Рет қаралды 13,078
ምራኝ
ምራኝ መንገድ አሳየኝ
ባስቸግርህ የማትለየኝ
ጉልበቴን ለፈቃድህ አበርታ
ብቻዬን መጓዝ አልችልም ለአፍታ
ህይወት ዝብርቅ እያለ
ሰው ምርጫውን ከተከተለ
በማስተዋሉ የተደገፈ
በራሱ ምኞት ተጠለፈ
ከአዕምሮ ባለፈ
በምክርህ ግን የተደገፈ
ሁሉ በፈተና ሲጠልል
እርሱ ብቻ ፀንቶ በድል አለፈ
እኔም ይህንን አውቄ
ትምክህቴን አውልቄ
በእራስ ከመተማመን ትምህርት ርቄ
ምንጬን ፈልጌ መጣሁኝ
ብቻዬን ስለፈራሁኝ
መጥቼ አንተ ውስጥ ገባሁኝ
ምራኝ መንገድ አሳየኝ
ባስቸግርህ የማትለየኝ
ጉልበቴን ለፈቃድህ አበርታ
ብቻዬን መጓዝ አልችልም ለአፍታ