gen be geta be eyasus sem yeh temert kemder gets yetefa
@hanamellese5694
@hanamellese5694 8 жыл бұрын
Amenn
@emushbekele2777
@emushbekele2777 8 жыл бұрын
Ere E/r hoy. Ende kalek anuren ke kalu wech menore yehunben Kezefen. Gare. Men mategagate new Beyesusim. Anekebelem 🙅
@ክብርለኢየሱስክርስቶስይሁ
@ክብርለኢየሱስክርስቶስይሁ 8 жыл бұрын
ዘፈን ኃጢአት አይደለም አልክ አቶ ዮናስ? ዘንድሮ ገና ጉድ ይሰማል ዘሩት ከበደ የአንተን መጻሐፍ አንብበ ይሁን እንዴ ኢየሱስ ዘፈን ይወዳል ያለችሁ; ኧረ እባከችሁ አታሰድቡን kiya ግን ከአቶ ዮናስ ምን እንድንማር ነው በሾው ያቀረብከው ? ለማንኛውም የመጨራውን ሀሳብ መስማት እፈልገለሁ part 3 እንጠብቃለን ደግነቱ እሄንን ሁሉ ጉድ እየሰማ ጆሮችን ምን አይሆንም
@segenetsegenetlassaye936
@segenetsegenetlassaye936 8 жыл бұрын
ዘፈንን እንደ እግዚያብሄር ፓስተሩን ያስመርምር ይሄ ሰውዬ ችግር አለበት ንስሀ ያስፈልገዋል መፅሀፍ ቅዱስ የጠቀሰ ሁሉ በጌታ ነው አይባልም
@hadumuhur261
@hadumuhur261 8 жыл бұрын
ይህ interview ኣስፈላጊ ኣይደለም ። ለምን ግን ግዝየ ትሰጣላኣቸው በጣሚ ኣሳዛን ነው
@jesuslovelove703
@jesuslovelove703 8 жыл бұрын
kiyya endzi aynet ya ant show lay makereb tenesh leteweldu terunew belek tasebalh
@mihartabtaye7870
@mihartabtaye7870 3 жыл бұрын
cherch west mezelel be serat alemezemer & bibeln alemastemar new ket yata fentezeya malet hahaaa...
@hanafeleke314
@hanafeleke314 8 жыл бұрын
እባክህ የፕሮግራሙ አቅራቢ ሌላ የሚያንፅ ትምህርት ብታቀርብ ማስተዋል ይስጥህ
@tadelechworku2624
@tadelechworku2624 8 жыл бұрын
Brothers and sisters, cursing each other is not glorify God .if you have a knowledge to confront put the right word, read your comment it is not godly way let us be machu rd when I say this I am not justify his opinion, but beyond that, I want Love and pray for him . however he is ower brother because of he belive in christ ,we are called to Love even ower enemy this man is not , yes we have to corect one to another it has to be marinated with Love , that should be done wisely . our disagreement should not destroy our Love. You can agree on your disagreement, with out compromise what we believe, this media is a gift from God , let us glorified God with it and let us atak the problem not the person.
@illasha
@illasha 8 жыл бұрын
Thank you kiya! Thank you Yonas Gorfe! leave them all ... Truth hasn't signed for any group. Let them shout... they are loud, you are true.
