🔴 የሰው ተከታይ አትሁኑ || አንደበቱ ተከፈተ || እጅግ ድንቅ ትምህርት ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ | Aba Gebrekidan Grma New

  Đ ĐľŃ‚ қаралды 244,478

ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi

ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi

28 күн бұрын

ሉቃስ 1
ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ
⁵ በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
⁶ ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።
⁷ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜያቸው አርጅተው ነበር።
⁸ እርሱም በክፍሉ ተራ በእግዚአብሔር ፊት ሲያገለግል፥
⁹ እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።
¹⁰ በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር።
¹¹ የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።
¹² ዘካርያስም ባየው ጊዜ ደነገጠ፥ ፍርሃትም ወደቀበት።
¹³ መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።
¹⁴ ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።
¹⁵ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና፥ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ገናም በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል፤
¹⁶ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል።
¹⁷ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ፥ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጻድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል።
¹⁸ ዘካርያስም መልአኩን፦ እኔ ሽማግሌ ነኝ ምስቴም በዕድሜዋ አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ? አለው።
¹⁹ መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤
²⁰ እነሆም፥ በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ መናገርም አትችልም አለው።
²¹ ሕዝቡም ዘካርያስን ይጠብቁት ነበር፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ስለ ዘገየ ይደነቁ ነበር።
²² በወጣም ጊዜ ሊነግራቸው አልቻለም፥ በቤተ መቅደስም ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ።
²³ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሄደ።
²⁴-²⁵ ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና፦ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች።
²⁶ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥
²⁷ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።
²⁸ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ፦ ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
²⁹ እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና፦ ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።
³⁰ መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
³¹ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
³² እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤
³³ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።
³⁴ ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው።
³⁵ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
³⁶ እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
…
³⁸ ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
³⁹ ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥
⁴⁰ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
⁴¹ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
⁴² በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
⁴³ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
