Рет қаралды 9,207
አመሰግናለሁ
አንተ ታላቅ ነህ
ከሁሉ የበላይ
እኔ ግን ትንሽ ነኝ በጣም
ከሩቅም አልታይ
ከትልቅነትህ ብዛት
አላውቅህም ነበር
ግን ፍቅር ነህ ሳትንቀኝ
ልጅህ አደረግኸኝ
አመሰግናለሁ
ፍቅርህ ዘለዓለም ነው
አመሰግናለሁ
ቃል አጥሮኝ ነው /2x
ደካማ ነበርሁኝ
ስንፍና የተጫነኝ
ትዕግስትህ ደገፈኝ
ምህረትህ አቆመኝ
የቃልህ ፍቺ ብርሃን ሆነኝ
ሞኙን ሰው አስተዋይ አደረገኝ
ይኸው አለሁ እየደገፍኸኝ
ተስፋ ሳትቆርጥብኝ
አመሰግናለሁ
ፍቅርህ ዘለዓለም ነው
አመሰግናለሁ
ቃል አጥሮኝ ነው /2x
ሁልጊዜ አለህ
ከእኔ ጋራ
ከአንተ ጋር ትልቅ ሆኛለሁ
በሠራኸው ሥራ