@jesuslovesyou8508
@jesuslovesyou8508 8 жыл бұрын
zefen bemegemeriya hatiat new weyis aydelem teblo wuyiyit wust yemigeba neger aydelem....rome:-12 lay endi yilalal yeminetachinin fetsami yehonewun kirstosn eyayen ruchachinin betigist enirut yilal....enkias kirstosmislaiyachin kehone yet ga new lehageru yezefenew hagerachu besemay new ale engi....endante ababal kehone kidus zefen yemibal neger ale malet new😂....mangnawum legizabiher kibr yalhone zema hulu zefen new minim belela kuanka mayet ayasfeligim even orthodox bitil musilim hatiyat mehonun bedenb yawkalu pls ante tesasiteh lelawun wede sihitet menged endigeba atarg miknaytum kirstos leyandandu min yahil waga endekefele bitawuk yihen lemenager difret balhoneh sint yemiwera neger eyale kiya antem bezi hasab meweyayetih agbab aymesilegnim miknaytum begta adis lehone sew mesenkil enji yemiyanitis neger yelewum.....e/r yibarkachu
@HananMohamed-ge5wm
@HananMohamed-ge5wm 8 жыл бұрын
ersachehun chalu muselimen ateteru enate menamenamoche
@segenetsegenetlassaye936
@segenetsegenetlassaye936 8 жыл бұрын
እኔ ያልገባኝ ነገር ሰውዬው በጌታ ነኝ እያለ ነው ቆይ እንዴ እያበረታታ እኮ ነው ስለ ሙዚቃ ስለ ዘፈን መዝናኛ ነው እያለ እንዴ ብዙ ዶክተር ይቅማይ so what? መቃምንም ከምን ጋር ልታያይዝልን ይሆን
@abrahamlakew1221
@abrahamlakew1221 8 жыл бұрын
Go to Anthropology of "Zefen" not to English Context or meaning. Western context can not interpret Ethiopian understanding. "Zefen" is not just a word it is big concept. As a word you are right but as a concept we need to go deeper. Together with all other mentioned in Galatians" Zefen" is clearly sin no compromise. I said "zefen" in Semitic context as a whole.
@lemimilion5908
@lemimilion5908 8 жыл бұрын
በጣም ያሳዝናል ቃሉን እንደሚመችህ ነው የምታጣምመው ዬናስ ተብዬ አጉል ፈላስፋ ሲጀመር የዘፈን አግባብ ምን አለውና ነው ? -ባግባቡ እስከሆነ ድረስ የምትለው ? እግዚአብሔር ማስተዋል ይስጥህ ትውልድን የምታጣምም
@jesuslovelove703
@jesuslovelove703 8 жыл бұрын
be eyasus sem
@mekedsalemu522
@mekedsalemu522 8 жыл бұрын
እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስንጥህ.
@mahitilahun9207
@mahitilahun9207 8 жыл бұрын
are you really serious???
@Kininet
@Kininet 8 жыл бұрын
Geta Yishalenal ... ! Ke esu yemileyen hulu yikir. Lelela masenakeya dingay anhun ... Paulos enkuan Wendimen yemiyasenakle kahone siga enkuan yikribign bilual. Enkuan clearly yetenegere hatiyat ... Metew kalebin legeta kibir bizu eyetewin ... enakebrewalen ... Wedechelema Alimelesim ... Alem Kehula ... Meske Kefite ...No more ... No more Worldiness ... We are the son and daughter of the king of kings. Children of the most high God, we are not going to look for places to see if they have decent "worldly Music"... for what ... Be Eyesus erektenal ... Medanachin Yibekanal ... Enkuan zefen ... Metew Kalebin bizu entewalen. Beyekenu Lekiristos enisekelalen ... new yemilew kalu.Don't be deceived guys ... read the word of the living God. No matter who says it, let His word "Bible" be your final say. If you have doubt ask God to reveal His word for you. Egziabhere Yirdan. Wendme Yonas ... Geta Yikir bay new ... I pray that you come before God and ask Him humbly to reveal His word to you. He will. He will forgive.In Him,
@እየሱስያድናልብቻውንያድና
@እየሱስያድናልብቻውንያድና 8 жыл бұрын
አቶ ዮናስ ዘፈን ሀጥያት አደለም ብለሀል ለአተ ሀጥያት ካልሆን እራስህን ዋልበት እኛ ግን ሰይጣን አንስተውም እናውቀዋለን በዘመን መጨረሻ አተ መጠቀመያህን አድርጎሀል አምልጥ ተጠንቀቅ ወዳጅህን ሲኦል እንዳይከትህ እሱ ከዛውጪ ሽልማት የለውም
@zeleketemesgen5439
@zeleketemesgen5439 8 жыл бұрын
This is one of the most ridiculous programs I have ever seen. You should have kept in mind that this is a spiritual program that is viewed by a number of Christians, men, women, youth and children, all over the globe. You should have done a background check on the people you invite on your show; especially with regard to their relationship with Christ, knowledge of the word of God and spiritual maturity. The man you invited here is lacking in all respects.