⁴⁴ እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
⁴⁵ ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
⁴⁶ ማርያምም እንዲህ አለች፦
⁴⁷ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
⁴⁸ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
⁴⁹ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
⁵⁰ ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
⁵¹ በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
⁵² ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
⁵³ የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
⁵⁴-⁵⁵ ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
⁵⁶ ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።
⁵⁷ የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ጊዜ ደረሰ፥ ወንድ ልጅም ወለደች።
⁵⁸ ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ምሕረቱን እንዳገነነላት ሰምተው ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።
⁵⁹ በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፥ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ወደዱ።
⁶⁰ እናቱ ግን መልሳ፦ አይሆንም፥ ዮሐንስ ይባል እንጂ አለች።
⁶¹ እነርሱም፦ ከወገንሽ ማንም በዚህ ስም የተጠራ የለም አሉአት።
⁶² አባቱንም ማን ሊባል እንዲወድ ጠቀሱት።
⁶³ ብራናም ለምኖ፦ ስሙ ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ።
⁶⁴ ያንጊዜም አፉ ተከፈተ መላሱም ተፈታ እግዚአብሔርንም እየባረከ ተናገረ።
⁶⁵ ለጎረቤቶቻቸውም ሁሉ ፍርሃት ሆነ፤ ይህም ሁሉ ነገር በይሁዳ በተራራማው አገር ሁሉ ተወራ፤
#ርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን #ጣና_ቅዱስ_ቂርቆስ #ርእሰ_ሊቃውንት #Fewus_Menfesawi #menfesawi #Aba #Africa #Ethiopia #አፍሪካ #ኢትዮጵያ #Mezmur #መዝሙር #መዝሙርተዋህዶ #ፈውስ_መንፈሳዊ #for_you #Viral #parati #pfy #storytime #tiktok ፈውስ መንፈሳዊ ዘጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fewus Menfesawi / ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ / Aba Gebrekidan Girma
#፩ ሃይማኖት
#፩ ሲኖዶስ
#፩ ፓትርያርክ
#ርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳን #aba_gebrekidan_girma #ethiopia #viral #aba #africa #አባ_ገብረኪዳን_ግርማ #አባይ #ሲኖዶስ
#sinodos

Пікірлер: 557
@user-jg9wc2gb4r
@user-jg9wc2gb4r 26 күн бұрын
እልልልልልል ተመስገን አባታችን ጠፍተውብን ነበር መጡልን አስሬ ይቱብ ስገባ ነበር😂 እኳን ሰላም መጡልን ብዙ አትጥፉብን በድሜ በፀጋ ያቆይልን ላይክና ሸር እያረግን ግን
@GetachewGeach
@GetachewGeach 25 күн бұрын
Betame tewdaje memeher nachew
@fasikaalem7483
@fasikaalem7483 25 күн бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን መምህር እኔ በተዋህዶህምነቴ ሁሌም ደስተኛነኝ ትምህርቶችን ስሠማግን የሚያወዛግበኝ ነገርአለ የትምርት አሰጣጥ አድ ባለመሆኑ÷ለምሳሌ በርሚል ገወርጊስ የሚታየዉን ታምር ለማየት የዘወትር ፀሎቴ ነበር አሁደም የሚያናግራችሁ ሠይጣንጂ መላክ ወይም ክርስትስ አደለም ማለት ምድነዉ??ላባባሌ በእግዚአብሄርስም ይቅርታና በዉኑሥ የበቁ አባት እናትስ የሉንም ማለትነዉ ?በየገዳማቱሥ የሚነገሩ የታምር ስራወች ሁሉንም አላልኩም አዳዶቹ እዉነትአደሉም ከዚህ አፃር የቀደሙአባቶች የሰሩት ገድል ሲነገረን አብዛኛወቹ በእግዚአብሄር ቸርነትካልሆነ በሠዉ ሐይምሮ አምኖለመቀበል ከባድነዉ እነሱንሥ ሠዉ እደመሆናቸዉ የበቁ ናቸዉ ብለን ማመን አችልም ማለትነዉ?መፃፋቅዱሥ አድነዉ ካተባለ የትምርት አሠጣጦች ለምን የተለያየ ሆነ ይሄ በምምናኑላይ ለኛ ለምናዳምጠዉ ጥያቄ እየፋጠረብንነዉ ወይም እራሤን ወክየ ስናገር የትምርቶች አሠጣጥልዩነት ጥያቄ እየፋጠረብኝ ስለሆነ እዴትልረዳዉ ???ከይቅርታጋር ያያችሁት የገባችሁ በእግዚአብሄር ስም እድታሥረዱኝ ስል እጠይቃለዉ 🙏🙏🙏
@user-jg9wc2gb4r
@user-jg9wc2gb4r 25 күн бұрын
