Рет қаралды 154,562
በስምንት አመቷ የአይጥ መርዝ በልታ ራሷን ለማጥፋት ሞከረች::
በልጅነቷ ከሰው ቤት ወደ ሰው ቤት በሰራተኝነት ስትመላለስ እንዲውም በአረብ ሀገር ህምም እና ስቃይን አይታለች::
ገና በ13 አመቷ መስተንግዶ ስትሰራ ሴተኛ አዳሪነት ነው የምትሰራው ተብላ በማሀረሰቡ ተገላለች::
ሳታስተውል ከሱሰኛ ጏደኞች ጋር ገጥማ የጫት : የሲጋራ : የመጠጥ እና የሺሻ ሱስ ውስጥ ገብታለች::
ሱሱ አይሎባት ገንዘብ አሳጣት::ለዚህም መፍትሄ ጫት ቤት ተቀጠረች::
አንድ ቀን ግን ከሁሉም የከፋው አጋጣሚ ደረሰባት::
በአጋጣሚ ያገኘችው የታክሲ ሹፌር ሸውዶ አልብርጎ ተከራይቶ ደፈራት::
የሰከረ ረዳቱም ሊደፍራት ሲሞክር ገፍትራው በሰፈሩ ወደ ምታውቀው ቪዲዮ ቤት ገባች::
የቪዲዮ ቤት አከራዩም ከሌሊቱ 10 ሰዓት በዛው እለት ደፈራት::
እሷ ግን መጀመርያ ከደፈራት የታክሲ ሾፌር ፍቅር ያዛት::እሱ ግን አይፈልጋትም::
በጭንቀት በሽታ ውስጥ ወደቀች የሁለት አይኗቿን የማየት አቅም አጣች::ድንግል ማርያምን እንድታበራላት ተማፀነች::
ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ በማንያዘዋል እሸቱ ግቢ ተግኘች::