@wakeup2503
@wakeup2503 8 жыл бұрын
He only knows verses that are related to ''zefen" that is why he described him self "maseb yamal" when he start to talk about the scripture he even never say one scripture correctly...."mared meklat...mekuret...kkkkk" He is tough when he starts to quote about zefen....No offense to call him son of Lucifer. Because if some on is not a child of God by default he is child of Satan; No third option.
@bekrihassen4433
@bekrihassen4433 8 жыл бұрын
ሴጣን እራሱ "ኽረ ሼም ነው ብሎ ከንፈሩን አንሻፎ ሲያልፍ" አየሁት
@tigistshewaamare4158
@tigistshewaamare4158 8 жыл бұрын
I DONT THINK YOU KNOW ABUT bible so read your bible very well before write book you are funny
@nainegash3172
@nainegash3172 8 жыл бұрын
hiwet yegel selehone bechahn teguz abreh lila lemechemer atetar ok mknyatum ke enezih ketenanshoch andachewn yemiyaset weyewelet yalew gita new selezih yehi men yemilut megelet new yehi semith new semithn teteh yedankebetn kedusun menfes semaw hatiyat hatiyat new beand egr hulet bota aychalm mekedesh yawatahal hatiyat bedejh tadebalech ena feteneh negesebat yalezia tekedemhalech
@retashersher798
@retashersher798 8 жыл бұрын
የበግ ለምድ ለብሰዉ ከሚመጡባችሁ በዉስጣቸዉ ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑት ተጠበቁ ቃሉ ማንም ሳይተረጉመዉ እዉነተኛ ነዉ የእግዚያብሔር ቃል ማስተካከያ አያስፈልገዉም ዘፈን ሀጥያት ነዉ ዘፋኝ መንግስተ ሰማይ አይገባም። እኛ አንዘፍንም እንዘምራለን ለእግዚያብሔር ክብር ጌታ እየሱስ ይቅር ይበልህ ወደ እግዚያብሔር ተመለሱ ብለህ ፃፍ
@beletusheno8596
@beletusheno8596 8 жыл бұрын
geta eyesus ykr ybelk ante satawkew yelusifer melktegna honehal geta ytadegh
@እየሱስያድናልብቻውንያድና
@እየሱስያድናልብቻውንያድና 8 жыл бұрын
እኔ የክርስቶስ ጠላት አልስማህም
@tics-ethiopia
@tics-ethiopia 8 жыл бұрын
I have seen part 1 & 2 of this show what i understood is one the show host has limited Biblical knowledge that is why he just accept all the mislead man talking, the other thing is the music person stick to only Gelatian 5:-21 In hermetic we couldn't interpret by pointing a single verse instead one step before and one step after even we can refer the whole chapter, the whole book of Gelatian or the whole content of the bible also the time which the book writer refers, in my opinion this man has gone far away from Truth because Bible says Don't love the world and the content in it because the content in it is the lust of eyes and flesh. so what we call ZEFEN is part of this what ever we consider the poem we have given the holly spirit to reach all good ideas not ZEFEN because this guy advice to church leaders to consult youngster what kind of ZEFEN they should play and where they should go to enjoy ZEFEN it is very funny and devilish. One thing we all should know Every Good words are not God words But Every God Words are good Words so lets stick to the guidance of Holly Ghost instead of "Good ZEFEN"
@solomongizaw7299
@solomongizaw7299 8 жыл бұрын
Ayyyyy Yonas, "Pasterochachin zefen sansur madreg yijemiru" alk? "Iyandandun zefen inde Egziabiher kal ayito......?" "Club wust yeChurch lijoch muzika sichawetu kefit kuch bilo yadamtu alk?"? My brother, for some reason I always like you and appreciate you as a person, but I really X really pity you. I am utterly disappointed about your confused state of mind, your anger filled exaggerated view of zefen and about your misguided assumption of other people's views. Ante indalkew, "kemimer medhanit wust dehininet ligegn yichil yihonal." Betilacha wust gin medhanit yelem. Ye-Amarigna Metshaf Kidu tirgum wrong, Qwanqwanchin wussin, Evangelicals yetesastu ina masseb yemaychilu (why we need critical thinkers like you), le-DV medeges wrong. My brother, you should not have hate rule your thinking as you mislead the young and the confused. I would be highly disappointed if your book, "BETU YETEFABET" is your only contribution to the new generation; to the work of the Kingdom and your final gift to the world. As much as I appreciate your contribution to Church music (before you became Critical Thinker), I hope you would revisit your skewed view and redeem the generation through obedience and love. The love of our Lord and Savior Jesus Christ. For someone who claims to know so much about the whole world I am somewhat surprised that your translations are vague, designed only to serve the point you are dying to make. Hey man, nothing else, but still love wins!