​​@@fasikaalem7483 በመጀመሪያ እኛ ቅዱሳንንና መላእክትን ጌታችንን እመቤታችንን ለማየት ብቁ ነኖይ ብሎ ማሰብ አለብን ?ከመፀሃፍ ቅዱስ ምጭ ብዙ አሉን ከዛ እያስተማሩን ቢሆንስ የበቁ አባት የሉንም ወይ ላላችሁት አሉን እግዚአብሔር ይመስገን በገዳም ተሰውረው የሚፀልዩ ስለኛ በነሱም ፀሎት ልመና ነው በእግዚአብሔር ቸርነት ነው ያልነው በገዳማት የሚደረጉት ሁሉ እውነት ናቸው ብለሽ ደግሞ መቀበል የለብሽም ተዋህዶን ለማጥላላት ብዙ የኛን አባቶች መስለው ቤተ ክርስቲያናትን የሚያዋርዱ አሉ ለሁሉም አካባቢሽ የሃይማኖት አባት ካለ ጥያቄሽን ጠይቂ መጠየቅ አይከፋም ጥያቄ የፈጠረብሽን ሁሉ🤗ሲቀጥል የምሰሚውን መርጠሽ ስሚ😴አባታችን ስለ በርሜል ቅዱስ ጊወርጊስ ያስተማሩት አሁላይ ሁሉም ያንን ለማየትጅ እደ አይሁዳውያን የምንሄድ ለመዳን አይደለም ምክንያቱም እኛ ተአምር ወዳጆች ስለሆንን እምነት ይኑረን ለማለት ነውጅ አች እዳሰብሽው ላይሆን ይችላል ከልብሽ አድምጭው ምክንያቱም አሁላይ አድ ተአምር ታየ የተባለበት ቦታ ለማየት መጋጋትንጅ አጠገባችን ያለው ፀበል የሚያድነን አይመስለንም ሳስበው ካመንን የትም ቢሆን የፈጣሪ ቤት ነው በሁሉም ስላለ አጠገባችን ያለውን አንርሳ ነው ያሉት እዳሰብሽው የበቁ አባት የሉንም ፀበሉም አይፈውስም አላሉም
@tuuilgig
@tuuilgig 25 күн бұрын
እኔም
@user-ky1zc8qw8w
@user-ky1zc8qw8w 25 күн бұрын
​​@@fasikaalem7483ቃለህይወትን ያሰማልን እኅታችን / ወንድማችን አወ እውነተኛ አባቶቻችን እኮ የሚሉን አድ ነገር አለ እሱም ምንድነው ትክክለኛውን ሰባኪ አባት ካህናትን የሚያስተምሩትን ትምህርት አዳምጡ ይሉናል ስለዚህ እኛ ማመዛዘን አለምብን እገሌን ከእገሌ ለማመዛዘን ሳይሆን የትኛው ነው ትክክል የክርስቶስን የድንግል ማርያምን የቅዱሳንን ትምህርት የሚያስተምሩ ብለን መለየት አለብን ስርአተ ቤተክርስቲያንን ህግጋትዋን ቅኖናዋን የሚያከብር የትኛው ነው ብለን መለየት አለብን ክርስቶስን በሱ እየሸፈነ ድንግል ማርያምን ቅዱሳን አባቶቻችንን በሱእየሸፈነ የክርስቶስን የድንግል ማርያምብ ክብር ከመናገር ይልቅ የራሱን ክብር የሚናገር ከሆነ እሱን ትክክል ነውብለን አንወስድም እደታውቁት ባሁኑ ስአት ሁሉ አስተማሪ ሁሉ ሰባኪ ሁሉ ተአምረኛ ነኝ ሁሉ እኔ አውቃሉሁ ነው እሚለው ስለዚህ እኛስ ይሄን ይሄን መለየት መቸም አያቅተንም ብዙ የሚዘባርቁ እዳሉ ሁሉ ብዙ እውነተኞች አሉ ስለዚህ ሰባኪ መስለው ከሚሰጡት ትምህርት መጠንቀቅ አለብን ቅድስት ቤተክርስቲያን አድት ነች ትምህርትዋም አድ ነው ህግዋም አድ ነው የተለየ ነገር ምንም የለም ተአምር መስራት በራሱ ችግር የለም ፀጋው ከተሰጣቸው ምክንያቱም ሁሉም የተለያየ ፀጋ አለው እንጅ የተለየ ትምህርት ግን የለም ቅዱሳን አባቶቻችን ሂድ አተ ሰይጣን ብለው በክርስቶስ ስም አጋንትን ይፈውሳሉ እንጅ እኔ አቃጥየው እኔ እድህ አርጌው አይሉም ነበር ክብሩን ለክርስቶስ ነበር እሚያስቀድሙት ትክክለኛ አባት ፀጋው እድታወቅለት አይፈልግም ስለዚህ ትክክል የሆኑትን የክርስቶስን ፍሬዎች የድንግል ማርያምን ልጆች የቅዱሳንን ወዳጆች የሆኑትን እውነተኞቹን አባቶቻችን የሚያስተምሩትን ትምህርት እግዚአብሔር በፈቀደልን አቅም ያክል መከታተል አለብን እግዚአብሔር ይስጥልኝ ከብዙው በጥቂቱ ነው
@user-oc5jn1mg2q
@user-oc5jn1mg2q 25 күн бұрын
አባታችን በእውነት ቃለህይወት ያሰማልን እረጅም እድሜ ይስጥልን በእውነት ታመናል ጠፍተናል ሁሉም እየተነሳ ማርያም አየሁ ቅዱሳንን አየሁ እያሉ እረረ ሰንቱን እያየን እየሰማን ነው ክፉ ሰዓት ነው አዲስ ጠበል ፈለቀ የበቁ አባት አለ ታምር አየን እያሉ ሰይ እናደዳለሁ የድሮ ጠበልስ የት ሔደ እላለሁ እንደው አባታችን ምከሩን ገጸጽን እባካቹሁ መልፋት እየለፋቹሁ ነው የሚሰማ ጠፋ እንጂ የእናቶቻችን እምነትን ይሰጠን በእውነት እናቶቻችን ከዚያም ከዚያም መዞር ምንድነው ትርፉ ከዚህ ሚካኤል አለ ከዚህ እመቤታችን አለች ከዚህ እግዚአብሔር መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ጠበል አለ ከዚህ መጽናት መጠመቅ ነውንጂ በየቦታው መዞር ምንድነው ሁሉም እኮ አንድ ነው ይላሉ የቆዩ እናቶቻችን እንደኛ እኮ ፊደል አልቆጠሩም ግን ከቆጠርነው በላይ ናቸው በእምነታቸውም በሁሉም ነገር በህገ ልቦና የተማሩ ናቸው ተማር ብለን እየጠፋን ነው ያለነው እኛስ አሁን ግን በቃ ብቻ ከባድ ነው ልቦና ይሰጠን አባታችን ኑሩልንበእውነት እኔ በራሴ የደርስ ነገር ላካፍላቹሁ የእናቶቻችን እምነት ጥብቅነው ታምሜ ተኮርትሜ መራመድ አልችልም ነበር ለብዙ አመታት እና እናቴ አዝላኝ ብዙ ተጉዟ ነው ዳገት ቁልቁለቱ ን አዝላኝ በ ባዶ እግሯ አዝላኝ ሲደክማት ታወርደኝና እንበዋን ጠርጋ ዙሯ አይዞሽ አልከበድሽኝም ልጄ ወድሜ ሲደክመው እሷ እያሉ መቼም አቡነሐራ ድንግል ገዳሙን የማታዉቁት ታዉቁታላቹሁ ዳገቱ ቁልቁለቱ ያ ሁሉ አልበገራትም ሳታደክም አሁን እየደርስን ነው አይዞሽ እያለች በተሰፋ በእምነት ወሰደችኝ ሁሌም ጠበል እምነቱን ታሰጠምቀኛለች ታጠጣኛለች ትቀባኛለች ወዩ እናቴ ልፋቷ 😭😭የሚገርመኝ ወድሜ የአብነት ተማሪ ነበርና አድርሰኝና ሔድ ወደትምህረትህ አላማ አላማ ነው ልብህ አይናወጽ ወደእኛ አትስብ በአንድ ልብህ ተማር አይዞል ልጄ ሔድ ወደ ትምህርትህ አሁን ትዳናለች ኮቼሮ ሽሮ ይዛ መጥታ ተይሃለች አለችውና ወደትምህረቱ ሰደደችው ብቻሽን አትችይም እናቴ ሲላት አንተም የእመቤታችን አገልገይ ሁነህ ብቻሽን ትላለህን ልጄ እመን እንጂ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አይደለ እንኳን ከቤቱ ገባን እንጂ እርሱ ያግዘኝ አይደለ በል ሔድ አለችው እሱም ሔዴ ወደትምርቱ እናቴዋ የምታመልኬው የሰማይ የምድር የፈጣሪ የቅዱሳን