አውሬ ብቻ ነው የምወደው ምንም ምግብ አልበላም ሃያአራት ሰዓት ምግቤ ጫት ነው በመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ

  Рет қаралды 89,816

Kesis Hailemelekot Girma Wondimu

Kesis Hailemelekot Girma Wondimu

3 жыл бұрын

Subscribe, Share, Like, Comment እያደረጋችሁ ላልሰሙት አሰሙ ላልነቁ አንቁ! መንፈሳዊነት ይብለጥ! የማዳመጥ ጊዜ ላይ ነን!!!
ቃሉን ደግመን እንመልከተው፡፡ እናስተውል ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ "ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።" (የዮሐንስ ራእይ 12፥9)
"ዓለሙን ሁሉ" ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ጤነኛ ሰው ከላይ በርዕሱ የተጠቀሰውን "እያንዳንዱ ሰው መንፈስ አለበት ወይ?" የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ እንዲችል፤ አስቀድሞ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በግርድፉ እንኳን መገንዘብ አለበት፡፡ እንኪያስ "ዓለሙን ሁሉ" የሚለው ቃል ምን ይነግረናል? ዓለሙን ሁሉ ማለት ምን ማለት ነው? በዓለም አንዳንድ ቦታዎች ላይ አላለም፡፡ በዓለም አብዛኛው ሥፍራ ላይም አይልም፡፡ ዓለምን ሁሉ የሚለው እያንዳንዱን ሰው በሚነካው ቃል ውስጥ፤ ሁሉም የሰው ልጆች እንደተጠቀለሉ ሰማያዊው ቃል ቅልብጭ አድርጎ ይናገራል፡፡ ወደ ዓለም ሁሉ የመጣው ደግሞ እያንዳንዱን የአዳም ልጅ አስቶ ያጠፋው ዘንድ ነው፡፡ መኖሪያውም ታዲያ በአብዛኛው ጊዜ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ነው፡፡ ነገር ግን ይሄንን ያስተውሉ ዘንድ ያላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ በቀደመው ዘመን ከጥቂቶቹ ወገን ሆነው ይህንን ያስተዋሉት የጌታ ደቀመዛሙርት እንዲህ አሉ፤ "ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም_በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፥19)