@dg.sinamosinamo8000
@dg.sinamosinamo8000 8 жыл бұрын
he is caring about for those who west money not for the truth and for white peoples behalf . please if he is confused he must come to me i can explain more (dgs from pretoria theology student ).
@nainegash3172
@nainegash3172 8 жыл бұрын
kkkkkkk er tesh efer aydelem be kerstos amna yedanech bitkerstiyan west ortodoxm aychalm man lekoh new metfatm selale melse bel astewel wedmachn er ooooooo endia zefen leman lemn areka alk begitah badangh mnew mn nekah gita aymerohn yeelsew
@nainegash3172
@nainegash3172 8 жыл бұрын
matiwos15:20 seleIH yenageral anbebew yehatiyat tensh telke tensh yelem gitan yemayamakel bemngot besemit yehonew hulu yesega feri hulu hatiyat new mot alebet hatiyat new hatiyat new mashshaya yelewm
@jesuslovesyou8508
@jesuslovesyou8508 8 жыл бұрын
ena demo bemezefenachinis yeminagegnewun tikims mindin new? kesiga desta lela yemisetew desta yale aymesilegnim...tadia ante zefen hatiyat aydelem bileh lezefen tebeka enditkom yaderegeh mikniyat giltse alhoneligim....e/r gosh lijochen bezefen rasachewun endiyastesitu adereglign yemilih yimesilihal....mn ale endezi kirikir wust kemegibat bayzefenis....yihe fitsum yehast timihirt new ewunet legizabiher tekorkureh bihon sew e/r kemitelachew(hatiat)neger hulu endirik tinageraleh enji mn alebet zefen binzefin bileh atastemrim.....endezi aynet astesaseb satawik new lemalet bikebdegnim ebakihin gn ante tesasiteh lelelaw sihitetin atastemir....bizu endante andebetachew ende ebab milas(yihen sitekem aznalew) yetesale maninim masamen yemichilubizu sewochin awkalew pls gn ewunet getan emitwedew ena yemitiferaw kehone yihen timihirt akum.....belela ababal lehatiat 1 ermiga wedefit kirebu eyalk new enkuanis sewun endezi bilehew endihum gimash geta bet gimash demo alem wust new yalewna yibas demo mesebakil atihun demo geta sile 1 nefis metfat endemiteyikih atirsa
@sarahmulu6475
@sarahmulu6475 8 жыл бұрын
ደሞ ፓስተሩ ስለዘፈን ያታራ ነው የምትለው ኦኦኦ ኣሳፋር ነው
@hlawe
@hlawe 8 жыл бұрын
This is parallel spirit God forbid in Jesus name
@amanuelgizaw5557
@amanuelgizaw5557 3 жыл бұрын
የዮናስ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ የምስማማበት ነው።
@danielyohanes6651
@danielyohanes6651 8 жыл бұрын
Agents of satan
@Elshadai-A
@Elshadai-A 8 жыл бұрын
betam yigermal ! zefen hatyat aydelem? chirash le wengelawyan ena le pasteroch sayker beye Clebu ena beye concertu eyehedu endiketatelu yemiasgedid mikir ! I don't think this kind of advice is from God's spirit,
@danielyohanes6651
@danielyohanes6651 8 жыл бұрын
ኢየሱስ ሆይ እባክህ ተመልሰህ ና ! ከዚህ የባሰ ምን እንስማ !!!