አምላክ መልካሙን ዋጋ ይክፈልልኝ በእውነት እና ጻዲቁ አቡነሐራ ድንገል ጠበል እየተጠመቅሁ ሳለሁ እናቴ አይዞሽ ልጄ አሁን ቁመሽ ትራመጃለሽ እጅሽ ሁሉም ይቀሳቀሳል እመኚ ልጄ አሁን ትፈወሻለሽ አይዞሽ ትለኛለች እና ከዚያ የሚጠመቁ ሰውች አሉ የሚያዉቃት የማያዉቃት ሁሉ እናታችን ከዚህ አዲስ ጠበል ፈልቋል እና ከዚያ ይወሰዷት ከዚያ ነው የምትድነው ይሏታል በየቀኑ ከዚህ ቦታ አለ አዲስ ጠበል ከዚያ ይወሰዷት ከዚህ ብዙ ወራትን እየተጠመቀች ምህረት አላገኚችም ይሏታል እና እናቴ ልጄ አትሰሚያቸው እነዚህ እምነት የጎደላቸው ናቸው ጠበል አዲስ የቆየ የሚባል የለም ሁሉም የእግዚአብሔር ጠበል ነው ቦታ ሰለተቀያየርን አዲሰ ነገር የለም ልብሽ እንዳይጠራጠር አይዞሽ ተመሰገን አሁን ልትድኝልኝ ነው እግዚአብሔር በጻዲቁ በአቡነሐራ ድንግል ላይ አድሮ ሊፈውስሽ ልትቆምልኝ ነው ሰይጣን በሰው ላይ አድርሮ እንዳትድኝ ዉጭ እያለሽ ነው እናም ልጄ ልብሽ ይጽና አሁን ይመጣል ምህረት አለችኝና አጠነከርችን ሰውችም አላርፉም ይዉሰዷት ይላሉ እሷም እሽ እያለች ዝሜ አለቻቸው ማታ ጠበል እምነቱን ተቀብቼ ምግብ መጎርስ አልችልምና እሷ ነች የምታጎርሰኝ የምታስተኛኝ የምታሰሳኝም እሷ ነች ጧት 10 ሰዓት ሁኗል ልጄ ተነሽ ብላ ልታነሳኝ ሰትል እጄ እግሪ የዞርው አንገቴ ሁሉ ቀጥ ብሎ ተሰተካክል አገኚነው ልክ ሰነሳ በቃ ሁሉም ነገር የድሮ ማንነቴ ገዳሙን እየሮጡህ ዞርሁ መቆሜ እውነት አልመሰለኝም በቃ ደስታውን መግለጽ አልችልም መራመድ ብርቅ ነበር ለእኔ እና ተደሰተን እናቴ አለቀሰች ተመሰገን ልጄን አየሃትን ምህረትህ አበዛህልኝ ብላ አመሰገነች እነዚያ ወሰጇት ወደሌላ ያሏት ሰውችም ተገርሙ ዝም አሉ ምሰክርም ሰጠች ልጄ እኔ ልሞት እችላለሁ ማን እንደሚቀደም የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው ግን የምመክርሾ ነገር ገና ህጻን ሰለሆንሽ አሰተወይ በእምነት ጽኝ እምነትሽ ለጊዜው አይሁን እሰከመጨረሸው መጽናት ነው ልጄ ከዚህ ይህ አለ ከዚህ ይህ ፈለቀ እያሉ የያሽውን እምንት እንዲጎልሽ ከሚያደርጉ ሰዎች እራቄ ከሁሉም ቦታ የአንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ያለው በሁሉም ጠበል እምነቱ ቤተክርስቲያን በየቦታው ቢኖርም ሁሉም እግዚአብሔር ነው የሚፈውሰው እሳት ውስጥም ገደል ውስጥም በተለያየ ቦታች ችግር ብትሆኝ እግዚአብሔር በሁሉም ነገር እዳለ እመኚ አምላክ አይቀያየርም ምን የሚካኤል የገብርኤል የራጉኤል የማርያም ቤተክርስቲያን ቢኖርም በዚያ ላይ እግዚአብሔር ነው የሚመለከው ምህረቱም በዚያው አለ እና ቦታ ሰለተቀያየር ይፈወሳል አምላክን አገኚዋለሁ ማለት የለብሽም ልጄ አደራሽን አለችኝ በእውነት እና በአጭር ዛሬ ሰው ሁኜ ይህው በሰው ሀገር እሰራለሁ እና ወገኖቼ በእውነት የእናቶቻችን እምነት ለሁላችን ያድለን በእውነት እኔን በምህረቱ የጎበኚኝ የአባቶቻችን የእናቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን ለእናንተም ይድረስላቹሁ እና በእምነት እንጽና በየቦተው አንሯሯጥ አንምርጥ ጠበል ጠበል ነው አዲስ የድሮ የሚባል ነገር የለም ሁሉም አንድ ነው በትግስት ጽኑ
@Fewus_Menfesawi_Aba_Gebrekidan
@Fewus_Menfesawi_Aba_Gebrekidan 25 күн бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን።
@user-oc5jn1mg2q
@user-oc5jn1mg2q 25 күн бұрын
@@Fewus_Menfesawi_Aba_Gebrekidan አሜን አብሮ ያሰማን በእውነት እጽብ ድንቅ የሆነውን የአምላካችንን ቃል ሁሌም ሳሰለቹ ሳትደክሙ ሰለምትመግቡን ሰለምታሰተላልፉልን በእውነት ፈጣሪ ያክብራቹሁ እረጅም እድሜን ይሰጣቹሁ ኑሩልን በረቱልን ጠንክሩልን ሁሌም እከታተላቹኃለሁ ደስስ ይለኛልም ወገኖቼ በረቱ
@fentayismaw1591
@fentayismaw1591 25 күн бұрын
እግዚአብሔር ይመሰገን ቃለሕይወት ያሰማልን የሚገርም እምነት
@user-qq6wy5mu1z
@user-qq6wy5mu1z 25 күн бұрын
ደስስ ይላል እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር አምላክ ፍጹም እምነት ይስጠን በእውነቱ ❤🎉
@ethiopialove2158
@ethiopialove2158 25 күн бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ለዚህ ክብር አበቃሽ ግን ፅሁፍ እንዳነበብኩት እዛ ገብርኤል አለ እዛ ሚካኤል አለ ላልሽው ስህተት ነው ምክንያቱም ሰው በእርቀት የሚሄደው የተለያየ ያመልካን ማለት አይደለም በሁሉም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር ነው የሚመለከው ግን ርቀን የምንሄደው ምን ያክል አቅም እንዳለን እግዚአብሔርን ታመሰግኚዋለሽ ለዛ ነው አብዛኞቹ ልጅሽን እዚህ ውሰጃት እዛ ውሰጃት የሚሉት ጥቅሙን ስለሚያውቁ እንጂ እዛ ያለው ይለያያል ብለው አይደለም ካጠፋሁ ይቅርታ በንግግሬ
@Usernumber21_16
@Usernumber21_16 26 күн бұрын
አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰኝ። መድኃኔዓለም ከክፉ ኹሉ ይጠብቅዎ።
@taytay4962
@taytay4962 26 күн бұрын
እግዚያብሄር የጠብኮት አባ 🙏🙏🙏
@user-gv5rl1sl6r