አሁን ይሄን ጽሑፍ የሚያነቡ ዓይኖች ሦስት ምድብ ላይ ይገኙ ዘንድ ግድ ነው፡፡ አንደኛው ፍጹም ሥጋዊያን ዓይኖች ናቸው፡፡ እነዚህኞቹ እንዲህ አይነት መንፈሳዊ ጉዳይ በምንም ተዓምር አይጥማቸውም፡፡ በሚያነብቡት ጊዜ ከውስጥ በባሕሪይ፣ በልምድ፣ በኑሮ ውስጥ ተመሳስሎ የተቀመጠው አጥፊ መንፈስ አብሮ ስለሚያነብ፤ በነፍስ በኩል አስተውለው የእግዚአብሔር ቃል ሕይወታቸውን እንዲመረምረው ዕድል አይሰጣቸውም፡፡ ስለዚህ ወይ ጀምረው ያቋርጡታል፤ አሊያ ጨርሰው ቢያነቡት እንኳን ደረቅ የሆነ ትርክት፣ ዝም ብሎ የተደረደረ የቃላት ጋጋታ፣ ምንም ከእነርሱ ሕይወት ጋር የሚያገናኘው እንደሌለ አድርገው እንዲገነዘቡት ልቦናቸውን በጠባብ መስመር ላይ አስገብቶ ውስጣቸውን ይገዛዋል፡፡ ሁለተኛዎቹ ከሥጋዊ ወደ መንፈሳዊ ዓይንነት ለመሄድ እየጣሩ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህኛዎቹ በከፊል ይረዳሉ፤ በከፊል አይረዱም፡፡ በሕይወታቸው፣ በጊዜያቸው፣ በአኗኗራቸው፣ በዕድላቸው፣ በቤታቸው ውስጥ ያለውን ጠላት ተገንዘበው እንዲህ አይነት መረጃ ለማግኘት በጣም የሚጓጉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ትልቁ ችግር አንድ እግራቸው ዓለም ውስጥ፤ አንድ እግራቸው መንፈሳዊ እውነት ውስጥ ስለሆነ፤ በመረዳትና ባለመረዳት መካከል እንደጊዜው ከጊዜው ጋር የሚለዋወጡ ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛዎቹ የዓለም መናኞች መንፈሳዊ ዓይን ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ፤ የምድር ኑሮ የጊዜ ቆይታ ብቻ እንደሆነ የተረዱ፤ እያንዳንዷ ሰኮንዳቸው ሰማያዊ እውነትን እንድትረከብ የሚጥሩ፤ የክፉ መናፍስትን አሠራርና ስውር አካሄድ በሕይወታቸው ውስጥ የተገነዘቡ፤ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ እውነትና ኃይል በምግባር ለመያዝ በየቀኑ የሚታትሩ እና የመጽሐፍ ቅዱስን የኑሮ ቅርጽ በእነርሱ ኑሮ ውስጥ አዛምደው የሚያስተውሉት ናቸው፡፡ እያንዳንዷ በእንዲህ አይነት መረጃ ውሰጥ የሚጣሉትን ቃላት በነፍሳቸው ሆነው ያነቡታልና የመኖር መሠረታዊ ትርጉም በደንብ የገባቸው በየቀኑ የሚማሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ እንደ አንባቢው ውስጣዊ ቅንነትና እውነትን የመረዳት አቅም፤ በደረጃው ልክና ጊዜው በሆነለት ልክ ሰማያዊ ቃልን ለሥጋና ለነፍሱ ይገልጥለታል፡፡
የሰው ልጅ በምድር የዕድሜ ቆይታው ሲመላለስ የመኖሩ መሠረታዊ ትርጉም ምንድነው? ሐብታም መሆን ነው? ባለዝና መሆን? በእውቀት ማዕረግ ከፍ ማለት ነው? ባለሥልጣን መሆን ነው? እነዚህና መሰል ዓለማዊ ጉዳዮችን በስኬት መያዝና ማጠናቀቅ ደግሞ የከንቱ ከንቱ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አስምሮ ይነግረናል፡፡ " ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?" (የማርቆስ ወንጌል 8፥36)