@መልካምምኞት
@መልካምምኞት 8 жыл бұрын
ምኑን አሰማኚ ኮንሰርት ደሜን ያፈለኛል አልክ እኔን ደም አንተነህ ደሜን ያፈላህ ማንም አይሰማህም ዘፈን አያዝናም በጣም ተሳስተሃል ዎዮልህ ሠዉን እያሰናከልክ ነው ያለምን ነገር ከወደድክ እዛው ተዘፈቅ እኛን ለቀቅ ።
@masiyegetalijemasiyegetali5505
@masiyegetalijemasiyegetali5505 8 жыл бұрын
Are geta yikirayibal gizadiromidinow misamawi geta yitabiqani baiwinat batmi yasifaral kazfamalkamine nagara miyiganl wodimachi baiwinata getayikiyibal gina zafani geta idetilawodiyichilal nagaru yemacarshi zamnicalhonanow ateawqayayidelami idazyalako
@asmerettekie8105
@asmerettekie8105 8 жыл бұрын
My God sorry ehi ye setan melekt new ,srahn metew kalfeleg lante ymeleketal gn,sewn massat atchlm.zefen zefen new hulum zefen setann new yemyageleglut,antem zefen yemtketel kehone botah ateratari new
@yeglleshemlis2774
@yeglleshemlis2774 8 жыл бұрын
ይቅር ይበልህ !እኛ ተመችቶናል አማርኛው ትርጉም ።በየትኛውም የሀይማኖት ተቋም ዘፈን ፅድቅ ነውየሚል የለም።።ትውልዱን አታስት ።ቢቻልህ ንስሀ ግባ።።።
@mesayte174
@mesayte174 8 жыл бұрын
የተምታታ ሃሳብ.....ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ የሌለው ሰው...መጽሃፍ መጻፍ ሲችል ገረም ይላል!!!!!!!! ዘፈን ሃጢያት ቢሆንበት ይገርመኝ ነበር...ሰውዬው ባዶ ነው!!!
@eyobachen
@eyobachen 8 жыл бұрын
takes a strong man to do this... ትልቅ ሰው ነህ። ኮርተናል
@mahiafrika7596
@mahiafrika7596 8 жыл бұрын
በጣም የምትገርም ብለክ ቃሉን ልታሥተካክል ፈለክ አንተ ሁለተናው መሀመድ ነክ የትንቢት መፈፀሚያ ነክ ይቅር ይበልክ
@ሀብትነሸእዩሱሰ
@ሀብትነሸእዩሱሰ 7 жыл бұрын
Mahalet እውነትሽ'መረ'ማይት'አሲጣላኛ
coco在求救? #小丑 #天使 #shorts
00:29
好人小丑
Рет қаралды 120 МЛН
Гениальное изобретение из обычного стаканчика!
00:31
Лютая физика | Олимпиадная физика
Рет қаралды 4,8 МЛН
Что-что Мурсдей говорит? 💭 #симбочка #симба #мурсдей
00:19
Yonas Maynas - WEDI SHUQ 4 (Full Video) - Eritrean Comedy
40:12
Yonas Maynas
Рет қаралды 2 МЛН
Tamsaasa Guyaadhaa Guyyaa
29:16
VOA Afaan Oromoo
Рет қаралды 5 М.
Amharic Audio Bible Psalms - Ethiopian Amharic Bible Reading
3:48:29
Amharic Mezmur & Amharic Bible
Рет қаралды 325 М.
ዮናስ ጎርፌ - ምን እንጠይቅልዎ | Hintset
42:13
coco在求救? #小丑 #天使 #shorts
00:29
好人小丑
Рет қаралды 120 МЛН