@user-gv5rl1sl6r 15 күн бұрын
አባ ያኑርልን
@DawitGebeyaw-rl4fm
@DawitGebeyaw-rl4fm 26 күн бұрын
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን🙏ለ አዘጋጆችም እግዚአብሔር ይስጥልን።።።።እንደ አስተያየት ደግሞ የ አባታችንን ትምኽርቶች ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ እየተተረጎሙ ወደ ዓለም ቢሰራጩ።።🙏 ልክ እንደ አቡነ ሺኖዳ ትምህርቶች።።እግዚአብሔር ይስጥልኝ🙏
@merd24
@merd24 26 күн бұрын
በጣም ደስ የሚል አስተያዬት ነው
@user-uo3lw4wi9o
@user-uo3lw4wi9o 26 күн бұрын
በትክክል።ከዚህ የህይወት ምንጭ የተጠማ ሁሉ ቢጠጣ! ምኞቴ ነው።
@besttube8710
@besttube8710 26 күн бұрын
በጣም ግሩም ሐሳብ ነው ሊደረግ የሚችልበትን መንገድ ተባብረን ስራዬ ብለን እንፈላልግ። በተደጋጋሚ ተናገረው ይሄንን ሐሳብ
@uaes-hr1pi
@uaes-hr1pi 25 күн бұрын
Beawunet
@BdMs-ci3dp
@BdMs-ci3dp 24 күн бұрын
አሜን ለሁላችንም ያሰማን ጥሩ ሃሳብ ነው እግዚአብሔር አምላክ የገነት ሰዎቸሰ ያድርገን❤❤❤
@user-jk3in5xm8t
@user-jk3in5xm8t 26 күн бұрын
እሰይ እሰይ እሰይ እሰይ የኔ ወርቅ ወርቅ ወርቅ ..... አባት ዉሎየን ስጠብቅ ነበር እሰይ እንኳን ደህና መጡልን የኛ መጽናኛ አባት በተለይ ለኔ 😢 ቡራኬዎት ትደርሰኝ ባለሁበት ሀገር አሜን ፫🙏 ቃለህይወትን ያሰማልን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን እኛም በሰማነዉ ቃል 30:60:100 ያማረ ፍሬ እንድናፈራ ቸሩ ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ በቸርነቱ ይርዳን አሜን፫ ረጅመ እድሜ ከጤና ጋር ልዑል እግዚአብሔር ያድልልን አሜነ ፫🙏
@user-jk3in5xm8t
@user-jk3in5xm8t 26 күн бұрын
መጥምቀ ዮሐንስ የኢትዮጵያን ሀገራችንን የተዘጋባትን በምልጃህ አስከፍትልን አሜን ፫🙏😢
@wnyenegesti4791
@wnyenegesti4791 26 күн бұрын
አባ ግን ገወርግሰ ጠበል ትክክል አይደለም እያሉ ነው
@user-jk3in5xm8t
@user-jk3in5xm8t 25 күн бұрын
@@wnyenegesti4791 እመብርሀንን እኔም ዉስጤ ደስስ አላለዉም እግዚአብሔር እዉነቱን ይግለጥልን 😢🙏
@user-jk3in5xm8t
@user-jk3in5xm8t 25 күн бұрын
@@wnyenegesti4791 እመብርሀንን እኔም ዉስጤ ደስስ አላለዉም እግዚአብሔር እዉነቱን ይግለጥልን 😢🙏
@fasikaalem7483
@fasikaalem7483 25 күн бұрын
​@@wnyenegesti4791እኔም ጥያቄ ፋጥሮብኛል😢
@alemgmichael2127
@alemgmichael2127 26 күн бұрын
ዮሐንስ ብሎ ፃፈ ፣ አንደበቱም ተከፈተ ። ቃለ ሕይወት ያሰማልን ።
@የኤማሁስ_መንገደኞች
@የኤማሁስ_መንገደኞች 17 күн бұрын
ቃለሕይወት ያሰማልን አባታችን
@fatmasaeed6043
@fatmasaeed6043 26 күн бұрын
እልልልል አባታችን መጡልን እኔኮ ውስጤ ስክን እሚለው በአባ ገብረኪዳን ትምህርት ነው እርሰዎን በዝህ በጭቅ ዘመን እግዚአብሔር ስለሰጠን ክብሩ ይስፋ
@raheltsegaye7875
@raheltsegaye7875 10 күн бұрын
እግዚአብሔር ረጅም እድሜ ይስጥልን
@user-ze1de1gp3q
@user-ze1de1gp3q 26 күн бұрын
አባታችን ቃለህይወት ያሰማልን❤❤❤❤🕊🕊🕊አገራችንን ኢትዮጵያ ሰላም ያርግልን
@netsanetmedia21
@netsanetmedia21 20 күн бұрын
አባታችን ቃለ ህይወትን ያሰማልን በረከትዎ ይድረሰን🙏🙏
@mollaligntesfa4554
@mollaligntesfa4554 9 күн бұрын
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን። እባታችን በረከትዎ ቡራኬዎ አይለየን🥀🥀🥀💚💛❤️🙏
@zelalemanagaw8921
@zelalemanagaw8921 26 күн бұрын
ይፍቱኝ ብራኬዎት ትድርሰኝ አባ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን ዕድሜ በጤና ያቆይልኝ መምህር ካህን መነኮስ
@user-uz6uk6zm2v
@user-uz6uk6zm2v 26 күн бұрын
ቃለ ይወት ያሰማልን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን 🙏🙏🙏
@mazaadubai
@mazaadubai 26 күн бұрын
አባታችን እንኳን ደና መጡልን❤❤❤❤❤ቤተሰብ👍👍👍👍👍👍 share አንርሳ❤❤❤❤❤
@user-oj2zs7if8k
@user-oj2zs7if8k 26 күн бұрын
ተመስገን 💖 አባየይ እንኳዕ ብሰላም መፃኹም 🎚️
@musemamilove4519
@musemamilove4519 25 күн бұрын
ሸዊተይ ❤የኔ ልጅ
@dawityerdaw4436
@dawityerdaw4436 25 күн бұрын
Thanks
@zinabmohamammd3146
@zinabmohamammd3146 26 күн бұрын
በእውነት ለአባታችን ቃለ ህይወት ያሰማልን ለእኛም የሰማነውን ቅዱስ ቃል በልቦናችን ሰሌዳ ይጻፍልን በእውነት ሁላችንም ጠፍተናል
@user-it2ge3so1i
@user-it2ge3so1i 26 күн бұрын