Пікірлер: 433
@gubsatadso1049
@gubsatadso1049 3 жыл бұрын
አባየ።።ናፍቆቴ።።ስስቴ።።እንደኔ።።የናፈቃችሁ።።ሁላችሁም።።እንደምን።።ዋላችሁ።።አሜን
@Eminetn
@Eminetn 3 жыл бұрын
አባባ ግርማ አባቴ የማቱሳላን እድሜ ይስጥልኝ መቸ ይሁን እድሉ ሚደርሰን ስራኤል ሀገር መቸ ይሆን ምትመጥሉን አባቴ በእርስወ ትምህርት በመከታተል ከሰይጣን ድኛለሁ አራት እራሴን መኪና ላያችን ወጥቶ ከሞት ተረፍን አባቴ እወድወታለሁ ❤️
@shameershami1017
@shameershami1017 3 жыл бұрын
እግዚአብሔር ሆይ አድነን አድነን ለነሱ የደረሰላቸው ይህ ፈውስ ለኛም ይድረስልን ለአባታችን ረጅም እድሜ ይስጥልን እልልልልልልልልል።
@user-gm5wt2gz2x
@user-gm5wt2gz2x 3 жыл бұрын
እግዚአብሔር ሆይ ሁላቺንን በምህረት አይኖቺህ እየን የአባታቺንንም እድሜ ዘላለም አኑርልን ከጠላት አይንነ ምላሰ ጠብቅልን
@ababaalu9543
@ababaalu9543 3 жыл бұрын
የጫት ስሩ ይቃጠል የኔም ባለቤት ጫት ይቅማል እግዚአብሔር ለአንተ የደረሰ ለሱም ይድረስለት አባ እባክዎ ወልደ መድን ነው የክርስትና ስሙ እኔም እየጸለኩ ነው አንድ ቀን ድል እነሳለሁ በእግዚአብሔር ተስፋ አለኝ
@user-ip3eh9bh9o
@user-ip3eh9bh9o 3 жыл бұрын
አባቴ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን ፀጋውን ያብዛልን አባታችን 💒❤️🤲
@yaredhailu6793
@yaredhailu6793 3 жыл бұрын
በለጬ ያደርጋል ጩጭ እያልን ስንት ዘመን ቃምን እድሜ ለአባታችን ትምህርት አሁን የለሁበትም እባካችሁ share በማድረግ ላልሰሙት እናሰማ ትውልድ እናድን
@user-xf3sc9jy9b
@user-xf3sc9jy9b 3 жыл бұрын
አባ እኛስ መቼ ይሆን የምንፍወስው በርሶ በስው ሀገር እየተንከራተቱ ስርተውት እማይባርክላቼው ስንት እህቶች አሉ
@user-cx1wm8wv1x
@user-cx1wm8wv1x
እግዚአብሔር ይመሰገን አምላኬ እኛም ከእሰራታችን ኤፋታህ ይበለን አሜንንን🙏❤🙏
@Meklit27
@Meklit27 3 жыл бұрын
እግዚአብሔርን እንዴት ላመስግነው? እኚህን የመሰሉ የወንጌል አርበኛ ሰጥቶን ስንቱን ነፍሳት ታደገ? በየገዳማቱ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የክርስቶስን ፀጋ ለብሰው የጠፋትን በጎች የምትሰበሰቡ አባቶቻችንን ሁሉ መድሀንያለም ይጠብቅልን:: ለአባታችን ረጅም እድሜ ይስጥልን ከክፉ ሁሉ ይጠብቅልን::
@user-mu1qf4ed5q
@user-mu1qf4ed5q 3 жыл бұрын
አምላኬ እመብርሃን ይሄ ቀን ናፈቀኝ 😭😭😭😭😭
@user-cw5nb9jc7q
@user-cw5nb9jc7q 3 жыл бұрын
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ለአባታችን ረጅም እድሜና ጤና ያድልልን አሜን፫።
@user-ou2ho1vb3b
@user-ou2ho1vb3b 3 жыл бұрын
ለአባታችን እድሜና ጤናውን ያድልልን ለወገኖቻችን የደረሰ ለኛም ይድረስልን
@user-sz4fg5zn6l
@user-sz4fg5zn6l 2 жыл бұрын
አባታቺን እድሜና ጤና ይስጥልን የኛንምየመፈወሻ ግዜአቺን ያቅርብልን💒💒💒
@hayelileyewu55
@hayelileyewu55 3 жыл бұрын
አባታችን በረከትወ ትደርብን
@ayngedadessie7076
@ayngedadessie7076 Жыл бұрын
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
@user-tw6mo5jk7k
@user-tw6mo5jk7k 3 жыл бұрын
አባታችን እግዚአብሔር ረጅም እድሜና ጤና ይስጥልን ❤️
@yemesgenamlake2000
@yemesgenamlake2000 3 жыл бұрын
አባታችን እድሜና ጤናውን ያድሉት እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ ለወድማችንም ዝማሬ መላእክት ያሰማልን በርቱልን
@sgsgsgsg8142
@sgsgsgsg8142 Жыл бұрын
ለአባዬ ሁሌም ከነቤተሰቦቻቸው ፀጋበረከቱን ያብዛላቸው ተመስገን ሁሉን ስላደረገልን አምላካችን በሳቸው ላይ አድሮ ለሰራልን ድንቅ ስራ የከበረ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን ➕🕯
@user-bx9tz4ey6r
@user-bx9tz4ey6r 3 жыл бұрын
አባየ የኛስ ቀን የምንፈወስበት መቸ ይሆን አባየየየየየ የኔ እንቁ አባት
How Many Balloons Does It Take To Fly?
00:18
MrBeast
Рет қаралды 194 МЛН
Secret Experiment Toothpaste Pt.4 😱 #shorts
00:35
Mr DegrEE
Рет қаралды 33 МЛН
Memehir Girma Wondimu Video 424  ሥልኬ ያለ ሲም ካርድ ይደወልበታል  የ1,000,000 ብር ሎተሪ ደርሶኝ ተቸገርኩ
28:26
Nku Tamirtsion :- በመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ትውልድ ይዳን
Рет қаралды 63 М.
How Many Balloons Does It Take To Fly?
00:18
MrBeast
Рет қаралды 194 МЛН