Рет қаралды 56,806
ኢየሱስ ብቻ Iyesus Bicha: Track 09 of the live recorded gospel album “Silante”.
የተፈለገ ሁሉ ቢገኝ
ለነፍስ ሚሆን ጠብ አይልም
ምቾትን በገፍ ቢገዙ
ልብን ማሳረፊያ የለም
ዕውቀት ቢኖር ወይ መታወቅ
ኃይል ቢይዝ ብዙ ንብረት
መዳንን ያመጣ የለም
ከነገስታት ከመላዕክት
ፍቅር የፍቅር ምንጩ
ሌላ ቀራቢ የሌለው
ብቸኛ መጣኝ መስዋዕት
እርቁን በፍትህ የፈፀመው
ከልኮች ሁሉ በላይ ልክ
በጩኸት ይህን መስክሪ
ነፍሴ ትልቁን እውነት ያዥ
ይህንን በደንብ አክርሪ
ከኢየሱስ ውጪ
እውነት የለም
ከኢየሱስ ውጪ
ህይወት የለም
ከኢየሱስ ውጪ
መንገድ የለም
ከኢየሱስ ውጪ ...
ኢየሱስ እውነት
የዘለዓለም ህይወት
ብቸኛ መንገድ
ከሞት ነፃነት
ኢየሱስ ብቻ
ኢየሱስ ብቻ ብቻ
ኢየሱስ ብቻ ...
ከኢየሱስ ውጪ
እውነት የለም
ከኢየሱስ ውጪ
ህይወት የለም
ከኢየሱስ ውጪ
መንገድ የለም
ከኢየሱስ ውጪ ...