የኔ አባት እንኳን ደህና መጡልን
@user-lo9zo6ix2k
@user-lo9zo6ix2k 23 күн бұрын
Aba ebakotene beremele giyoregise hiduna selesu sebele yehiduna yasetemerune besematu yezetalewe
@bereketmeberatu4367
@bereketmeberatu4367 25 күн бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን ቅዱስ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን አባታችን, አሜን
@user-ck2kx6ld1x
@user-ck2kx6ld1x Күн бұрын
ኣሜን ኣሜን ኣሜን ቃል ህይወት ያሰማሌን ክቡር አባታችን 🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤❤❤
@asterstefanos7842
@asterstefanos7842 25 күн бұрын
❤አባታችን❤ቃለ❤ሕይወት❤ያሰማልን❤ቅዱስ:አማኑኤል❤በዕድሜ❤በጤና❤በፀጋ❤ይጠብቅልን❤ይፍቱኝ❤ይባርኩኝ❤በረከትዎ❤ይድረሰኝ❤ለንስሀ❤ያብቃኝ❤
@selamselam699
@selamselam699 Күн бұрын
እልልልልልልልል ተመስገን አምላካችን አባቶችን ቃለ ህይወት ያሰማልን 🙏🙏🙏
@pinkroad-9201
@pinkroad-9201 26 күн бұрын
ሁሌም ትምህርትዎ ህይወት ቀያሪ ነው ። ቃለ ህይወት ያሰማልን ድንቅ አባታችን❤❤❤
@nardosabebaw7809
@nardosabebaw7809 11 күн бұрын
እግዚአብሔር እንኳን በሰላም አገናኘን እግዚአብሔር ይመስገን
@user-bk4sl2fz8z
@user-bk4sl2fz8z 26 күн бұрын
_እግዚአብሔር ኣምላኽ ይከበር ይመሰገን ሰላምኩም ዮብዘሐዮ ክቡር ኣቦና ብሓቂ ቃል ህይወት ቃል በረከት የሰመዐልና ነውሕ ዕድመን ጥዕናን ይሃብኩም ቅዱሰ እግዚአብሔር ኣምላኽ አሜን አሜን አሜን✝️✝️✝️_
@selamasefa6049
@selamasefa6049 21 күн бұрын
ይህን ኪቦርድ ነገሩኝ በጣም ነዉ ደስ የሚለኝ
@user-rh7vk3bb7c
@user-rh7vk3bb7c 26 күн бұрын
አባ በረከትዉይድረሰን
@tsegaasfaw3330
@tsegaasfaw3330 25 күн бұрын
አባታችን:- ቃለ ህይወት ያሰማልን። መታደል ነው እኛም የምናዳምጥዎት ታድለናል። ጌታ ይሸፍንዎት:: አሜን አሜን አሜን
@KalkidanMerise
@KalkidanMerise 26 күн бұрын
እውነት ነው አባታችን ቃለህይወት ያሰማልን ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ያድለን በቸርነቱም ያስበን ይመልከተን🙏🙏🙏
@BelAeshTeDese
@BelAeshTeDese 4 күн бұрын
አባታችን ቃለህወት ያሰማልን እግዚአብሔር በእድሜ በጤና ይጠብቅልን🙏🙏🙏❤❤❤
@user-ot8zu5ov2d
@user-ot8zu5ov2d 7 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን
@heliLulu-bf9tq
@heliLulu-bf9tq 26 күн бұрын
ቃለህይወትን ያሰማልን አባታችን❤❤❤
@user-ln9cv2oi6d
@user-ln9cv2oi6d 26 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለህይወት ያሰማልን አባታችን እንኳን ደህና መጡ አባታችን❤❤️❤️🙏🙏🙏
@AboGra-l3u
@AboGra-l3u 10 күн бұрын
ቃለ ሕይወት ያሰማልን በረከትዎ ይድሰን
@user-oh6rc3mv6w
@user-oh6rc3mv6w 25 күн бұрын
😢ሁሌ እየፈለኩ ነበር የኔ ወርቅ አባት እንኳን በሰላም መጡ❤🎉❤
@zemaritseblewengielofficia5926
@zemaritseblewengielofficia5926 6 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይወት ያሰማልን አባታችን እግዚአብሔር እረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን 🙏🙏🙏🙏❤❤❤❤❤❤
@MssSabeala
@MssSabeala 10 күн бұрын
ቃለሂዎት ያሠማልን አባታችን እረጅም እድሜ ያድልልን❤❤❤
@birukmesfin-ix5jw
@birukmesfin-ix5jw 14 күн бұрын
Kale hiwot yasemaln🙏🙏
@Meskerem-oz5oh
@Meskerem-oz5oh 10 күн бұрын
Abbatachen kal hiwot yasamalen ! Berketo yederben! kidisanun ena Egziabihern mekelej adergut eko
@zenebechmengste-wk7ce
@zenebechmengste-wk7ce 25 күн бұрын
አሜን ቃለህይዎትን ያሰማልን ለዓባታችን አረዥም እድሜ ከጤና ይስጥልን አሜን 👏
@haregmengsha5657
@haregmengsha5657 26 күн бұрын
እንኳ ደና መጡልን አባታችን ❤ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በጤና ይጠብቅልን አሜን የሰማነውን በልቦናች ያሳደርበን ❤
@rigatdesita1826
@rigatdesita1826 26 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃለሂወት ያሰማልን አባታችን ቡራኬዉ ይደርብን በፀሎቱሁ ያስቡኝ አባ ❤❤❤
@user-ho8hk6ii7k
@user-ho8hk6ii7k 26 күн бұрын
Abatachn ,kale hywetn yasemaln!
@sdgs6877
@sdgs6877 7 күн бұрын
አሜንን አሜንንን አሜንን አሜንን አሜንን
@alganesh-xe4yb
@alganesh-xe4yb 25 күн бұрын
Abatachen kale hiwot yasemalen ye Amargna dawit yet maggnet enchlalen ebakachu ngerugn❤
@user-wk2jw5bi6v
@user-wk2jw5bi6v 26 күн бұрын
እንኳን ደህና መጡልን ክቡር አባታችን❤❤❤
@sileshegirma2909
@sileshegirma2909 26 күн бұрын
ቃለ_ሕይወት ያሰማልን🙏
@betetsion
@betetsion 25 күн бұрын
ቃለሕይዎት ያሰማልን ክቡር አባታችን ቡራኬዎት ይድረሰኝ እሚወዷት ድንግል ማርያም ከክፉሁሉ ትጠብቀዎት
@tewabechberta8297
@tewabechberta8297 19 күн бұрын
የኔ አባት እድሜና ጤና ይስጦት ትክክለኛውን የክርስቶስ ወንጌል ስለሚሰብኩ ነፍስና ስጋዬ እረፍት የሚያኘው ።
@solomonbekele9212
@solomonbekele9212 25 күн бұрын
አቤት! የማይጠገብ አንደበት የማይሰለች ልሳን ረዥም ዕድሜንና ጤናን አሟልቶ ይስጥልን
@gebretekle5610
@gebretekle5610 26 күн бұрын
አባይ በፀሎት አሰቡን 🙏🙏🙏🙏
@hitechinstituteoftechnology
@hitechinstituteoftechnology 25 күн бұрын
ቃለህይወት ያሰማልን በእድሜ በጸጋ እግዚአብሔር ይጠብቅልን
@tilahunzewdu3022
@tilahunzewdu3022 7 күн бұрын
Okay😊❤ thank you
@salamrita2646
@salamrita2646 25 күн бұрын
አሜን ቃልህይወት ያሰማልን አባታችን እንካን ደህና መጡልን❤
@NebyuDawitEthiopiain2016
@NebyuDawitEthiopiain2016 26 күн бұрын
እሰይ፣ እንኳን ደህና መጡ አባታችን።
@TayechZeynu
@TayechZeynu 26 күн бұрын
አባታችን ቃለ ሂወት ያሠማልን ፀጋውን ያብዛሎ ት በእድሜ በጤና ይጠብቅልን
@BirukBiruk-hb1ij
@BirukBiruk-hb1ij 15 күн бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን
@alemalem7462
@alemalem7462 25 күн бұрын
ቃልሂወት ያሰማልን እረዥም እድሜ ከጤና ጋር ይስጥል የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን🙏🙏🙏
@user-ko6dl9ln4t
@user-ko6dl9ln4t 25 күн бұрын
ቃለ ህይወትን ያሰማልን አባታችን እድሜ ጤና አብዝቶ ይስጥልን
@assilaselefechbedeke3292
@assilaselefechbedeke3292 25 күн бұрын
Amen Amen Amen KALE Hiwotin Yasemalen Eyina Enikuw Abatachin Edimena Tena Fetar Yadilen ❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉❤❤❤
@Aplus-ft9rw6eh3j
@Aplus-ft9rw6eh3j 25 күн бұрын
አባ ቃለ-ህይወት ያሰማልን ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፡፡ ትምህርቶት ከማር ወለላ በላይ ለነፍስ ተስማሚ መሆኑ አይካድም ከዚህ በላይ ወንጌልን እያመሳጠሩ እንዲያስተምሩን የወንጌሉ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ይሁኖ፡፡ ግን ከዚህ ስብከቶ ውስጥ ትንሽ ግር ያለኝ ስለ ቤርሜል ቅ/ጊዮርጊስ ፀበል ተዓምራት የተናገሩት… ባይሆን በሚቀጥለው ትምህርት ግልፅ ያደርጉልናል፡፡ ከዚህ በላይ ለፈጣሪ እግዚአብሔር የሚያገለግሉበትን ዕድሜ ከጤና ይስጦት፡፡
@Woinshet27
@Woinshet27 25 күн бұрын
አሜን, አባታችን ቃለ ህይወት ያሰማልን!
@lemlemlem7098
@lemlemlem7098 26 күн бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን ያገልግሎት ዘመንወን እግዚአብሔር ይባርክልን
@user-yv6ve3or5q
@user-yv6ve3or5q 26 күн бұрын
አባታችን ቃለ ህይወትን ቃለ በረከትን ያሰማልን በድሜ በጤና ይጠብቅልን 🙏🙏🙏🙏🙏
@Arsiema97
@Arsiema97 26 күн бұрын
የእኔ ኣባት🥰❤🙏
@danielbekele2977
@danielbekele2977 25 күн бұрын
አባታችን ቃለ ህይወት ያሰማልን, ለኛም ቃሉ የህይወት ቃል ይሁንልን።
@user-vt9ik9vw2r
@user-vt9ik9vw2r 25 күн бұрын
አሜን 🙏አሜን 🙏አሜን 🙏ቃለ ህይወት ያሰማልን አባታችን 🙏🌹💜
@kedanayemariyam1323
@kedanayemariyam1323 25 күн бұрын
አሜን አሜን አሜን ቃል ህይውት የስማልን ቃል ህይውት የስማልን ቃል ህ ይውት የሰማልን ❤ልልልልል
@kasakassa9572
@kasakassa9572 25 күн бұрын
አሜን (፫) ቃለ ህይወት ያሰማልን አባ ❤️🙏
@berketfekadu2736
@berketfekadu2736 26 күн бұрын
ቃለ ሕይወት ያሰማልን የኛ ውድ አባት እግዚአብሔር ይብቅልን 🙏🙏🙏🙏
@user-wf9ij5nt5o
@user-wf9ij5nt5o 26 күн бұрын
,ዮሐንስ ብሎ ፃፈ አንደበቱ ተከፈተ:: ,አባታች ቃለ ህይወት ያሰማልን
@yafetlijyee
@yafetlijyee 25 күн бұрын
አባታችን ቃለ ሂወት ያሰማልን
@bareshdubai6535
@bareshdubai6535 25 күн бұрын
ቃለ ሕይወት ያሰማልን አባታችን
@aelaflisanu9491
@aelaflisanu9491 25 күн бұрын
Yene abat kalehiwot yasemalen edme yestln
@ghennetwoldegabrel9229
@ghennetwoldegabrel9229 25 күн бұрын
እግዚአብሔር ይመስገን ፣ በቸርነቱ ይጠብቀን ፣ያስበን አሜን አሜን አሜን ❤
@user-si9ne1pc3e
@user-si9ne1pc3e 25 күн бұрын
ለአባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን አሜን
@user-wf9ij5nt5o
@user-wf9ij5nt5o 26 күн бұрын
,አባታችን ቃለ ህይወት ያሰማልን በእድሜ በጤና ያቆይልን
@user-zp3zz3yz9n
@user-zp3zz3yz9n 25 күн бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን
@Menemebekamenemem
@Menemebekamenemem 26 күн бұрын
አባታችን እድሜና ጤና ይስጥልን ቃለ ሂወት ያሰማልን አባታችን❤❤❤
@MariamawitAbera-lj9sv
@MariamawitAbera-lj9sv 17 күн бұрын
Abatachin kale hiwot yasemalen ,Abba beteselotwo yasebugn
@AbyotDeresse-jy3bo
@AbyotDeresse-jy3bo 25 күн бұрын
,አባ እንኳን ደህና መጡ
@sara_mandefro
@sara_mandefro 14 күн бұрын
አባዬ❤❤❤❤
@AlexKassa-ub2of
@AlexKassa-ub2of 26 күн бұрын
የኔ አባት ቃለ ህይወትን ያሰማልን ተስፋ ርስተ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን
@manalo1965
@manalo1965 26 күн бұрын
ሰላም ቤተሰብ እንዴት አመሻችኹ አባታችን ጠፍተው ሰንበተውብን ነበር እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ደህና መጡልን 🙏❤🙏
@mahletzegeye775
@mahletzegeye775 26 күн бұрын
ቃለ ህይዎት ያሰማልን አባታችን
@fikertefentahun9800
@fikertefentahun9800 17 күн бұрын
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን
@sipara9224
@sipara9224 26 күн бұрын
አባታችን ቃለህይዎት ያሰማልን
@medhanitabebe9930
@medhanitabebe9930 26 күн бұрын
ቃለ ህይወት ያሰማልን ርስትመንግስተሰማያትን ያውርስልን
@mesaybasazin6358
@mesaybasazin6358 20 күн бұрын
abatachen kaliwot yasemalen
@elsanegussu7889
@elsanegussu7889 5 күн бұрын
Kalhiwot yasmaln🙏🙏🙏🙏
@user-xu8ix4kp2e
@user-xu8ix4kp2e 18 күн бұрын
የብዙዎቻችንን ሕይወት ቀይረውልናል እድሜና ጤና ይስጥልን።
@user-tt8lj5tp1z
@user-tt8lj5tp1z 25 күн бұрын
Amen Amen Amen kale hiwoten yasmalin abtachin 🙏 ❤😊😊😊😊
@ZnebeAlemu
@ZnebeAlemu 25 күн бұрын
ቃለሂወት ያሰማልን አባታችን❤❤❤❤❤❤❤🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
@TruyeAmbaw-nl6uk
@TruyeAmbaw-nl6uk 26 күн бұрын
❤❤❤ በጣም ደስ ይላል ቃለህይውት ያሰማልን አባታችን
@meherat938
@meherat938 26 күн бұрын
አባቴ እንክዋን ደና መጡልኝ ይፍቱኝ እህተ ማርያም ከነቤተሰቤ በጸሎቶ ያስቡኝ የልቤን መሻት ሰምቶ ለንሰሐ ሞት ያበቃን ዘንድ እባኮትን አባ ያስቡኝ በጸሎቶ ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለም::
@YegetachewLij-fn5gn
@YegetachewLij-fn5gn 24 күн бұрын
Abata kale hiwot yasemaln amen
@Mulugetamule-jk3wj
@Mulugetamule-jk3wj 21 күн бұрын
አባታችን እንደ እርስዎ ያሉ የምንፅናናባቸው እንቁ አባቶችን ያብዛልን።
@sste2838
@sste2838 23 күн бұрын
kale hiwot yasemaln amen
@lidyadaniel7449
@lidyadaniel7449 25 күн бұрын
Egzahabhir yemesegen 🙏❤️Qalehiwet yasemaln ❤️ 🙏 Abatachn 🙏❤️Amen ❤️ 🙏
🔴 እምነት| ተስፋ | ፍቅር ይኑራችሁ || እጅግ ድንቅ ትምህርት ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ |Aba Gebrekidan Grma New sibket
1:15:57
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
Рет қаралды 113 М.
🛑 || አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ | እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ  Aba Gebrekidan New Sibket  2024 #viral
1:51:18
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
Рет қаралды 478 М.
What it feels like cleaning up after a toddler.
00:40
Daniel LaBelle
Рет қаралды 87 МЛН
Best KFC Homemade For My Son #cooking #shorts
00:58
BANKII
Рет қаралды 69 МЛН
🔴 የዳዊት ልጅ ሆይ ማረን || እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ  Aba Gebrekidan New Sibket  SON OF DAVID
1:40:13
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
Рет қаралды 265 М.
🛑 አትቸኩሉ || ምልክት ያላቸው በጎች ለያዕቆብ ||ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ  Aba Gebrekidan New Sibket  2022
54:53
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
Рет қаралды 1,1 МЛН